Get Mystery Box with random crypto!

ዐርፈዋል ይላሉ - ያልተረዱ ሁሉ፣ በዚህ ዓለም ወሬ - መች ኖረው ያውቃሉ? ሞተዋል ይላሉ - ሳያ | Hilina Belete

ዐርፈዋል ይላሉ - ያልተረዱ ሁሉ፣
በዚህ ዓለም ወሬ - መች ኖረው ያውቃሉ?

ሞተዋል ይላሉ - ሳያወሩ ቢያዩ፣
ዓለምን ትተዋት - ዝምስ ካሉ ቆዩ።

ጠፋን ተጠፋፋን - እየለፈፍንና - እየለፈለፍነው፣
ግና ብናውቅበት - አፍ የተፈጠረው - ዝምም ለማለት ነው።

ጽድቅና ኩነኔ ቢያዝ ባይያዝም፣
ከክፉ ንግግር ይሻላል ማለት ዝም።

የማይጠቅም ወሬን - ሰርክ ከማቀበል፣
ከአባታችን ጋር - አብረን ዝም እንበል።

መርቆርዮስ የሚል - ሁለት ስም አውቃለሁ፣
አንደኛው አንገቱን
አንዱም አንደበቱን - ሰጥተዋል እላለሁ።

እንደምን ኃያል ነው - መርቆርዮስ 'ሚል ስም፣
ሰማዕት ያደርጋል - ባንገትም በአፍም።

ዝምታ ወርቅ ነው - ሲሉ ሰምቻለሁ፣
ጽድቅ መሆኑን ግን - በዐይኔ አሁን አየሁ።

ስንት ታሪክ እያለ - ካፋቸው ሚደመጥ፣
ዝም ብለው ዐረፉ - ለሊቅ ለደቂቁ - ቃል እንዳይጎረብጥ።

ስንት እውነት እያለ - ካፋቸው 'ሚለቀም፣
ስለሚልቀው ሐቅ - ጻድቁ አፋቸው - ከቶ አልተላቀቀም።

እውነታችን አልቆ
ተንጠፍጥፎ በንኖ - ለማውራት ስንቸኩል፣
እውነትን ሰንቆ
ዝም ያለ አንደበት - አለ በዚህ በኩል።

መርቆሪ መርቆሪ - ብለን ብንጣራ - 'አቤት'ህ ዝም ነው፣
ለነባቢ አፋችን - የዝምታህ ጸጋ - ረድኤት ይሁነው።