Get Mystery Box with random crypto!

#ኢሳ_እየሱስ ዐለይሂ_ሰላም ያ ነብይ...የሚስክ ሽታ አይነትም ያውዳል...።ከሱ በፊትም | History of islamic

#ኢሳ_እየሱስ ዐለይሂ_ሰላም




ያ ነብይ...የሚስክ ሽታ አይነትም ያውዳል...።ከሱ በፊትም ሆነ ከሱ በኋላ እንደሱ አይነት ውብ አልታየም...(እህ!!!እባክህ እንባዬ ትንሽ ታገሰኝ።አይኔን አትጋርደኝ.. ፅሁፌን ልጨርስ)
ዒሳ ሆይ !!! የዛን ነብይ ሀላፊነት ውሰድ..።የእናትህን ሀላፊነት ዘከሪያ ወስዶ እንደተንከባከባት ሁላ...።
ዒሳ ሆይ!!! ያ ነብይ እኔ ዘንድ ለማንም ፍጥረት ካለው ቦታ በላይ ቦታ አለው። ንግግሩ ቁርአን ነው...። ሀይማኖቱም ኢስላም ነው...። እኔም ደግሞ (ሰላም) ነኝ።
የዚያን ነብይ ዘመን ደርሶ የኖረ ሰው ምንኛ ታደለ...!!!በዚያ ዘመንም ያን ነብይ ቀርሶ ንግግሩን የሰማ ሰውስ ምንኛ እድለኛ ነው ..!!!"
አላህ ይህን ካለው በኋላ ሙሀመድ ዐሰ በሱ ዘመን ከመጣ ሙሀመድን ዐሰ እንዲከተል ቃል አስገብቶ መፀሀፉን አወረደለት።

በዚህ በታዘዘው ሁኔታ ዒሳ አላህን በመተናነስ እየተገዛ የጌታውንም ተልዕኮ ማድረስ ጀመረ።ከእለታት አንድ ቀንም ዒሳ መንገድ ላይ ሳለ አንዲት ሴትዮ በአንድ ቀብር ተደፍታ ስትንሰቀሰቅ ተመለከታት።
ዒሳም ጠጋ ብሎ፦"አንች ሴት ምን ሆነሻል!?" ብሎ ጠየቃት።
ሴትዮዋም፦"አንዲት ብቸኛ ልጄ ሞታ ነው።ከሷ ሌላ ምንም ልጅ የለኝም...።እኔም ለጌታዬ እሷን ያቀመሳትን ሞት እስኪያቀምሰኝ ወይም ልጄን አንድ ግዜ ቀስቅሷት እስኪያሳያኝ ይህን ቦታ አልለቅም ብዬ ቃል ገብቻለሁ" አለችው።

ዒሳም፦"አንድ ግዜ ካ

የሻት ግን ይህን ቦታ ለቅቀሽ ትሄጃለሽን?" ብሎ ጠየቃት።
ሴትዮዋም፦"አዎን" አለች።
ዒሳም እዛው ቦታ ላይ ሁለት ረክዐ ሰግዶ ወደ ቀብሩ ጠጋ በማለት፦"አንች ኤኬሌ! በአላህ ትዕዛዝ ቁሚ" ብሎ ጠራት።
ያን ግዜ ቀብሩ ተንቀሳቀሰ። ሁለተኛም ሲጣራ ቀብሩ መከፈት ጀመረ...። ሶስተኛም ሲጣራ ከዒሳም እዛው ቦታ ላይ ሁለት ረክዐ ሰግዶ ወደ ቀብሩ ጠጋ በማለት፦"አንች ኤኬሌ! በአላህ ትዕዛዝ ቁሚ" ብሎ ጠራት።
ያን ግዜ ቀብሩ ተንቀሳቀሰ። ሁለተኛም ሲጣራ ቀብሩ መከፈት ጀመረ...። ሶስተኛም ሲጣራ ከፀጉሯ አፈር እየጠረገች ከቀብር ውስጥ ወጣች።
ዒሳም ከቀብር የወጠችውን ልጅ፦"ስጠራሽ ለምን ዘገየሽ?" ብሎ ሲጠይቃት።
እሷም፦"መጀመሪያ ስትጠራኝ አንድ መልዐክ መጣና ቆመብኝ...ሁለተኛ ስትጠራኝ ነፍሴ በገላዬ ገባችልኝ...። ሶስተኛ ስትጠራኝ ቂያማ የቆመ መስሎኝ ፀጉሬ ቅንድቤ ሀሉ ሸበተ" አለችው።
ከዚያም ልጅቱ ወደ እናቷ ዞራ፦" እናቴ ሆይ..!! ምነው የሞትን መራራ ፅዋ ሁለቴ እንድቀምስ ፈልገሽ ነው ወይ ያስቀሰቀሽኝ...!!! እናቴ ታገሺ የትዕግስትሽንም ምንዳ ከጌታሽ ጠብቂ...። እኔ አሁን ከዱንያ ጉዳይ የለኝም...።አንተ የመርየም ልጅ ሆይ!!! ጌታህ ወደ አኪራ እንዲመልሰኝ ጠይቀው። የሞትንም ጣር እንዳያቀምሰኝ..." አለች ዒሳም ዱዓ አድርጎ ወደነበረችበት የሙታን መንደር በአላህ ፍቃድ መልሶ ቀላቀላት።
ይህ ወሬ አይሁዳውያን ዘንድ ሲደርስ አይሁዳውያኑ እጅጉን ተቆጡ....እሱ ዘንድም ተሰብስበው ሊፈትኑት፦"የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሞት ቀስቅሰቅልን" አሉት........

ኢንሽአሏህ
ይ.......ቀ......ጥ.......ላ......ል፡፡



@historyofislam2
@historyofislam2