Get Mystery Box with random crypto!

ያቺ ሴት አዳሪ . . . . ንግግር ስትጀምር፥ ፈገግታን አክላ፥ ጥርሷን ታሳያለ | ግጥም ፍቅር ቅኔ

ያቺ ሴት አዳሪ
.
.
.
.
ንግግር ስትጀምር፥ ፈገግታን አክላ፥ ጥርሷን ታሳያለች፤
ስዉሩ ህመሟን፥ ከሰው ለመደበቅ፥ ሠርክ ትስቃለች፤
ህይወቷን ለማኖር፥ አማራጭን አጥታ፥ ኑሮዋ ሲከፋ፤
በኩል ተደልዞ፥ የልጅነት መልኳ፥ ወዝነቱ ጠፋ፤

ያቺ ሴት አዳሪ
.
.
.
አይዞሽ ባይን ያጣች፥ ሁሉም የሚሸሻት፥ ዘማዊት ነች ብሎ፤
ስሜቱ የነዳዉ፥ የሚገዛት ከፍሎ፤
ቁስሏን ልታስታግስ፥በቢራዋ ጠርሙስ፥ ራሷን ደብቃ፤
ሲጋራ ለኩሳ፥ ካፏ ስታላትም፥በእጆቿ አንቃ፤
የሚጮኸው ልቧን፥ በሙዚቃው ንዝረት፥ ዝም ልታሰኘዉ፤
የናወዘ አካሏን፥ በአስረሽ ምቺው ሰበብ፥ ልታደነዝዘዉ፤
በመጠጡ ግለት፥ ጭንቀቷን ለመርሳት፥ ሰክራ ልታጠፋዉ፤

ከሰው ስትገናኝ፥ ፈገግታን አክላ፥ ጥርሷን ታሳያለች፤
ስዉሩ ህመሟን፥ ከሰው ለመደበቅ፤ሠርክ ትስቃለች፤

ይህቺ ሴት
.
.
ከምድራዊዉ ሲኦል፥ ሀዘን ከከበበዉ፥ ከፈቃድ ባርነት፤
መዉጣትን ትሻለች፥ ከቡና ቤት አለም ፥ካለችበት ጽልመት፤
እሷም ተለዉጣ፥ ነገን ታስባለች፥ ኑሮን ለመጀመር፤
ሰርታ ልታስመልስ፥ የጠፋውን ስሟን፥ ያጣችውን ክብር፤
ጨለማውን ገፋ፥ ብርሃን መልበሷን፥ ወጥታ ለመመስከር።