Get Mystery Box with random crypto!

ሕግ እና ሕይወት

የቴሌግራም ቻናል አርማ hegenaheywet — ሕግ እና ሕይወት
የቴሌግራም ቻናል አርማ hegenaheywet — ሕግ እና ሕይወት
የሰርጥ አድራሻ: @hegenaheywet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 376
የሰርጥ መግለጫ

ሕግን ቀለል ባለ መንገድ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-17 23:31:17
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤት ስም ማዞሪያ ታሪፍ ላይ ያደረገው ማሻሻያ።
362 views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 19:29:36 ሸሪዓ እና ተጨባጩ እውነታ በሂክማ በድሩ መልካት ንባብ
709 viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 16:20:14 ጥያቄዎች በዚህ ግሩፕ ነው የሚደርሱን https://t.me/hegenahywet/2884
669 views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 16:14:50 መብቶችን በተመለከተም ብዛት ያለው ዘርፍ ያለው ሲሆን ለምሳሌ የሰብአዊ መብት የሰራተኛ መብት ወዘተ ያካትታል።
ጥያቄዎ መሰረተዊ የሰዎች መብቶች ጋር የተያያዘ መሆኑን በማመን የሰብአዊ መብቶች አለም አቀፍ ድንጋጌ የአማርኛ ትርጉም ያያዝን ስለሆነ እንዲያነቡ እንጋብዛለን።
587 viewsedited  13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:24:36 የሕግ የበላይነት ሰፊ ጽንሰ ሀሳብ ከመሆኑ አኳያ ጠያቂያችን እና ሌሎች ፍላጎቱ ያላቸው በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይህንን ሰነድ ማጋራቱ የተሻለንመሆኑን ስላመንን እንድታነቡት እንጋብዛለን።
473 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:28:55


488 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 19:28:24 ሰላም !
አንዲት ሙስሊም ሴት በፌደራል ፍርድ ቤት ባለቤቷ ፍቺውን እየተቃወመ የፍቺ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን ይህ ፍቺ በሸሪአ ሕጉ መሰረት እንዴት ይታያል?
ይህች ሴት በድጋሚ በሸሪአ ፍርድ ቤት ፍቺ በድጋሚ ብትጠይቅ በድጋሚ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ /res judicata/ ይሆንባት ይሆን?

በእርግጥ ይህ ጥያቄ የሸሪዐ ፈትዋ ጥያቄ ያዘለ በመሆኑ ለሀይማኖቱ ልሂቃን-ኡለሞች መቅረብ ያለበትጥያቄ ነው ።

በግልጽ እንደሚታወቀው በሸሪአ ህግ ፍቺ እራሱን የቻለ ሕግ እና ስርዐት አለው። በሸሪዐ ሕግ ፍቺን የመፈጸም ስልጣን as a rule ለወንድ የተሰጠ ሲሆን በተለየ ሁኔታ exception ሴቶች በጋብቻው መብታቸው በማይከበርበት ሁኔታ ወይም ኹልዕ በተባለ ስርአት ፍቺ ለመፈጸም ለቃዲ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።

በፌደራል ፍርድ ቤት የፈረሰን ጋብቻ በተመለከት የሽሪዐ ሕግን ሥርዐት አሟልቶ ጋብቻው ፈርሷል እንደማይባል የሀይማኖቱ ልሂቃን ሀሳብ ይሰጣሉ።

Resjudicata /ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ በድጋሚ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄን/ በተመለከተ በፍ/ሥ/ ሕግ ቁጥር 5 በተቀመጠው ፍርድ በተሰጠበት ጉዳይ ላይ በድጋሚ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ በቀጥታ ከሕጉ አንጻር ካየነው በድጋሚ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ሊያስብል ይችላል። በኢፌድሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በተሰጠ ውሳኔ መሰረት አንድ ጉዳይ በድጋሚ የቀረበ ነው የሚባለው ፍሬ ነገሩ ወይም ተከራካሪዎቹ ተመሳሳይ ከሆኑ እንደሆነ ውሳኔ ሰጥቷል።
የሸሪዐ ፍርድ ቤቶች ጉዳዮችን የሚያሳልጡበት እና ሥነስርዐት የሚያስኬዱበት ሕግ የፍ/ሥ/ሕግ በመሆኑ ጉዳዩ በድጋሚ የቀረበ ነው ሊባል የሚችልበት እድል ሰፊ ነው።

የሸሪዐ ፍርድ ቤቶች ፍርድ የሚሰጡበት መሠረታዊ ሕግ ቁርአን እና ሀዲስ ከፍታብሄር ከሥነሥር ሕግ ጋር የሚጋጩ ቢሆን እንዴት ዳኝነት መስጠት አለባቸው የሚለው ገና የሕግ መፍትሄ ያላገኘ የምርምር ርዕሰ ጉዳይ ነው። ለምሳሌ በሸሪዐሕግ መብት በተለይም የወራሽ መብት በጊዜ ገደብ የማይደረግበት ሲሆን በሽሪዐ ፍርድ ቤቶች የውርስ ጥያቄ በሚቀርብበት ጊዜ የሥነሥርዐት ሕግን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ ሲቀርብ እያስተዋልን ነው።

በተመሳሳይ በእህታችን የቀረበው ጥያቄ ጥናት እና ምርምር ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ ነው። እንደኛ እምነት ጉዳዩ ራስን ነጻ ማድረግ /innocence برائت ذمه/ መርህ ጉዳዩ ለሸሪዐ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት። ሸሪዐ ፍርድ ቤት በድርሚ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ነው በሚል ውሳኔ ቢሰጥበት እንኳን ተቋማዊ ባልሆነ መልኩ ጥያቄው ለግለሰብ ቃዲ ቀርቦ ያሸሪዐ ፍቺውን ለማግኘት ጥረት ማድረጉ አስፈላጊ ነው።

በዚህ መልስ ላይ በሸሪዐ ጉዳይ የቀረበው ምላሽ የመጨረሻ ተብሎ ሊያዝ የማይገባው በምሆኑ በጉዳዩ ላይ ፈትዋ መስጠት የሚችሉ አሊም ለሚጠይቅ በኢንቦክስ ስልክ ለመላክ እንችላለን።

ለጥያቄው እናመሰግናለን።
411 viewsedited  16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 17:52:24 የታክስ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ አዲስ የወጣ መመሪያ
317 viewsedited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 13:40:41 የፌዴራል ጠበቆች ምዝገባ - መራዘሙን ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር በአባልነት ላቀፋቸው ጠበቆች አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነት እና ግዴታውን ለመወጣት ይችል ዘንድ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ

1. በድህረ-ገጽ በኦንላይን በዚህ አድራሻ http://t.ly/RzWs ወይም
2. በፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ወይም በአራዳ ምድብ ችሎት በሚገኘው የማኀበሩ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት
እንድትመዘገቡ መጠየቁ ይታወሳል።

በዚህ መሠረት በርካታ ጠበቆች በኦንላይን እና በአካል በመገኘት ምዝገባቸውን አከናውነዋል።

ምዝገባው እንዲከናወን የታሰበበት ጊዜ የበዓል ቀናት የተበራከቱበት መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለመመዝገብ ያልቻሉ ጠበቆች ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ማኅበሩ አምኗል።

በዚህ መሠረት ያልተመዘገባችሁ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች በሙሉ የምዝገባ ጊዜው

ከሰኞ ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ማኅበሩ ያሳስባል።

በኦንላይን ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ http://t.ly/RzWs

በአካል ተገኝተው ለመመዝገብ፦
1. የጥብቅና ደብተርዎን መያዝዎን አይዘንጉ፤
2. የጥብቅና ደብተርዎን የፊት ገጽ እና ፈቃድዎ የታደሰበትን የሚያሳየውን ክፍል ኮፒ አድርገው መያዝዎን አይዘንጉ
3. ለማኅበሩ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ መያዝዎን አይዘንጉ፤
4. የግብር መለያ ቁጥር መያዝዎን አይርሱ፤

የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር
332 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 20:46:06 ወአለይኩም ሰላም
እኛም መልካም ኢድ እንመኝሎታለን!
ላቀረቡልን ጥያቄ ከታች ምላሽ አቅርበናል።

"አሰላሙ ዓለይኩም !
በቅድሚያ ዒድ ሙባረክ!
አንድ ነገር መጠየቅ ፈልጌ ነበር! በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የሚፈጠር የስራ ክርክር ማመልከቻ የሚቀርበው ለማን ነው?
ይዘቱስ ምን መምሠል አለበት?
በደንብ ቢብራራ!"


በአሰሪ እና ሰራተኛ መሀከል የሚኖር ቅሬታ ላይ በቅድሚያ በየ ክፍለ ከተማው ለሚገኙ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ቢሮ አስማሚዎች ሊቀርብ እና ሰራተኛውን እና አሰሪውን ጠርተው ቅሬታ እና መልሱን ሰምተው ሊያስማሙ ይችላሉ።
ካልተስማሙ ግን ቅሬታውን በፌደራ ከሆነ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይቻላል።

የአቤቱታውን ዝርዝር በተመለከተ ቅሬታ ያለው ሰራተኛው ከሆን እና የአሰሪ እና የሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሠረት በማድረግ የተጣሰ መብት ካለ ጥሰቱ እንዲቆም፤ ለምሳሌ በሕገወጥ መንገድ ከሥራ መሰናበት ከሆነ ወደ ሥራ ለመመለስ ወይም ካሳ እንዲከፈል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል።

ጠያቂያችን የአሰሪና ሰራተኛ ሕግን ማጣቀስ እንዲችሉ ከዚህ በፊት በቻናላችን የለጠፍነውን የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በድጋሚ አያዘናል።

ተጨማሪ ጥያቄ ካሎት ወይም ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር የተገናኘ በተለይ የሚጠይቁት specific ጥያቄ ካሎት ለሌሌችም ትምህርት ሊሆን ስለሚችል ከመጠየቅ ወደ ዃላ አይበሉ።
ለተሳትፎዎ እናመሰግናለን!!
332 viewsedited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ