Get Mystery Box with random crypto!

የሰረቅኩት..! ከቤት በጠዋት ነበር የወጣሁት 2 ሰዓት ላይ ለህክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ እንዳላረፍ | HAppy Mûslim

የሰረቅኩት..!

ከቤት በጠዋት ነበር የወጣሁት 2 ሰዓት ላይ ለህክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ እንዳላረፍድ በማሰብ ነበር በጠዋት የወጣሁት ከቀጠሮዬ ቦታ ከሰዓቱ ቀድሜ 1:40 ላይ ደረስኩ :: እዛው ቆይቼ በሰዓቴ ህክምናዬን ካከናወንኩ በኋላ በዚሁ ለምን መንጃ ፈቃድ አላድስም ብዬ ወደ መንገድ ትራንስፖርት አመራሁ እዛ እንደደረስኩ ወረፋ ስለነበረው ወረፋ እየጠበቅኩ ስልኬን ፍለጋ ወደኪሴ ስገባ ስልኬን አጣሁት ።

ስልክ ድንገት ከኪስ ሲጠፋ ስሜቱን ታውቁታላችሁ መቼም ። የት እንደጣልኩት ማሰብ ጀመርኩ ከሆስፒታሉ ስወጣ ሰዓት ለማየት ኬሴ ውስጥ እንዳወጣሁት አስታወስኩ ስለዚህ ታክሲ ውስጥ ሻሻ እንደሰሩኝ ገባኝ ። ቀድሞ አዕምሮዬ ላይ የመጣው እና የቆጨኝ ነገር ሃይደርን ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ማስታወሻ ይሆናሉ ብዬ በየቀኑ የማነሳው ፎቶዎች መጥፋት ነበር ። በጣም የምወዳቸው ፎቶዎች ነበሩ ።

ወረፋዬን ጠብቄ መንጃ ፈቃዴን አድሼ ከመንገድ ትራንስፖርት ወጣሁ :: የሚገርመው ነገር የተፈጠረው የዛኔ ነው የሆነ ህፃን ልጅ ስልኩን እና የሆነ ወረቀት ሰጠኝ ስልኩን ሳየው የራሴ ስልክ ነው ። ከዛ ወረቀቱን ስከፍተው ስልኩን ለመስረቅ የተገደድኩት ልጄ ስለታመመብኝ ለአስቸኳይ ህክምና እና ለወተት ብር ስላስፈለገኝ ነበር ግን Wallpaper ላይ ካደረከው የልጅህ ፎቶ ላይ የፃፍከውን ፅሁፍ ሳየው የሆነ ስሜት ፈጠረብኝ እና ስልኩን መመለስ እንዳለብኝ ተሰማኝ ልጅ) ስላለህ ትረዳኛለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ በጣም ይቅርታ ልታግዘኝ ከፈለክ ግን በዚህ ስልክ ቁጥር ታገኘኛለህ ተብሎ ቁጥሩ ተፅፎበታል ።

በጣም አሳዘነኝ ምን አልባት እኔ በሱ ቦታ ብሆን ልጄ ቢታመምብኝ ለልጄ ቅድሚያ በመስጠት ስልኩን ሁሉ የምመልስለት አይመስለኝም ነበር ። በተፃፈው ቁጥር ደወልኩለት አነሳው ሰላም ካልኩት በኋላ ባለስልኩ መሆኔን ነገሬው እጄ ላይ ብር የለም ወተት የምትፈልግ ከሆነ ግን እቤት አለ ልላክልህ አልኩት እሺ አለኝ ስልኩን እና ወረቀቱን የሰጠኝ ልጅ አብሮኝ እንዲሄድ ነገረው ወደ ቤት እየሄድን አብሮኝ ከነበረው ልጅ ጋር ብዙ ነገሮችን አወራን ልጁ የምሩንም እንደሆነ ተረዳሁ ።

አሳዘነኝ ብችል እና እጄ ላይ ገንዘብ ቢኖረኝ ልጁን ባሳከምኩለት ግን ብር አልነበረኝም ። ቤት | እንደደረስን ለሃይደር የገዛሁት ግን አሁን ሃይደር እዚህ ስለሌለ የተቀመጡ 3 የቆርቆሮ ወተቶች ነበሩ እነሱን አብሮኝ ለመጣው ልጅ ሰጠሁለት እና ሄደ ። ቆይቶም ወተቶቹ እንደደረሱት ለሰራው ነገር ይቅርታ ጠይቆ እንደሚያመሰግነኝም ነግሮኝ እኔም አይዞህ ይሻለዋል ብዬው ስልኩን ዘጋሁት ።

ከመስረቁ በላይ ለልጄ ፍቅር Wallpaper ላይ በፃፍኩት ፅሁፍ ሀሳቡን ቀይሮ ስልኩን መመለሱ አስገረመኝ የልጅን ፍቅር ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነው ። ማጣት ከምንም በላይ የሚያመው ለልጅህ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት አቅም ሲያንስ ነው :: ስትወልድ የምትኖረው ለልጅህ ነው ለራስህ ማሰብ ታቆማለህ አባትነት ስሜቱ ጥልቅ ነው ለልጅህ ስትል የማይሆን ነገር ውስጥም ትገባለህ። አላህዬ ልለምንህ ማንም አባት ለልጁ ሲል አይቸግረው!! ልጁንም አላህ አፊያ ያድርግለት

@heppymuslim29