Get Mystery Box with random crypto!

በምስማር ቸነከሩህ፤ አንተ ግን ይህንን ለድኅነታቸው አደረግህ። በጦር ጎንህን ወጉት፤ ለኃጢአታቸው | Hilina Belete

በምስማር ቸነከሩህ፤ አንተ ግን ይህንን ለድኅነታቸው አደረግህ። በጦር ጎንህን ወጉት፤ ለኃጢአታቸው መታጠቢያ ይሆናቸው ዘንድ ወዲያውም ውኃ ወጣ። በመደነቅ ይቆሙ ዘንድ ከደምህም ንጹሕ እንዲሆኑ ይታጠቡ ዘንድ ወዲያው ውኃና ደም ከጎንህ ወጣ። አራጆቹ ይታጠቡ ዘንድ÷ ሕይወትንም ያገኙ ዘንድ የታረደው እርሱ ከደሙ ውኃን አቀረበ።

(ቅዱስ ኤፍሬም እንዳስተማረን÷ እንደተረጎምሁት)

ኦ መድኃኒት ሆይ ማረን!

እንኳን አደረሰን!