Get Mystery Box with random crypto!

#የነብያት_ታሪክ #ኢሳ_እየሱስ_ዐለይሂ_ሰላም                  ይህ ወሬ አ | History of islamic

#የነብያት_ታሪክ

#ኢሳ_እየሱስ_ዐለይሂ_ሰላም
                

ይህ ወሬ አይሁዳውያን ዘንድ ሲደርስ አይሁዳውያኑ እጅጉን ተቆጡ....እሱ ዘንድም ተሰብስበው ሊፈትኑት፦"የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሞት ቀስቅሰቅልን" አሉት።
ዒሳም ለጌታው በመተናነስ ህዝቡ ያምን ዘንድ ዱዓ በማድረግ የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሙታን መንደር ቀስቅሶ ከፊታቸው አቆመላቸው።አይሁዳውያንም ስለ ኑህ ዘመን ስለተከሰተው ጠየቁት...ሳምም ሁሉንም ነገራቸው'ና ተመልሶ ሞተ።
በዚህ ሁኔታ ለኢስራኢላውያን የተለያዩ ተዐምራትን ባሳያቸው ቁጥር ጥሜታቸው ይልቅ ይጨምር ነበር።
ዒሳ ለኢስራኢላውያን ከጭቃ የወፍን ቅርፅ ሰርቶ ትንፋሹን ሲነፋበት በአላህ ፍቃድ ወፍ ይሆን ነበር።በዘመኑ መድሀኒት የሌለውን የለምጥ በሽታን በአላህ ፍቃድ ይፈውስ ነበር። ማየት የተሳናቸውንም በአላህ ፍቃድ ይፈውስ ነበር።ነገር ግን አብዝሀኛዎች የጥሜትን መንገድ አሟሙቀው ይዘውት ነበር።
ይህ ሊሆን የቻለውም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አንድን ነብይ ወደ ህዝቡ ሲልከው ያ ህዝብ የተካነበትን የጥበብ ዘርፍ ለዝያ ነብይ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይሰጠው ነበር።
ለምሳሌ፦ በሙሳ ዘመን የድግምተኞች መራቀቅ የድግምትን ጫፍ ደርሶ ነበር። አላህም ድግምትን የሚያስንቅ ግሩም ተዐምር ለሙሳ ሰጠው።
በዒሳ ዘመንም አይሁዳውያን የህክምናን የጥበብ ጫፍ ደርሰው ነበር።አላህም የነሱን ጥበብ በሚያስንቅ ሁኔታ ለዒሳ ሰጠው።
በረሱላችንﷺ ዘመንም ቁረይሾች የንግግር እና የስነፅሁፍ ጥበብን ከየትኛውም ትውልድ በላይ ተክነውበት ነበር። አላህም የሁሉንም የንግግር ስልት በሚያስንቅ ሁኔታ የቁርአንን ተዐምር አወረደላቸው።
በዚህ ሁኔታ በዒሳ ዘመንም የነበሩ ህዝቦች ከፊሉ በዒሳ ነብይነት ሲያምን አብዝሀኛው ደግሞ ኩፍርን በመምረጥ የዒሳ ጠላት ሆኑ።
ከእለታት አንድ ቀን ዒሳ አላህን፦"ጡባ ምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።
አላህም፦"አንድ ተክል ናት...። እኔ ነኝ በእጄስ የተከልኳት..።ለጀነቶችም ሁሉ አድርግያታለሁ...። ስሯ ከሪድዋን ነው...።ውሀዋም ከተስኒም ነው...።ቅዝቃዜዋም እንደ ካፉር ነው...። ጣዕሟም የዘንጀቢል ነው...። ሽታዋም የሚስክ ነው...። አንድ ግዜ ከሷ የተጎነጨ እስከዘለአለም ጥም አያገኘውም" አለው።
ዒሳም፦" ያ ረብ...እስቲ ከሷ ለኔም አጠጣኝ" አለው።
አላህም፦"ያ የሚጠበቀው ነብይ ከመጠጣቱ በፊት የትኛውም ነብይ እንዲጠጣ አልተፈቀደለትም።የዚያ ነብይ ኡመቶችም ከሷ ከመጠጣታቸው በፊት ለየትኛውም ኡመት መጠጣት አልተፈቀደለትም" ብሎ መለሰለት።
አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ዒሳ ሆይ!!! ወደ እኔ(ወደ ሰማይ) ከፍ አደርግሀለሁ"አለው።
ዒሳም፦" ለምን ያ ረብ...?" አለ።
አላህም፦"አሁን ወደ ሰማይ የምሰቅልህ በመጨረሻው ዘመን የዚያን ነቢይ ኡመቶች አጃዒብ ልትመለከት እና የተረገመውን ደጃልንም ልትገድልላቸው አወርድሀለሁ።በሰላት ሰዐት ላይ ሳሉ አወርድሀለሁ ከዚያም አንተ ኢማም ሆነህ አታሰግደቸውም...ምክንያቱም የታዘነላቸው ኡመቶች ስለሆኑ" አለው።
ዒሳም፦" ያ አላህ...ስለኒዝያ ስለታዘነላቸው ኡመቶች ንገረኝ" አለው።
አላህም፦"ዒሳ ሆይ! የአህመድ ኡመቶች እኮ በጥበብ የመጠቁ ዑላማኦች ሲሆኑ ልክ ነቢያትን ይመስላሉ(ኡለማኦቹ)።
እኔ ትንሽ በሰጣኋቸቅ ፀጋ ይደሰታሉ፤ እነሱም ትንሽ በሰሩት ዒባዳ እደሰትባቸዋለሁ። ላ ኢላሀ ኢለላህ በምትለዋም ቃል ጀነትን አስገባቸዋለሁ።
ዒሳ ሆይ!!!! እነሱ እኮ አብላጫው የጀነት ነዋሪያን ናቸው። ምክንያቱም የነሱ ምላሶች ለ(ላኢላሀ ኢለላህ) የተናነሱትን ያህል የማንም ኡመት አልተናነሰም።የነሱ ትከሻዎች ለኔ ሱጁድ በማድረግ የተናነሱትን ያህልም የማንም ኡመት ትከሻም ለኔ ሱጁድ በማድረግ አልተናነሰም" አለው።
በሌላ ቀንም ዒሳ አንድ ትልቅ ተራራ ላይ አላህን እያመለከ ሳለ ኢብሊስ መጣ።ወደ ዒሳም ጠጋ ብሎ፦"አንተ አይደለህ እንዴ ሁሉ ነገር በቀዳ እና በቀደር ነው እያልክ የምትሰብከው" አለው።
ዒሳም፦"አዎና" አለው።
ኢብሊስም፦"እስቲ ከዚህ ተራራ ዝለል'ና ቀደር ነው በል" አለው።
ዒሳም፦" አንተ እርጉም..! አላህ ባሪያዎቹን ይፈትናል እንጂ ባሪያዎች አላህን አይፈትኑም" አለው።
ኢብሊስም፦"የመርየም ልጅ ሆይ!!! አንተ የአምላክነትህ ልቅና በልጅነትህ እንድትናገር አድርጎሀል" አለው።
ዒሳም፦"ልቅናም ሆነ አምላክነት ያ በልጅነቴ ላናገረኝ እና አኑሮ ለሚገድለኝ አላህ ብቻ ነው" አለው።
ኢብሊስም፦"የመርየም ልጅ ሆይ!!! አንተ በአምላክነትህ ልቅና ሙታንን ህያው አድርገሀል" አለው።
ዒሳም፦"ልቅናም ሆነ አምላክነት ያ የፈለገውን ህያው ለሚያደርግ አላህ እና እኔ በሱ ፍቃድ ህያው ያደረግኩትን ለሚገድለው አላህ ነው" አለው።
ኢብሊስም፦ወላሂ አንተ እኮ በሰማያትም በምድርም ጌታ ነህ" አለው። ይህን ግዜ ጂብሪል በክንፉ ኢብሊስን በከፍተኛ ሁኔታ ሲመታው ኢብሊስ በአንዴው የፀሀይ መውጫ ላይ ደረሰ።
ዳግም ሲመታው...ወደ ምዕራብ መጨረሻ አደረሰው።አሁንም ዳግም ክፉኛ ሲመታው በጭቃ እስኪላወስ ድረስ ሰባተኛ ባህር ውስጥ ዘፈቀው።
ከዚያም ይህ ቀልበ ደረቅ ከዛ ባህር ውስጥ በመውጣት ዒሳ ዘንድ ሄደ'ና፦"ወላሂ አንተ የመርየም ልጅ ባንተ ሰበብ የተሰቃየሁትን በማንም ሰበብ አልተሰቃየሁም" አለው።
በመጨረሻም የኢብሊሱ ተከታዮች፦"አለቃችን ሆይ!! ዛሬ በጣም ተሰቃየህ እኮ" አሉት።
ኢብሊሱም፦"አይ ይህ እንኳን የተጠበቀ ባሪያ ነው። እሱን ማጥመም ስለማይቻለኝ በሱ ሰበብ ግን ቁጥር ስፍር የሌለውን ህዝብ አጠማለሁ።እሱንም እናቱንም(መርየምን) ከአላህ ጋር አድርገው እንዲያመልኳቸው ሰዎችን እመራለሁ" አላቻው።
ዒሳ ላይ የሰዎች እና የሰይጣናት ፈተናዎች እጅጉን በዝቶበታል።አሁን የነገሩም መገባደጃ እየተቃረበ መጥቷል....።
ዒሳ አንድ ቀን ሀዋሪያቶቹን ሰብስቦ ለ30 ተከታታይ ቀናት እንዲፆሙ አዘዛቸው።ሀዋሪያቱም ሰላሳውን ቀናት ፁመው ካጠናቀቁ በኋላ ዒሳ ዘንድ በመምጣት፦"የመርየም ልጅ ሆይ!! ፆማችንን አጠናቅቀናል። ከሰማይ ማዕድ አውርድልን። አንደኛ እንበላለን...፣ሁለተኛ ፆማችንን አላህ እንደተቀበለን እናረጋግጣለን...፣ሶስተኛ ደግሞ 30 ቀን ለፆምነውም ዒድ ይሆነናል" አሉት።
ዒሳም ይህን ንግግራቸውን ሲሰማ ለአላህ ምስጋና በማሳነስ እንዳይጠፉ ሰግቶ መከራቸው...።እነሱም የሱን ምክር ወደ ጎን ትተው ማዕዱን አሁን ካላወረድክ ብለው ወጥረው ያዙት(አስቡት እስኪ ሙእሚኖቹ እንዲ ካደረጉት ካፊሮቹ እንዴት እንደሚያንገላቱት!!)
ይህን ግዜ ዒሳ ተስተካክሎ ቆመ አንገቱንም ወደ መሬት አቀርቅሮ ከአይኖቹ የክጃሎት እና የፍራቻ እንባ እያዘነበ እላህን ማዕድ እንዲያወርድ ለመነው።
አላህም፦"እኔ (ማእድዋን) በናንተ ላይ አውራጅዋ ነኝ፡፡ በኋላም ከእናንተ የሚክድ ሰው እኔ ከዓለማት አንድንም የማልቀጣውን ቅጣት እቀጣዋለሁ" አለ።
ከዚያም በኋላ በሁለት ዳመናዎች የተጫነ ማዕድ ከሰማይ በከፍተኛ እርጋታ መውረድ ጀመረ።ዒሳ ማዕዷ ወደ ምድር በተቃረበች ቁጥር፦"ያ አላህ የፀጋ ማዕድ እንጂ የመቅሰፍት ማዕድ አታድርግብን" እያለ ይደጋግም ነበር።
ከዚያም ቀስ በቀስ ማዕዱን የተሸከሙት ሁለቱ ዳመናዎች ወደ ምድር በመቃርብ በእርጋታ የተሸከሙትን ማዕድ በዒሳ ፊት ለፊት አስቀመጡት።
ዒሳም ብድግ ብሎ የማዕዱን ሽፋን፦"በአላህ ስም መልካም ለጋሽ በሆነው"

#የዒሳ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ_የመጨረሻዉ ክፍል

ኢንሽዓሏህ
ይ.....ቀ.......ጥ.......ላ......ል፡፡