Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላ | መርጌታ አለምአየሁ

ጤና ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ
በቅንነት ሼር ያድርጉ

ዛሬ ስለ ገንዘብና ቤትሰላቢ መጠበቂያ ስለሆነችው ታምረኛዋ እፅዋት ትንሽ መላ ልበላችሁ ።

#ጉድይኝ
ጉድኝ በብዛት በደጋማው ሀገርና በወንዛንዝ በጎድጓዳ ውሃ ፈረጥ ቦታ የምትበቅል እፅዋት ስትሆን የተለያየ ጥቅም እንዳላት ከሊቃውንቶች ውጭ ብዙም የሚያውቅ የለም ።


ነገር ግን የተለያየ ጥቅምና አገልግሎት ያላት ወሳኝና አስፈላጊ እፅዋትናት
ከጥቅሞቿ በጥቂቱ ፦

፩#ለመፍዝዝ ማክሰኞ ቀን በጥዋት እፅ አንግስ ፯. {7 } ጊዜ ደግሞ በወይራ አንካሴ ቆፍሮ የቀረጥ ተቀፅላ የጠንበለል ተቀፅላ የክትክታ ተቀፅላ የኤሊ አፅም ጨምሮ አንግሶ ከትቦ ቢይዙት ከጠላት ከምቀኛ ይሰውራል ለጠላት አያስነካም።

፪#ለክፉ መንፈስ ቅጠሏን ጭቅጭቆች በውሃ ዘፍዝፎ ጥዋት ጥዋት ፯. (7 ) ማጥመቅ መጠመቅ።
ክፉ ቁራኛን የዛር ውላጅን ያስለቅቃል።

፫#ለቤትሰላቢ መመለሻ የጉድኝ ስር የአንባጮ ተቀፅላ የዘርጭ እንቧይ ስር ሁሉንም በአንድ ከትቦ አንድም በገንዘብ ማስቀመጫ ሳጥን ማስቀመጥ። ሁለተኛ ከቤት ከዱቄትና ከሊጥ ስር ማስቀመጥ ነው
ጠቅላላ የገንዘብ (ብር ) የእህል የሊጥ የዱቄት ሰላቢ በረከት የሚያሳጣ ነገርን በሙሉ ያባራል ከቤት አያስገባም ።

ስለዚህ የማይጠቅምና የማይረባ መስሎ እንደዋዛ የምናየው እፅዋት እሄን የመሰለ ጥቅም አለው።

ጥበብ ታላቋን ታከብራለች።


በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ #ሸር #share ማድረግዎን እንዳይረሱ

➤ የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል


0912 99 97 05 በስራ ሰዓት ይደውሉ