Get Mystery Box with random crypto!

☞በድሮ ግዜ አንድ ሰውየ ሱቢህ ሶላት ለመስገድ በለሊት ወደ መስጅድ በሚሄድበት ሰአት በሰአቱ ዝናብ | HAppy Mûslim

☞በድሮ ግዜ አንድ ሰውየ ሱቢህ ሶላት ለመስገድ በለሊት ወደ መስጅድ በሚሄድበት ሰአት በሰአቱ ዝናብ ጥሎ ስለነበር ከሆነ ቦታ ላይ መሬቱ ያዳልጠውና ይወድቃል ።

ከዛም ጀላብያው በጭቃ ሲበከልበት እንዲህ_አለ "ዛሬማ የሱቢህን ሶላት የግድ በጀማዐ መስገድ አለብኝ አለና ወደ ቤቱ ልብስ ለመቀየር ሄደ።

እንደገና ልብስ ቀይሮ ሲመለስ መጀመሪያ ከወደቀበት ቦታ ላይ ሁለተኛ ወደቀና የለበሰው ጀላብያ በጭቃ ተበከለ።የሚገርመው ግን ይሄ ሰውየ ተስፍ አልቆረጠም ነበር ይልቁንስ የሱቢህ ጀማዐ ሶላት አያመልጠኝም አለና ወደ ቤቱ ልብስ ለመቀየር ተመለሰ።

አሁንም ሶስተኛ ግዜ ልብሱን ቀይሮ ወደ መስጅድ በሚሄድበት ሰአት ሁለት ግዜ ከወደቀበት ቦታ ላይ ለሶስተኛ ግዜ ሊወድቅ ሲል ምን ቢከሰት ጥሩ ነው አጅሬ ሸይጧን በሰው ተመስሎ ይመጣና ደገፍ አድርጎ ያሳልፈዋል።

ከዛም ይሄ ሰው ተገረመና አንተ ማነህ ብሎ ጠየቀው?  ሸይጧን ነኝ አለናም መለሰለት።

ከዛም ይሄ ሰው እንዲህ አለው "ሸይጧን ከመቼ ወዲህ ነው ለሰው ኸይር የሚሰራው"አለው?

ሸይጧንም እንዲህ አለው"እኔ ላንተ አስቤ አይደለም ግን መጀመሪያ ስትወድቅ አሏህ ያንተን ወንጀል ሲምርልህ አየሁ ሁለተኛ ስትወድቅ ደግሞ አሏህ የቤተሰብህን ወንጀል ሲምርላች አየሁ ሶስተኛ ብትወድቅ የ ሰፈሩ ሙስሊም ሰዎች ወንጀላቸውን አሏህ ስለሚምራቸው ከሚማሩማ ደግፊ ላሳልፍህ ብየ ነው አለው።

አሏህ ከሸይጣን ተንኮል ይጠብቀን
@heppymuslim29