Get Mystery Box with random crypto!

#የነብያት_ታሪክ #ኢሳ_ዐለይሂ_ሰላም መርየምም የመውለጃ | History of islamic

#የነብያት_ታሪክ

#ኢሳ_ዐለይሂ_ሰላም






መርየምም የመውለጃ ሰዐቷ በተቃረበ ግዜ የቤተ አምልኮውን ግቢ ለቃ ወጣች።ብቻዋን #በረሀ ላይ ሳለች ምጡ ጀመራት በጣምም አመማት አሁን ያለችበትን እንግልት እና ከመውለዷ በኋላ የሚከተላትን እንግልት ስታስብ፦"ዋ! ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ" ብላ ተመኘች።
በመጨረሻም ወደ አንድ የደረቀ #የተምር_ዛፍ ዘንድ በመጠጋት ልጇን ዒሳን ተገላገለች።ልክ ልጁን እንደተገላገለች ጂብሪል መጣ'ና፦" አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡
የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም" አላት።
በልታ ስታበቃም ጂብሪል፦"ማንም ሰው ሊያናግርሽ ቢፈልግ እኔ ለአር ረህማን(ለአላህ) ማንንም ሰው ላላናግር ፆሚያለሁ በይ" አላት።
ኢብሊስም መርየም ልጇን ከተገላገለች በኋላ ወደ ኢስራኢላውያኑ ካህናት በመሄድ የመርየምን መውለድ ነገራቸው።ካህናቱም በጣም በመቆጣት ይዝቱባትም ጀመሩ።
ከዚያም መርየም ልጇን ተሸክማ ወደ ቤተ አምልኮው መጣች። ሁሉም ተሰብስቧል....ገና ፊትለፊታቸው ብቅ ስትል፦"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም" አሏት።(የሀሩን እህት ያሏት ሳሊህ ሰዎችን በሀሩን ስለሚመስሉ ነው።)
እሷም ምንም መልስ ሳትሰጥ ህፃኑን እንዲያናግሩ ወደ ልጇ አመላከተቻቸው።ሁሉም በሁኔታዋ በመገረም ዚና ያደረገችው እንሷት እኛ ላይ ታሾፋለች እንዴ እያሉ ከተነጋገሩ በኋላ፦"በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን" አሏት።
ያን ግዜ ህፃኑ ዒሳ ቀና በማለት፦"እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል።
በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል፡፡
ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም።
ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን" ብሎ ተናገረ።
ይህን የህፃኑን ንግግር በሰሙ ግዜ ሊወግሯት ተሸክመው የመጡትን ድንጋይ ይዘው ተመለሱ።
የአላህ ፍቃድ ሆኖ #ዒሳ አድጎ ከህፃናት ጋር በመንገድ ላይም ለመጫወት በቃ።
ከእለታት አንድ ቀን ዒሳ ከአከባቢው እኮዮቹ ጋር በመጫወት ላይ ሳለ አንድ ህፃን ሌላኛውን ህፃን በእግሩ ገፍትሮ ሲጥለው ህፃኑም የዒሳ እግር ስር ወድቆ ሞተ።
ሰዉ ሲሰበሰብ ሟች ህፃኑን በዒሳ እግር ስር ወድቆ ተመለከቱ።
የህፃኑ ገዳይ ዒሳ ነው በማለትም ዒሳን በጨቅላ እድሜው ለፍርድ አቀረቡት።
ዳኛውም፦"ህፃኑን ገድለሀልን?" ብሎ ሲጠይቀው
#ዒሳም፦"አልገደኩትም" አላቸው።ከዚያም ዒሳን ለቅጣት ዚያዘጋጁት ዒሳም ለዳኛው፦"እሺ የሞተውን ህፃን አምጡልኝ" አለ።
ዳኛውም በዒሳ ሁኔያ በመገረም የህፃኑ አስክሬን እንዲቀርብ አዘዘ'ና #ዒሳ ፊትለፊት ላይ ቀረበለት።
ዒሳም ዱዓ ሲያደርግ አስክሬኑ በአላህ ፍቃድ ህያው ሆነ።ከዚያም አስክሬኑን፦"ማን ገድሎህ ነው?" ብለው ሲጠይቁት፦"ኤኬሌ...ነው" ብሎ የገዳዩን ልጅ ስም ጠራላቸው።
#ዳኞቹም፦"የዚህስ ልጅ ስሙ ማን ይባላል" ሲሉት፦"ዒሳ" ብሎ መለሰላቸው።
አስክሬኑም ........


ለወዳጅ ዘመድዎ ሸር ያድርጉ


ኢንሻአላህ ይቀጥላል

@historyofislam2
@historyofislam2