Get Mystery Box with random crypto!

በገሞራው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ የግል ህይዎትና በሙዚቃ ስራዎች የትግል ህይወቱ ዙሪያ 'SP | Heni Z Man (Qoricha Buda)

በገሞራው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ የግል ህይዎትና በሙዚቃ ስራዎች የትግል ህይወቱ ዙሪያ "SPEAR THROUGH THE HEART " የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በ Bruno Sorrentino ተዘጋጅቶ በUS , Minneapolis 28 በAugust 28, 2022, from 5:00 PM - 10:00 PM ለይታ ይቀርባል። ይህ ታሪካዊ ዘጋቢ ፊልም በተለያዬ ሃገሮች የአሜሪካ ከተሞች እና በሃገር ቤት ለሚሊዩን ታዳሚዎች ወይም ተመልካቾች ለእይታ ይቀርባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። በMinneapolis ያላችሁ ግን በ Fridley Public School Auditorium , 6000 W Moore Lake Dr NE , Fridley , MN 55432 በAugust 28, 2022, from 5:00 PM - 10:00 ባለው ሰዓት በመገኘት መመልከት ትችላላችሁ ።

ሃጨ በሚሊዩኖች ውስጥ ያለ ሲሆን ፣ በነገው በርካታ ሚሊዩን ኦሮሙማ ትውልድ ህያው ሁኖ የሚኖር አንድ የታሪክ ክስተት ነው። ገሞራው ሃጨን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከእስልምና ክርስትና ዋቄፈና ኤቲስት የሆነ ሁሉንም በእኩል የሚወድ በእነሱ የሚወደድ ነው። ስለዚህ ገሞራው ሃጨ በስጋ እንጅ በመንፈስ መቸም የትም አይለየንም ገሞራው ሃጨ ትናንት ዛሬም ነገም በኦሮሙማ ታሪክ ዘላለም ህያው ነው።
ባላምባራስ ነጋሽ Negash Qemant