Get Mystery Box with random crypto!

የስነ-ልቦና የምክር አገልገሎት Psyc

የቴሌግራም ቻናል አርማ hiyawkaljordan — የስነ-ልቦና የምክር አገልገሎት Psyc
የቴሌግራም ቻናል አርማ hiyawkaljordan — የስነ-ልቦና የምክር አገልገሎት Psyc
የሰርጥ አድራሻ: @hiyawkaljordan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 979
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ የስነ ልቦና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው የሚቀርቡበት ልዩ ቻናል፡፡

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-03 14:16:51 ፅናት ይኑርህ!

ሰሚ ባጣህ ፣ ጆሮ በተነፈክ ሰዓት ፅናት ይኑርህ ፤ ትኩረት ባልተሰጠህ ፣ ተመልከች ባጣህ ጊዜ ፅናት ይኑርህ ።

አዎ! ለሰዎች እየለፋህ ፣ ለሰዎች እየጣርክ ፣ እየደከምክ ሰዎች ችላ ሊሉህ ይችላሉ ፣ ሰሚ ፣ አዳማጭ ላታገኝ ትችላለህ ፣ አንድም አስታዋሽ ፣ አንድም ተመልካች በሌለበት በብዙ እጥፍ ልትደክም ትችላለህ ። አበረታች ስትፈልግ አታገኝም ፤ አጋዥ ስትመኝ አይኖርህም ፤ ከጎንህ የሚቆም ፣ በሃሳብህ የሚስማማ ባንተ የሚተማመን ሰው ፈልገህ ልታጣ ትችላለህ ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፅናትህ የሚፈተነው በዚህ ሰዓት ነውና ፅናት ይኑርህ ፤ ታግሽ ሁን ፤ በቶሎ እጅ አትስጥ ፤ አትረበሽ ፤ አትታወክ፣ ተስፋ አትቁረጥ ። በብቸኝነት ስሜት ከመዋጥ እራስህን አውጣ ፤ ማንም የለኝም አትበል ። አጋዥ ብታገኝ ፣ ረዳት ቢኖርህ መልካም ነበር ነገር ግን ባይኖርህም እርሱ ከመንገድህ አያስቀርህም ። ያሰብከው ብቻህን መሆኑን እንዳትዘነጋ ። አዕምሮህ ሲጠግብ ፣ ሲመቸው ፣ በእራስ መተማመን ሲኖረው ፣ የነገውን መልካም ውጤት መመልከት ሲችል ፅናት ይኖርሃል ፤ ቢደክምህም ትለፋለህ ፤ ቢያምህም ትችለዋለህ ፤ ቢሰለችህም ትጋፈጠዋለህ ፤ ቢከብድህም ታደርገዋለህ ።

አዎ! የማይሆኑ ተስፋ አስቆራጭ ቃላት በሰማህ ቁጥር ውስጥህን አትረብሸው፤ ትረትህን የሚጎዳ አላስፈላጊ ሃሳብ ቢሰጥህም ያለእርሱ ማደግ እንደማትችል አስብ ። ሳትተች ሙገሳ ላይ አትደርስም ፤ ሳትነቀፍ ለአድናቆት አትበቃም ፤ ሳትሰደብ ከበሬታን አታገኝም ፤ ሳትዘለፍ ብርቱ ወዳጅ አታፈራም ፤

አዎ! የሚደርስብህን አሉታዊ ጫና ሁሉ ዋጥ አድርገው ፣ ተቀበለው ፤ ቅስምህን ከመስበሩ በፊት አንተ እዛው ሰብረህ አስቀረው ፤ ተስፋህን ከማጨለሙ ፣ ራዕይህንም ከማደብዘዙ በፊት ተስፋህን አግዝፍበት ፤ ራዕይህን አርቅቅበት ። ማንም ቢያወራ ግድ አይኖርህም ፤ ሰው ውስጡ ያለውን ፣ እራሱ ያመነበትን ብቻ ያወራልና ማንም አለመቻልህን ቢነግርህ ያንተን ሳይሆን የእራሱን አለመቻል በሚገባ ተረዳው ። ብዙ ጅምር ስራዎች ከነበሩት አንተም እንዲሁ ትመስለዋለህ ፤ ያንተን ፅናትና ጥረት በእራሱ ልምድ ሊለካ ይሞክራል ። አንተ ግን እርሱ እንደማይሆን ፣ እንደማይሰራ አረጋግጥለት ። አንገትህን ደፍተህ ስራ፤ አቀርቅረህ ለህልምህ ኑር ፤ በጊዜው እርሱ ያሳልፍልሃል ፤ እርሱ ቀና ያደርግሃል ፤ በንቀት ላይ ያረማምድሃል ፤ በሳቅ ፣ በስላቅ ላይ ያሻግርሃል ፤ ትቺት ፣ ዘለፋን ሰብስቦ ያስወግድልሃል ፤ ያንቋሸሹህን ያዋርድልሃል ፤ ያበረቱህን ያኮራቸዋል ።

አዎ! በፅናት ታገል ፤ ጠንክረህ ስራ ፤ ውስጥህን ለማርካት ፣ ፍላጎትህን ለመሞላት ተፋለም ፤ ብትመታም ፣ ብትጎዳም ፣ ብታዝንም ፣ ብትሰበርም ከአሸናፊነት ዞር አትበል ፤ ፅናት ይኑርህ ፣ ድልም አድርግ ።
═════════❁✿❁ ═════════
Join አድርጉ ።
140 viewsYoftayh Y., 11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 18:12:35 ስኬታማ ሰዎች ከንፈር ላይ ሁለት ነገር ይስተዋላል፡፡ አንደኛው "ዝምታ" ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ፈገግታ" ነው፡፡

ልንገርህ ስኳርና ጨው አንድ ላይ አደባልቀህ መሬት ላይ ብትበትነው ቁጫጮቹ ጨውን ትተው ስኳሩን አንስተው ይሄዳሉ፡፡ አንተም ህይወትህን የሚያጣፍጡልህን ወዳጆች ምረጥና ጣፋጭ ኑሮን ኑረው፡፡

ግብህ ጋር መድረስ ከተሳነህ መንገድህ እንጂ መድረሻህ አይቀየር፡፡ አስታውስ! ዛፎች ቅጠላቸውን እንጂ ስራቸውን አይቀይሩም፡፡

ደሞም አስታውስ! ለጮኸው ውሻ ሁሉ እየቆምክ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ፈፅሞ ካለምከው አትደርስም፡፡

ክብደት መስጠት ባለብህ ጉዳዮች ላይ ክብደት ስጥ፡፡ ቀለል ማድረግና አንዳንዴም ማለፍ ባለብህ ጉዳዮች ላይ ጊዜህን አታባክን፡፡

ከአሳማ ጋር በጭራሽ አትላፋ፤ ሁለታችሁም ትቆሽሻላችሁ፡፡ አሳማው ግን በመቆሸሹ ቅንጣት አይከፋውም፤ እንደውም ደስ ይለዋል፡፡

መልካም ቀን፤ ቸር ያውለን፤ ቸር ያሰማን
Share and jon
https://t.me/hiyawkaljordan
166 viewsYoftayh Y., 15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 07:17:15 ሁሌም ወረቅ የሆነው ማንነትህ ካነተጋር ይሁን በጊዜ እና በቦታው በውድ ትሽጠዋለህ።
162 viewsYoftayh Y., 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 20:31:18 እያለህ አጊጥበት!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
አዎ! ዘላለም አብሮን የሚቆይ ነገር የለም፤ የእኔ የምንለው የገዛ አካላችን እንኳን አንድ ቀን ይከዳናል፤ ያረጃል፤ ያልፋል፤ ይጠፋል፤ እንዳልነበርም ይሆናል። የሆነው ሆኖ፣ የሆነው ላይቀየር፣ ያልሆንከውን ላትሆነው "እንደዚህ ቢሆን፣ እንደዛ ቢሆን ይሻለኝ ነበር" በማለት ማማረጥህንና ያለህን ማማረርህን አቁም። እንዳለህ ማመስገን ትችላለህ፤ ያለህን መውደድ፣ ማድነቅ፣ ማሞገስ፣ በእርሱም መኩራት ትችላለህ። ተጨማሪ ነገር እየፈለክ ያለህ እስኪወሰድ አትጠብቅ።
አዎ! ጀግኒት..! ተፈጥሮ አስውቦሽ፣ ዋናውን ነገር ሰቶሽ ሳለ በሰው ሰራሽ በጊዜያዊ ቁስ ለማጌጥ አትሽቀዳደሚ። ተጨመሪ ቁስ የሚያስፈልግሽ ጊዜ እስኪደርስ ባለሽ ማማርን፣ በተሰጠሽ መዘነጥን ተለማመጂ። ዛሬ ያለሽ ሁሉ ጊዜው ያልፋል፤ ያረጃል፤ በጊዜው ግን በነፃነት ተጠቀሚበት፤ ውደጂው፣ ተቀበይው፣ ተደሰቺበት። አሁን ሁሉ ነገርሽ ሙሉ ነው፣ ውብ ነው ከጊዜ ቦሃላ ግን ላይሆን ይችላል። ሙሉና ውብ ሆነሽ ሳለ የጎደለሽና ያነሰሽ ነገር እንዳለ ተጨማሪ ነገር ከማሳደድ ብትቆጠቢ በእራስሽ እንድትኮሪ ያደርግሻል።

አዎ! ጀግናዬ..! ከሌለ የለም፤ ካለፈም አለፈ፤ ከቀረም ይቀራልና እያለህ አጊጥበት፤ ድመቅበት፤ ታይበት። ዛሬ ሰውነትህን እንደፈለክ ማዘዝ ትችላለህ፤ ተነስ ስትለው የሚነሳ፤ ተቀመጥ ስትለው የሚቀመጥ፣ የፈለከውን የሚፈፅምልህ ብርቱና ጠንካራ ሰውነት አለህ። አንድ ቀን ግን ላትቆጣጠረው ትችላለህና በእጅህ እያለ ተጠቀምበት፤ ያሰብከውን ሁሉ በጊዜ ከውንበት። የሚያደምቅህን ተጨማሪ ጊዜያዊ ነገር ከምትፈልግ ባለህና በተፈጥሮዓዊ ነገር ደምቀህ ለመታየት ሞክር። ያለህን፣ የተሰጠህን፣ ያንተ ብቻ የሆነውን እያንዳንዱን ስጦታህን ተጠቀም፤ ኩራበት፤ አጊጥበት። የቀረብህን ጥቂት ነገር ፍለጋ ያለህን፣ የተሰጠህን ውድ ሰጦታም ዋጋ አታሳጣው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
181 viewsYoftayh Y., 17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:15:04 ማራኪ ስብዕና እንዲኖርህ ከፈለክ ሌሎችን እንዳንተ ማድረግ የለብህም።

ይልቁንም ከእነሱ ጋር በምትሆንበት ጊዜ ስለ ራሳቸው ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ አለብህ!


ማጋራት መተሳሰብ ነው!

213 viewsYoftayh Y., 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 08:59:14 ጓደኛን ስትመርጥ . . .

አመለካከትህ የምትመርጠውን ጓደኛ ይወስናል፤ አብረህ የምትከርመው ጓደኛ ደግሞ በተራው አመለካከትህን የመወሰን ጉልበት ስላለው ወደ ሕይወትህ ዘልቆ እንዲገባ የምትፈቅድለትን ሰው በጥንቃቄ ምረጥ፡፡

“ጓደኝነት እንደ ሊፍት (Lift / Elevator) ነው፡፡ ወይ ወደላይ ያወጣሃል ወይም ደግሞ ወደታች ያወርድሃል” የሚል አባባል አለ፡፡ ሌላ ረዘም ላለ ጊዜ የከረመ አባባል፣ “በአጠገብህ የሚገኙ የአምስቱ ቅርብ ጓደኞችህ ጭማቂ ነህ” ይላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ልቦናን የሚያነቃ እውነት ይዘዋል፡፡ የቅርብ ጓደኞችህን የያዝክበት የራስህ የሆነ ምክንያት ቢኖርህም፣ ለውጥ ለማምጣት በምትፈልግበት ጊዜ በዙሪያህ የሚገኙት ሰዎች ምን አይነት ሰዎች አንደሆኑ ማሰብ መጀመርህ አይቀርም፡፡

ከዚህ በታች ጓደኛን ስትመርጥ ሊኖርህ ስለሚገባ የምርጫ መመዘኛ የሚያስተምሩ ነጥቦችን ታገኛለህ፡፡

1. “ወደ ላይ” ምረጥ፡- የማደግና የመሻሻል ፍላጎቱ ካለህ የምትይዛቸው ጓደኞች ከአንተ ከፍ ያሉ እንዲሆኑ ትመከራለህ፡፡ ከፍ ያሉ ሰዎች ከፍ ያደርጉሃል፡፡ የበሰሉ ሰዎች ብስለትን ያስተዋውቁሃል፡፡ ይህንኑ ተመሳሳይ መርህ በመከተል የአንተን ላቅ ያለ ደረጃ ፍለጋ አንተን የሚቀርቡህ ሰዎች የመኖራቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንተ ግን ወደ ላይ መመልከትህን መዘንጋት የለብህም፡፡

2. ተመሳሳይ መርህ ያለውን ምረጥ፡- በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት ሳንክድ፣ አመለካከትንና መርህን አስመልክቶ ግን ተመሳሳይነት ያላቸውን ሰዎች መቅረብ ስኬታማ ያደርግሃል፡፡ መርህን አስመልክቶ ልዩነታችሁ ከጎላ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መያዝ፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ልዩነትን በማስታረቅ ዙሪያ የሚሽከረከር ግንኙነት ውስጥ እንድትቀር ያደርግሃል፡፡

3. ተመሳሳይ ግብ ያለውን ምረጥ፡- የዚህ ምርጫ ጥቅሙ የመደጋገፍና የመበረታታት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንተ ያለህ ግብ ሕብረተሰብህን የማገልገል ከሆነና የቀረብከው ጓደኛ ዋና ግቡ በገንዘብ የመበልጸግ ብቻ ከሆነ የጋራ የሆነን ሃሳብ በመወያየት የሞራልና የተግባር ድጋፍ መለዋወጥ ሊያስቸግራችሁ ይችላል፡፡

4. በስኬትህ ደስ የሚለውን ምረጥ፡- በተሳካልህ ቁጥር ከአንተ ጥቅምን እንደሚፈልግ የሚያሳይ፣ ስለስኬትህ ስትነግረው ብዙም ሃሳብ የማይሰጥ፣ ስኬትህን አስምልክቶ ከአንተ ጀርባ ለሌሎች የሚያወራና የመሳሰሉት ባህሪይ የሚያንጸባርቅን ሰው ጓደኛ ከማድረግህ በፊት ደግመህ ልታስብበት ይገባል፡፡

5. በውድቀትና በችግር የማይለይህን ምረጥ፡- ሁሉም ነገር በተሟላልህ ወቅት አብሮህ ሆኖ፣ ሁኔታዎች እንደ ቀድሞው አልሆን ሲሉህና ነገሮች ሲፈራርሱብህ ከአንተ ዘወር የሚል ባህሪይ ያለበት ሰው አይበጅህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ከአንተ ከሚያገኙት ጥቅም አንጻር ብቻ የሚቀርቡህ ናቸውና ስሜትህን ጠብቅ፡፡

6. እውነቱን የሚነግርህን ምረጥ፡- እውነቱን የማይነግርህ ሰው ከምታይበት ባህሪ አንዱ አንተ ጋር ሲሆን አንተን ደስ የሚልህን ብቻ እየመረጠ የመንገር ሁኔታ ነው፡፡ እውነተኛ ወዳጅ ግን እየወደደህና እያከበረህ፣ ቢያምህም እውነቱን ይነግርሃል፡፡ ይህ አይነቱ ሰው ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም፡፡ .......

https://t.me/hiyawkaljordan
262 viewsYoftayh Y., 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 23:15:45 ካለፈው መፋታት

ካለፈው መፋታት ማለት የትናንትን ስህተት በማረም ወደ ፊት መዝለቅ ማለት ነው፡፡ ምንም ብሻሻልና መሳሳት እንደሌለብኝ ባውቅም እንኳ ስህተት ከመስራት ነጻ የምሆንበት ዘመን በፍጹም ሊመጣ እንደማይችል ማወቅ አለብኝ፡፡ ዋናው ቁም ነገር ስህተቴን በማመንና በማረም ወደ ፊት የመገስገሴ ጉዳይ ነው፡፡

ያለፈውን እያሰቡ በጸጸት መኖር የእስር ቤቶች ሁሉ እስር ቤት ነው፡፡ ራሱን በመምራት የበሰለ ሰው ካለፈው ስህተት ራሱን መርቶ በማውጣት የወደፊቱ ላይ ያተኩራል፡፡ ሁሉን ካረመና ካስተካከለ በኋላ ወደ ፊት ይራመዳል፡፡

ከስህተት ባሻገር ለመሄድ ልታስታውሳቸው የምትችላቸው እውነታዎች፡-
1. ከመንቀሳቀስ አታቁም፡፡
ስህተት የማይሰራ ሰው የማይንቀሳቀስ ሰው ብቻ እንደሆነ እወቅ፡፡ ስህተትን ፍራቻ የማይነቀሳቀስ ሰው ሌላ የከፋ ስህተት እየሰራ ነው፤ ያለመንቀሳቀስን ታላቅ ስህተት! እስከተንቀሳቀስኩ ድረስ መሳሳትና ተደናቅፎ መውደቅ የማይቀር ነው፡፡

2. ለስህተትህ የምትሰጠውን ምላሽ አስተውል፡፡
የስህተትን ውጤት የሚወስነው ለስህተቱ የምትሰጠው ምላሽ እንጂ ስህተቱ ራሱ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎችን የሚያጠፋቸው የሰሩት ስህተት ሳይሆን ለስህተቱ የሚሰጡት ምላሽ ነው፡፡

3. ስህተትን አትድገም፡፡
የስህተት አስከፊ ገጽታ ያለው ስህተት ተደግሞ ሲሰራ ነውና ስህተትህን ከአንዴ በላይ ላለመድገም ወስን፡፡ ስህተትን የሚሰራ ሰው፣ “ሰው” ይባላል፡፡ ያንኑ ስህተት ደጋግሞ የሚሰራ ሰው ደግሞ “ሞኝ” ይባላል፡፡
393 viewsYoftayh Y., 20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 08:02:25 በዝምታ ተጓዝ፤ በፀጥታ እደግ!
፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨
ዝም ብለህ መንገድህን ቀጥል፤
አርምጃህን አጠንክር ወደፊት ብቻ ተራመድ፤
አድማጭ አትፈልግ አበርታች አትሻ። ብርታትህ እይታህ ነው፤ ጥንካሬህ አመለካከትህ፣ ግንዛቤህ ነው። ከአሰናካይ ምላስ እራስህን ቆጥብ፤ ከአወዛጋቢ ንግርት እራስህን ሸሽግ።
አዎ! ዝምታ ውስጥ ብርታት አለ፤ እርጋታ ውስጥ ጥንካሬ አለ። ምላስህ ጉድ እንዳይሰራህ ተጠንቀቅ፤ ቃላባይና አስመሳይ እንዳያደርግህ ተጠበቅ። ተናግሮ የሚያደርግ ለቃሉ ታማኝ ነው፤ ተናግሮ በቃሉ የማይገኝ፣ ወሬ ብቻ የሆነ ግን ቃላባይ እንኳን ለሌላው ለእራሱም ያልታመነ ነው። ከእዚ ሁሉ ሰጣገባ፣ ከዚህ ሁሉ አስገማችና አስኮናኝ ተግባር ምንናልባት የሚፈጠረው ነገር አይታወቅምና ለማድረግ ያሰብከውን ቀድመህ አትናገር፤ እርምጃህን ግልፅ አታድርገው፤ ለእውቅና አትልፋ፤ በቅድሚያ ውጤቱን እራስህ አጣጥም።
አዎ! ጀግናዬ..! በዝምታ እደግ፤ በፀጥታ እራስህን አጎልብት። ዛሬና ነገህን በትጋት ወጥረው፤ ከነገ ወዲያ አንደበትህን ሳይጠብቅ ትጋትህ፣ ልፋትህ አንደበት አውጥቶ ይናገርልሃል፤ የዝምታህንም ውጤት ያሳይልሃል። ቀድመህ ስላወራህ ከምታገኘው ይልቅ የምታጣው ይበዛልና አንደበትህን ቆጥብ፤ በስራህ በርታ፤ ተበራታ፤ እጅ እንዳትሰጥ።
በማውራት የተጠመደ ሰው ስላየህ ብቻህ በእርሱ መንገድ አትጓዝ፤ እያወክ የመታበይ ወጥመድ ውስጥ አትግባ። መሰናክልህን አታበጅ፤ ለውድቀት እራስህን አታመቻች፤ በርህን አትክፈት። ሰንቶች በምላሳቸው ወደቁ፤ ስንቶች በጥድፊያቸው ተቀጡ፤ ስንቶችስ ቀደም ቀደም በማለታቸው ነገሮችን አበላሹ።
አዎ! ባልበዛ ዝግታ፣ ባልተዋጠ ዝምታ እራስህን ቃኝ፤ እራስህን ደብቅ። ድምፅህን አጥፍተህ እራስህ ላይ ስራ፤ ማንም እንዲያሞካሽህ፣ ማንም ስላንተ እንዲያወራ አትጠብቅ። ከስራህ በላይ ማንም ሊያወራለህና ዋጋህን ሊከፍልህ እንደማይችል እወቅ። የማያቋርጠው ጥረትህ ወደፊት ይመራሃል፤ የማይቋረጥ ገቢ ያስገኝልሃል፤ ያሰብክበት ስፍራ ያደርስሃል፤ ስትጀምር ለእራስህ ቃለ ለገባህለት ቦታ ያበቃሃል።
አዎ! ወሬህን ቀንስ፤ ተግባርህን ጨምር፤
ክባድህን አጥፋ፤ በምግባር ስራ፤
በምንም አትታበይ፤ ስራህ ላይ ብቻ አተኩር።
በዝምታ ተጓዝ፤ በፀጥታ እደግ!
ውብ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

SUBSCRIBE ማድረጎን እንዳይረሱ!
https://t.me/hiyawkaljordan
392 viewsYoftayh Y., 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:57:20 The power of silence !!!

ዝምታ ውስጥ ውሳኔ አለ፤ ዝምታ ውስጥ አመጽ አለ፤ ዝምታ ውስጥ ማንም ያላየው ሃይል አለ፤ ዝምታ ውስጥ ጨለማ አለ፤ ዝምታ ውስጥ ብርሀን አለ፤ ዝምታ ውስጥ ማእበል አለ፤ ዝምታ ውስጥ ዛሬ አለ።

የዛሬ ማንነታችን የትናንት ዝምታችን ጽንስ ውጤት ነው። ዝምታ (Silence) ህመም አለው። ህመሙ ግን ለአዲስ ነገር ነው። ብዙ ነገሮቻችን ቅርጽ የያዙት በዝምታችን ውስጥ ነው። በብዙዎቻችን ውስጥ ያላየነውና ያልሰማነው አንድ ታላቅ ሀይል አለ። ይህ ሀይል እኛ ያላየነውን አይቷል፣ ያልሰማነውንም ሰምቷል።በዝምታችን ወቅት ይህ ሀይል ብዙ ለውጦችን በውስጣችን ጸንሷል። እስኪወለድ ግን ጸጥታ ይፈልጋል።
399 viewsYoftayh Y., 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 08:39:21 ጥፋቱን ከማይቀበል ሰው ጋር በደልከኝ እያልክ መከራከር መልሰህ ራስህን መበደል ነው።
504 viewsYoftayh Y., 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ