Get Mystery Box with random crypto!

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /5/ ▹ ጳውሎስ ጴጥሮስን ተቃወመው (2÷11-14) ▹ | ሕያው ቃል

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /5/

▹ ጳውሎስ ጴጥሮስን ተቃወመው (2÷11-14)

▹ ጴጥሮስ ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወሙት ። በዚህ ክፍል በጳውሎስና በጴጥሮስ መካከል ሰለተነሣው ከፍተኛ አለመግባባት እናነባለን ። ጳውሎስ ፊት ለፊት መናገሩን እንጂ አለማማቱን እናስተውላለን ። እኛም እንዲህ ከወንድሞቻችንና እህቶች በሚፈጠረው አለመስምማት ፊት ለፊት እንወቃቀስ ። ወንድማችንንና እህታችንን በማማት ኃጢያት ውስጥ አንግባ ።
ጴጥሮስ ተሳስቶ ነበር ። ስህተት እንዳደረገ ራሱ እንኳን ተቀብሎአል ። ስህተቱም ለራሱም ለሌሎችም የተገለጠ ነው ።

(12) በጳውሎስና በጴጥሮስ መካከል የነበረው አለመግባባት በመሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ላይ ሳይሆን ከባሕርይ የተነሳ ነበር ። ከአሕዛብ ወገን የመጡ ክርስቲያኖች የአይሁድ ወግና ሥርዓት የግድ መፈጸም የለባቸውም በሚል ሐሳብ ጴጥሮስ ተስማምቷል ። ከአይሁድ ወገን የሆኑ ጴጥሮስ እንኳን የአይሁድ ወግ አይጠብቅም ። በእርግጥ ኑሮ እንደ አሕዛብ ነበር (በቁ 14) ። የጴጥሮስ ስህተት ምን ነበር ? በቀላሉ በአንጾኪያ ካሉ አሕዛብ ክርስቲያኖች ጋር መብላትን ሰለተወ ነበር ። ይህን ለምን አደረገ ? ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ የመጡ ከንዳንድ አይሁዳውያን «ወንድሞች» አይሁዳውያን ከአሕዛብ (ከአረማዊ) ለምግብ በአንድነት መቀመጥ የለበትም ስላሉ ነው ። እነዚህም ሰዎች ከተገረዙት ወገን የሆኑ አይሁዳውያን ነበሩ ። እነርሱም ለመዳን መገረዝ አስፈላጊ ነው ብለው ያስተምራሉ ። ስለዚህ ጴጥሮስ እነዚህን ሰዎች በመፍራት ልክ ከአሕዛብ ክርስቲያኖች ጋር በማዕድ ኅብረት እንደማያደርግ ሰው ራቀ ። በአይሁድ አመለካከት አረማውያን «የረከሱ» እንደሆኑ ይቆጥራሉ ። ሰለዚህ አይሁዶች ከአረማዊ ጋር መመገብ እንደ እነርሱ የረከሰ ያደርጋል ብለው ያምናሉ ። አይሁዶች ወደ ክርስትና ከመጡ ብኋላ እንኳን እንዲህ ያለ የተሳሳተ አመለካከት ከአእምሮአችን ቶሎ አይወገድም ። ጴጥሮስ እራሱ ከአረማውያን ክርስቲያኖች ማግለሉ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል ። ወደ ክርስትና የገቡ አይሁዶችና አረማውያን በእግዚአብሔር ፊት እኩል እንደሆኑ ያውቃል (የሐዋ 10÷27-28 ፣ 15÷7-9 ፣ገላ 3÷28) ። ነገር ግን ጴጥሮስ የጥንቱ ፍርሃትና ወግ አሸንፎት ስህተት ላይ ጣለው ። እኛም ከሌላው ክርስቲያን ጋር በብሔር ወይም በቆዳ ቀለም ምክንያት ኅብረት ላለመፍጠር ወይም ላለመመገብ ባንፈልግ በክርስቶስ ላይ ኃጢአት እንደሰራን እንወቅ ።

(13) በአንጾኪያ የነበሩ ክርስቲያን አይሁዶች ከጴጥሮስ ግብዝነት ጋር ተባበሩ ። ይህም ግብዝነት የተባለበት ምክንያት እነዚህ ሰዎች በአንደበታችው አይሁድና አረማዊ በክርስቶስ አንድ ናቸው እያሉ በተግባር ግን ክርስቲያን የሆኑትን አረማውያን የበታችና ርኩስ አድርገው ይቆጥሩፈሯቸው ነበር ። ከዚህም ሁኔታ በተለያዩ መንገዶች ወደተሳሳተ ነገር በቀላሉ እንዴት እንደምንነዳ እናስተውል ። ታላላቅ መሪዎች የሚባሉት ጴጥሮስና በርናባስ እንኳን ስህተት ውስጥ ወድቋል ። መሪዎች ሲሳሳቱ ሌሎችን ወደ ስህተት ይዘው ይገባሉ ። መሪዎች በተለየም ለአዳዲስ ክርስቲያኖች መልካም ምሳሌች ሊሆኑ ይገባቸዋል ። (ማር 9÷24)

(14) በሐዋርያት ሥራ 15÷13-19 እንደ ተገለፀው በኢየሩሳሌም የነበሩት መሪዎች ወደ ክርስትና የገቡት አረማውያን የአይሁድ ሕግ የግድ መከተል እንደሌለባቸው ተስማምተዋል ። አይሁድና አሕዛብ በክርስቶስ በማመን በጸጋ እንደሚድኑ ይህ የወንጌል እውነት ነው ። ጴጥሮስ ከእውነት ጋር ተስማምቷል (የሐዋ 15÷7-11) ። በተጨማሪም እንደ አረማዊ ኑሯል ። አሁን ግን ከአረማዊ ወገን ከመጡ ክርስቲያኖች ጋር ለመብላት አለፈቀደም ። ምክንያቱም አረማውያን «ያልነጹ/ርኩስ» ሰለሚባሉ ነው ። ከጴጥሮስ ባሕርይ እንደሚታየው « የአይሁድ ሕግ ካልተከተላችሁ ከእናንተ ጋር አልበላም » ለአረማውያን በድርጊቱ መናገሩ ነው ። በዚህም መንገድ ወደ ክርስትና የገቡ አረማውያን የአይሁድ ወግ ፣ ሕግ እንዲከተሉ ማስገደዱ ነበር ።

▹ አንዳንድ ገለጻዎች

▹(በቁ.ር 11) አይሁድ በሚለው ቃል ፋንታ አንዳንድ ትርጉሞች «የተገረዘ» ይላሉ ።ይህም በመጀመሪያ በግሪክ መጸሐፍ እንደተጻፈው ሲሆን በትርጉም አንድ ናቸው ።
▹(12) አሕዛብ የሚለው ቃል በመጀመሪያ የግሪክ መጸሐፍ «ያልተገረዙ» የሚል ሲሆን በትርጉም አንድ ናቸው ።
▹(13) ቀኝ እጅን መስጠት (መጨበጥ ) በአብዛኛውን ሕዝብ ዘንድ ኅብረት ምልክት ነው ። በጳውሎስ ዘመንም እንዲሁ ነበር ።
▹(14) አንጾኪያ በሰሜን ሶርያ ዋንኛ ከተማ ነች ። በአንጾኪያ የቤተክርስቲያን መመስረት በሐዋርያት ሥራ 11÷19-25 ላይ ተዘግቦ ይገኛል

ይቀጥላል
ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe , Follow እና Share ያድርጉ :-

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid036avLND9y5yFnfpbMcmXf42UYCh1RHeynqpCAAEg58GtPff2PBEMtmdDXWT6beqZFl/?app=fbl Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur