Get Mystery Box with random crypto!

Repost ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተ | ☘ሒራ የቱርክ ምንጣፎች ትራስ ልብስ መሸጫ☘

Repost

ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ
ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር

አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ
ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።
በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም
ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ
" ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው
ቦርሳ 'ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው ማንዴላም"ገንዘቡን እወስደዋለሁ" …ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል
አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት
ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ

"ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል"
ብሎት እርፍ ፡፡ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ