Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም ፍቅር ቅኔ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hollypoem — ግጥም ፍቅር ቅኔ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hollypoem — ግጥም ፍቅር ቅኔ
የሰርጥ አድራሻ: @hollypoem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.33K
የሰርጥ መግለጫ

ግጥም
ቃላትን በንዝረት በምትሃት በዉበት እና በእዉነት አበጃጅቶ እፈጥርልናል
ቁስልን ማከም ተስፋን ማለምለም አቅም አለዉ
ፍቅር
ዉበት እንደ ተመልካቹ እንደሆነዉ ሁሉ ፍቅርም በዚዉ ሊገለፅ የሚችል በተለያየ አንደበት በተለያየ ትሩጋሜ ሊገለፅ የሚችል ረቂቅ የፈጣሪ ልግስና ነዉ
ቅኔ
ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ።
ለማንኛዉም አስተያየት👉 @hollynba

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-08 17:56:45 አየኋት ሰገድኩኝ
አየኋት ተሳልኩኝ
አየኋት አየኋት
ተስዬ አገባኋት
አግብቼም አየኋት
አይቼ አልጠገብኩም
አሁንም መልሼ
ጭኗን ተንተርሼ
በጨረፍታ አየኋት
በአትኩሮት አየኋት
የኋሊት አየኋት
የፊትም አየኋት
ፊቷ አልተቀየረም
ምንም ስህተት የለም
ከእንቁ የምታምር
እፁብ ድንቅ ተዓምር
ከዛን ተደፋሁኝ
እሷን ማየት ልተው
ፈጣሪን ልጠይቅ
አይኔን ከሷ መንቀል ለምን እንዳቃተው?
ጌታ ግን ሳቀብኝ በፀሎቴ አስካካ
ስሩ ተደፍቼም ሳያት አይቷል ለካ
*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ
"
"
@hollypoem
@hollypoem
446 viewsHollY ነኝ, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 17:56:16 ከማ ተዲኑ ቱዳን
(አትፍረድ ይፈረድብሀል)

ከል የለኝ ጠበቃ
ከሰው ፍርድ የሚጠብቅ
ለክሴ ድል የሚያበቃ
ዳኛ የለኝ በሰማይ
ቀና ፍርዱን እንዳያሳይ
አቤት አልል ለአባይ ጠንቋይ
ልቡ እውር ቅንዓት አያይ
ብከሰስ በጲላጦስ መንበር
ፍርዴ በደቦ ግርግር
ሀቅ በነፍስ የሚቀብር
ሀሰት በወንዝ የሚያሻግር
እኔ የለሁበት መለኪያው
የፍትህ ልክ መመዘኛው
አንድ አለኝ ግን አንድ ጠበቃ
ለክሴ ድል የሚያበቃ
አልኮነንኩም በሰው ኃጥያት
አልፈረድኩም በሰው ጥፋት
አልሰፈርኩም በራስ ቁና
ለራስ ያጠበቡት ለሰው ይሰፋልና
ይኸው
ይህ ይቁምልኝ ጥብቅና
ይሁነኝ ለፍርዴ ዋስትና።

ሞሲሳ ደምሴ
405 viewsHollY ነኝ, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 17:55:28 #እሰይ



ከመሳሳት ይልቅ ትክክል መሆንን ሰርክ ስለሚመርጥ፤
ይላል ያገሬ ሰው “ አስር ግዜ ለካ አንድ ግዜ ቁረጥ”።


እኔ ግን እላለው...
በመሳሳትክ ውስጥ የሚገኘው እክል፤
እሱ ነው ቁምነገር እሱ ነው ትክክል።


አሁንም እላለው...
ከትናንቱ ዛሬ በስለ እንድትጎመራ፤
“ አንድ ግዜ ለካ አንድ ግዜ ቁረጥ ” እሰይ ስህተት ስራ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
397 viewsHollY ነኝ, 14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 14:43:41 ስንት ሰዐት ነው ?
""""""""""""""""""""""


ጨርቁ ነትቦ
ሚታይ ወጣት ጎዳናው ላይ ፣
ስንት ሰዐት ነው ?
ይላል አላፊ አግዳሚ ሲያይ ፣
ፊት ነሺው ቢበዛም ሂድ ከዚ የሚለው ፣
አሁንም ድጋሚ ይላል ስንት ሰዐት ነው ?

ስንት ሰዐት ነው ?

ቀጥራው ቀርታ ይሆን ፣
ወይ አርፍዶ ይሆን ፣
ክሩ ፀሀይ አልፎ ዶፍ እየዘነበ ፣
ያገሬው ጎዳና በእንባ ታጠበ ፣
በመናፈቅ እንባ በመጠበቅ እንባ ፣
የቀጠረ ሲቀር አንጀት ሆድ ሲያባባ ።

ስንት ሰዐት ነው ?

ሰው ለመሮጥ ሲድህ ለመኖሩ ሲሞት ፣
ከእርምጃው ሰሌዳ መጠበቅ አቁሞት ፣
ወጋገን በጀምበር ብርሀኑ በፅልመት ፣
ቀን በቀን ሲተካ እድሜ ሲሆን ወረት ፣
መጠበቅ አንቅዞት የወጣቱን አቅም ፣
ሰዐት ካልነገሩት መራመድ አያውቅም ።

ሩብ ጉዳይ ሆነ
አስር ጉዳይ ሆነ ካናቱ ደፈነ ፣
ሰው አይጠረጥርም ራሱን ካመነ ።

ስንት ሰዐት ላይ
ይሆን ቀጥራው የቀረችው ፣
የልቡንስ እምነት የት አስቀመጠችው ፣
ትመጣለች ብሎ ሰአት ለሚቆጥር ፣
ምን ጀግና ይኖራል መቅረቷን ሚነግር ።

እኔም አየሁና የወጣቱን እድል ፣
የመጠበቅ አቅም ከልቤ እንዳይጎድል ፣
ስንት ሰዐት ነው ብዬ ሰአት አልጠይቅም ፣
አለመጠበቅ ነው የመጠበቅ አቅም ።

#በረከትዘውዱ
501 viewsHollY ነኝ, 11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:55:18 "ቃሌ ቃል ባይመስላት ስቀርባት ብትርቅም
ለወጉ ነው እንጂ ጠልታኝ እኮ አታውቅም
"
ብዬ ስነግራቸው ሰዎች ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
በማላቀው ምክንያት
እስቲ ዞረህ እያት
ሲሉኝ አያታለው
መች መልስ አገኛለው
ምንድነው? እላለው
መልሰው ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
"ስከተላት ብትሸሽ ስቀርባት ብትርቅም
ኮርታብኝ ነው እንጂ
ጠልታኝ እኮ አታውቅም "
የሚል ቃል ሲወጣኝ ሳቃቸው ይገናል
አሁን በእናና ሞት ይሄንን ማን ያምናል
እነሱ ያሳቃቸው
እኔ ያስተዋልኩትን መሆኑን ባላውቅም
ጥርሷ ይርገፍና
አብረን ባለን ጊዜ ስቃልኝ አታውቅም

*------------------*

(ሚኪያስ ፈይሣ)
439 viewsHollY ነኝ, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 21:55:17 ፃድቅ ነኝ ባይ በሞላበት በዚህ ከንቱ ዓለም
ያንተ አይነቱን ራስ ወዳድ
ለኔ ማግኘት ብርቄ አይደለም
ይህ ሁሉ የሆነው
ሄዋን ስትል አዳም አዳምም ሲል ሄዋን
ቆይ እስቲ ንገረኝ
ማንኛው ነው ፃድቅ ማንኛው ነው ሀጥአን
በራሱ አምሳያ እግዜሩ ፈጥሮአቸው
ከትንፋሹ ትንፋሽ ነፍስም ዘርቶባቸው
ማስተዋል ልቦና ሁሉን አድሏቸው
የስጋዊ ምኞት ህፀፅ ቢሆናቸው
ሀጥያት ቢያሰራቸው
ማን ማንን እንዲወቅስ ስልጣኑን ሰጣቸው
እርሱን ደ'ሞ ተወው
ቸሩ መድሃኒያለም ከሰማያት ወርዶ
ከድንግል ተወልዶ
ነፃ ቢያወጣቸው
እርሱ ይቅር ላላቸው

የዚህ ዘመን ትዉልድ ምን ስልጣን አግኝቶ
ለ'ምነው ሚወቅሳቸው
የዘመኑ አዳም የዘመኑ ተባዕት
እንኳን በለስ አይደል ሎሚ እንኳን ቢሰጠው
ከመግመጡ አልፎ ፍሬውን አኝኮ ነበረ ሚተፋው
ፍርዱን ለፈራጁ ብተውት ምናለ
ኮንኑልኝ እርሱ ቅጡልኝ መች አለ?
419 viewsHollY ነኝ, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 20:48:25 ከትንቢተኛሽ

ፀአዳ ገላሽን
በንፁህ ጠበል ውስጥ የነከርሽው እለት
አንድ ልጅ ይመጣል ትንቢቴን እመኚ እንዳይመስልሽ ተረት
ተረቱ ለምኔ እርሱ ልጅ ግን ላንቺ
ከመደሰት በላይ እንድትደሰቺ
ታጅቦ ይመጣል
የደፈነሽን ገል ከአይንሽ ላይ ይገልጣል
መንገድሽ ይሰምራል ጎባጣሽ ይቃናል
ድንድን ያለው ልብሽ ድጋሚ ሰው ያምናል
ነብስሽ ትስቃለች
ከልጅ መሀፀንሽ አንቺን መሳይ ቆንጆ ትፈነድቃለች
ትንቢቴን እመኚ
ለፀለይሽው ፀሎት ምላሹ ይላካል
የጨፈነገገው ፀሀይሽ ይፈካል
አፅናፍሽን ሁሉ ደስታ ይሞላዋል
ሁሌ መሳቅ እንጂ
ጥርስሽን መከደን ይከለክለዋል
ተረት እንዳይመስልሽ የምነግርሽ ነገር
ከትንሳኤሽ በፊትእንደምትነሺ
አውቄልሽ ነበር
ትንቢቴን እመኚ
ወረቀትን ይዞ ይመጣል ያ ወጣት
የሚያስደኘግጠው ገፀ ጥርሱ ንጣት
ከጎንሽ ይቆማል ወገብሽን ያቅፋል
ትንፋሹን ስትስቢ አለምሽ ይጠፋል
እጁ ከእግርሽ ሲያርፍ
ባትሽ ይወፍራል
የሳመው ከንፈርሽ ከእንቡጥ ፍሬ ያምራል
ትንቢቴን እመኚ
እርሱ ልጅ ሲመጣ ክፉ አይነካሽም
የፈርኦን ጭፍራ አይዳፈርሽም
አንዲት አንካሳ ዝንብ
ብትንገዳገድም
ባትንገዳገድም አትደረስብሽም
ትንቢቴን እመኚ
አውቃለሁኝ ላንቺ ይሄ ቀልድ ይመስላል
ወረቀቱን ገልብጭ
የጀርባው ማህተም ከሰማይ ቤት ይላል
ፈጣሪ ነው ያፃፈኝ ይህንን ደብዳቤ
ላንቺ ምን ይሰራል
ይዤ ብመጣልሽ እጣንና ከርቤ
ትንቢትን ፃፍኩልሽ
ትንቢት እንደሚሻል እንዳንቺ አስቤ
ፅፌ እንደጨረስኩ
ቃለ ትንቢቴን ቅፅ ይዤልሽ መጣሁኝ
ትንቢቴን አመንሽው
ትንቢተኛው እኔ ፊትሽ ቆሚያለሁኝ
ትንቢቴ ይኸውና
ግን እመኚኝ ቀድመሽ
ግብሩ አይገለጥም
የነገርኩሽ ትንቢት ካልከፈትሽው አምነሽ
እመኚኝ እመኚኝ
ውዴ ተለመኚኝ
ትንቢተኛው እኔ
ትንቢተኛሽ እኔ ከፊትሽ የቆምኩኝ
እንደ ጠዋት ዳዊት ሰርክ አንቺኑ ያልኩኝ
ከመዳፌ እኩል አንቺን ልጅ ያወኩኝ
ከእናትሽ በላይ
ትንቢት ሲያሳርፍሽ ቆሜ ያስተዋልኩኝ
እኔ ያንቺ አሳቢ
እኔ ትንቢተኛሽ
ለደስታሽ ፍሬ ስል ትንቢትን ፅፊያለው
ባማላጂቱ አይን አንቺን የሚያረቁ
የኔን መምጣት መሄድ
እንደ ምፅአት ቀን የሚጠባበቁ
ደቀመዛሙርታት በስሬ አፍርቺያለው
ይህንን ስትሰሚ
ትንቢትነህ ውሸት ነው
የሚል ቃል አታውጪ
ምን አማራጭ አለኝ ትንቢት ለሚገዛሽ
ከመተንበይ ውጪ
እናልሽ የኔዋ
እናልሽ የኔ ቃል
ትንቢቴ እንዲፈፀም ተለመኚኝ አሁን
ትንቢቴን አምነሺኝ
ሞኝ አፍቃሪሽ አና ትንቢተኛ ልሁን
።።።።።። ።።።።።።

(ሚኪያስ ፈይሣ)
426 viewsHollY ነኝ, 17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 20:39:48 የሴት ልጅ ነኝ

እኔ የሴት ልጅ ነኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት የወለደችኝ ፣
9 ወር አርግዛ እኔን የሰራችኝ ፣
በእግሬ እንድቆም መንገድ የሆነችኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት ያሳደገችኝ ፣

እንጀራ ጋግራ ወጥ እየሰራች ፣
እንጨት ተሸክማ ሸጣ እያመጣች ፣
ደከመኝም ሳትል ልብሱን እያጠበች፣
በፀሀይ በብርዱ ጉሊት እየሰራች ፣
ደከመኝ ሰለቸኝ የሚለውን ረስታ ፣
እኔን አኖረችኝ እሷ ለኔ ሞታ፣
እሷ ሳትማር እኔን ያስተማረች፣
አለችኝ አንድ ሰው እናት የተባለች።

እኔ የሴት ልጅ ነኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት የወለደችኝ ፣
9 ወር አርግዛ እኔን የሰራችኝ ፣
በእግሬ እንድቆም መንገድ የሆነችኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት ያሳደገችኝ ።

እሷ በየቀኑ እ የ ቀ ለ ጠ ች ፣
እኔ እዚህ እንድደርስ ሻማ የሆነች ፣
አለችኝ አንዲት ሰው የምትባል ሴት ፣
እኔ እንዳልጠፋ የሆነች መብራት ።

እኔ የሴት ልጅ ነኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት የወለደችኝ ፣
9 ወር አርግዛ እኔን የሰራችኝ ፣
በእግሬ እንድቆም መንገድ የሆነችኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት ያሳደገችኝ ።

አይደለም እኔ ወራዳዋ ቀርቶ ፣
እኛን ይቅር ያለን ወደዚህ አለም መጥቶ ፣
ወልድ እኮ እራሱ በድህረ አለም ፣

ከሴት ነው የተገኘው ከድንግል ማርያም ፣



እኔ የሴት ልጅ ነኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት የወለደችኝ ፣
9 ወር አርግዛ እኔን የሰራችኝ ፣
በእግሬ እንድቆም መንገድ የሆነችኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት ያሳደገችኝ ።

ታዲያ
የሴት ልጅ መባል ያልገባቸው ክብሩ፣
ከሴት መወለዳቸውን የ ሚ ጠ ራ ጠ ሩ ፣
ሲሳደቡ ታዲያ እኔን ያናደኛል ፣
ምንአገባሽ አትበል እኔን ያገባኛል ፣
የሴት ልጅ መባሌ እኔን ያኮራኛል ፣
ሴት ልጅ መሰደቧ በጣም ያናደኛል ።

እኔ የሴት ልጅ ነኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት የወለደችኝ ፣
9 ወር አርግዛ እኔን የሰራችኝ ፣
በእግሬ እንድቆም መንገድ የሆነችኝ ፣
አዎ የሴት ልጅ ነኝ ሴት ያሳደገችኝ ።

አንተም እኮ ቢሆን እዚህ የቆምከው፣
ሴት በሆነችው በ እ ና ት ህ ነው ፣
ስለዚህ እናትህን እውነት ከወደድካት፣
የሌሎችን እናት አክብረህ አሳያት ።

እኔ የሴት ልጅ ነኝ !!! .........

Señorita
520 viewsHollY ነኝ, 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 22:36:52 ሳታነሺው ሲቀር...

ፈገግታ ሳቅሽን ለመስማት ወድጄ
ከአንደበቴ ላይ የያዝኩት ሸምድጄ
ቀልድ አዘጋጅቼ ሳቅሽን ልገራ
ሳታነሺወሸ ሲቀር ስልኩ እየጠራ
ለራሴ ደግሜው ራሴው ሳኩበት
ብቻዬን ስስቅም እብድ ተባልኩበት
(ይሆን እንዴ እብደት?)

ድምፅሽን ለመስማት ላወራሽ ጓጉቼ
ዝርዝር ለቃቅሜ ካርዱንም ሞልቼ
ሳተነሺው ሲቀር ለብዙ አዋልኩት
ከጓደኞቼ ጋር እልፍ አወጋሁበት
ከዛም አልፎ ተርፎ ለሌላ ሰው ላኩኝ
ምስጋና፣ ምርቃት በብዙ አተረፍኩኝ!

በድምፅ ሳንረበሽ በምንም ሳንገታ
ላንቺ ለመደወል ከመረጥኩት ቦታ
ሳታነሺው ሲቀር ስልክሽ ተዘግቶ
አስተውል ጀመርኩ ያልታየኝን ከቶ
ፀጥታው ቢመቸኝ ግጥም ፃፍኩበት
የጥበብን ባህር በብዕር ቀዘፍኩበት!

ሳታነሺው ሲቀር ስልኩ ተከርችሞ
ንዴት ሊያበግነኝ ፊቴ ሳለ ቆሞ
ትርፌን አሰላሁት ካገኘሁት ጥቅም
በኢምንት ጊዜ ውስጥ ያለኝን አቅም

እናምልሽ ውዴ...

ሳታነሺው ሲቀር ልቤ ይህን አመነ
አንዳንዴም መገፋት ለራስ እነደሆነ።

Erma
501 viewsHollY ነኝ, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:29:16 #ተስፋ

ወቅቱ ክረምት ነው::
ዝናቡ ይዘንባል፣
በረዶ ይጥላል።
ቀኑ ብርዳማ ነው ፤
ሙቀት የናፈቀው::

በዚህ የቁር ዕለት
ሰው በማይወጣበት
ህይወት ያለው ፍጡር -
በአውራ ጎዳናው ላይ - በማይታይበት::
ቀዝቃዛ ቤቴ ውስጥ - ዱካክ ባናወዛት
የቆንጆ ሴት አምሮት - በሚወዘውዛት ፤
በበረደው ቤቴ - ትኩስ አካል ይዤ
በይሆናል ምኞት - በሃሳብ ናውዤ
በጠባብ መስኮቴ - አንገቴን መዝዤ...
ወደ ውጭ አያለሁ፡-
ምናልባት የኔ ውድ!
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታወቃል?

የፍቅር አምላክ ደጉ - ከዝናብ ሊያስጥልሽ
ወደ ተከፈተው - ወደ ባዶው ቤቴ
ያስገባሽ ይሆናል፡፡
ዝናቡ ከባድ ነው፣
ማንም የማይደፍረው፡፡
ወጨፎው ይነፍሳል፣
ውሐና በረዶ በበሬ እየገባ -ወለሌን ያርሳል፡፡
ግን መኖሪያ ቤቴ- መዋኛ ቢመስልም
ውስጤ ተስፋ አለና- በሬን አልዘጋሁም፡፡
“ምናልባት የኔ ውድ! -
የእህል ውሐ ነገር
ምኑ ይታመናል?
ወደ እኔ ስትመጭ-
በሩን ከዘጋሁት -
ሰው ያለበት መስሎሽ-
ትዘይኝ ይሆናል!
ብየ ስለማስብ
አለሁልሽ ውዴ፡-
ዝናብ እየመታኝ - ቤቴ እየበረደው
ትመጫለሽ ብዬ - ደጅ ደጁን እያየሁ፡፡
አለሁልሽ ውዴ....

በሙሉቀን
494 viewsHollY ነኝ, 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ