Get Mystery Box with random crypto!

ነቢዮ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ። ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ። ሲወጡ የሱን ነገር | ☘ሒራ የቱርክ ምንጣፎች ትራስ ልብስ መሸጫ☘

ነቢዮ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ።
ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ።
ሲወጡ የሱን ነገር ለአለቃቸው እንዲነግሩለት አደራ አላቸው።
እነርሱ ግን ረሱት።
ሓጃዉን ከነርሱ ይልቅ ለአምላካቸው መናገር የነበረባቸው ዩሱፍም ለዓመታት በእስር ቤት በሰበሱ።
ቀድመዋቸው ከወጡት አንደኛው አገልጋይ ሆነ።
ሁለተኛው በስቅላት ተገደለ።
ዘግይተው የወጡት ዩሱፍ ግን ከግብጽ ሚኒስቴሮች አንዱ ሆኑ።
እናሳ
እናማ
ያንተ/ያንች ፋይል አልተረሳም።
ጌታህም ረሺ አይደለም።
ጉዳይህ የዘገየው ለምክንያት ሊሆን ይችላል።
በደንብ አብስሎ ሊሰጥህ ይሆናል።
እስቲ አትቸኩል ንጉሥ ትሆን ይሆናል።
ሚኒስቴር ትሆን ይሆናል።
ይቅናህ አቦ ..

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል