ያፈቀረ አይርሳ ;;;;;;;;; አይረሳኝም ብለሽ አይተወኝም ብለሽ አውርተሻል አሉ ፣ ጉድ እስኪል ከተማው ምን ነካው እያሉ ፣ ያፈቅረኛል ብለሽ ይወደኛል ብለሽ ተናግረሻል አሉ ፣ ሲጠቋቆምብኝ ሀገሬው በሙሉ ። ወደደኝ ስትይ መንገር አላፈርሽም ፣ ኮራሁበት ስትይ አንገት አልደፋሽም ፣ በሀሜትሽ ጅራፍ ብትገርፊኝ ስድሳ ፣ የማፍቀር መንፈሴ ከላዬ ተነሳ ። እንድጠላሽ ምሴ እንድረሳሽ ዋሴ ፣ ወደድካት ባሉኝ ልክ የሳቀልሽ ጥርሴ ፣ ተኝቼ ስነቃ ከአልጋዬ ስወጣ ፣ ቃዠሁኝ መሰለኝ ፍቅርሽ በላብ ወጣ ። እኔ አላውቅልሽም አበዛሁ መሰለኝ ማር በዝቶ ላይጥመኝ ፣ አንቺን ማሰላሰል እንዲሁ ላይጠቅመኝ ፣ መዋሌ ማደሬ ከማፍቀርሽ ጥላ ፣ ምክንያት ሆነኝ ብልሽ አንቺን እንድጠላ ። እስኪ አሁን ለፍፊ አፍቃሪ የዋህ ነው ችሎ ቢታገስም ፣ ውስጡ ከቆረጠ ሀሳብ አይከልስም ፣ መገፋት በሙሉ አይጥልም ከገደል ፣ ከ ልብ ያስለቅቃል አፍቃሪን መበደል ፣ ፊት እንደጎረርሺው በይ አሁን ጎርሪ ፣ ወጥቼለታለሁ ጠላኝ ብለሽ አውሪ ። [ በረከት ዘውዱ ] @Helenitaaaaaaaa 53 viewsedited 04:06