Get Mystery Box with random crypto!

የጥያቄ 1 መልስ መ. አምላክም ሰውም ነው የሚለው ትክክለኛ መልስ ነው! ኢየሱስ ክርስቶስ በመለ | Holistic Bible College

የጥያቄ 1 መልስ

መ. አምላክም ሰውም ነው የሚለው ትክክለኛ መልስ ነው!

ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮታዊ ባህርው ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ የማያንስ ትክክል ወይም እኩል የሆነ የእግዚአብሔር የባህር ልጅ ነው(ዮሐ 1፡3፣ ቆላ 1፡15-16)። ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የእግዚአብሔር ቃል ነው። በቅድመ ዓለም በዘላለም ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል የሆነው ወልድ ድሕረ ዓለም ዓለምን ለማዳን ያለ ወንድ ፈቃድ ከድንግል ማርያም ተወልዷል። ኢየሱስ ክርስቶስ በመጀመሪያውና በዘላለማዊ ባሕርዩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ነው፤ በኋለኛውና በትሥጉት(በሰውነቱ) በያዘው ባሕርዩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከራሱም ባሕርየ መለኮት ያንሳል፤ በባሕርየ መለኮቱ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ እኩል ነው፤ በባሕርየ ትስብእቱ ግን አብና ከመንፈስ ቅዱስ፣ ከራሱም ባሕርየ መለኮት ያንሳል። በባሕርየ መለኮቱ አምላክ፣ በባሕርየ ትስብእቱ ሰው ነው። በባሕርየ መለኮቱ ፈጣሪ ነው፤ በባሕርየ ትስብእቱ ፍጡር ነው። በባህርየ መለኮት አባት አለው፤ በባሕርየ ትስብእቱ አምላክ አለው(ኤፌ 1፡3)። በባሕርየ መለኮቱ ጌታ ነው፣ በባሕርየ ትስብእቱ ባሪያ፣ በባሕርየ መለኮቱ የዳዊት ጌታ፣ በባሕርየ ትስብእቱ የዳዊት ልጅ ነው። በባሕርየ መለኮቱ የማርያም መገኛ (ፈጣሪ) ነው፤ በባሕርየ ትስብእቱ ደግሞ ከማሪያም የተወለደ ነው። በመጀመሪያው ኢውሱን ነው፤ በሁለተኛው ውሱን።

ለበለጠ መረዳት በኦንላይን #በነጻ በሰርተፍኬት ደረጃ የሚሰጠውን ነገረ ክርስቶስ የተሰኘውን ኮርስ ይማሩ!

ያናግሩን @infohbc

#Share to groups

JOIN Channel

@holisticbiblecollege
@holisticbiblecollege