Get Mystery Box with random crypto!

በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ምዕመናን ጾመ ነነዌን ጥቁር ልብስ በመልበ | Hello Ethiopia🇪🇹

በመላው ዓለም የሚገኙ የኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ምዕመናን ጾመ ነነዌን ጥቁር ልብስ በመልበስ የጸሎት መርሐ ግብሮችን እየተካፈሉ ነዉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ ከትናንት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየ አብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንዲመሩ እና እንዲከታተሉ ወስኖ ነበር።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ምእመኑ ጾመ ነነዌን ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሮች በመገኘት ጸሎት እያደረገ ይገኛል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ከትናንት ጀምሮ ጠዋት ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ ማታ የቤተሰብ ጸሎት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ "ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን" አስታውቆ ነበር።
ፎቶዎቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን አዲስ አበባ ውስጥ በ ሲ ኤም ሲ ሚካኤል ፣ በቅድስት ሰዓሊተ ምህረት እና በቅዱስ እስቲፋኖስ አብያተ ክርስትያናት በፀሎት ሲሳተፉ የሚያሳዩ ናቸው። https://t.me/helloethiopian