Get Mystery Box with random crypto!

#ተራዊሕ #በመስገድ ከሚገኙ #ጥቅሞች ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተና | ﷽ህብረ - ሙስሊም 2⃣﷽

#ተራዊሕ #በመስገድ ከሚገኙ #ጥቅሞች

ተራዊሕ የረመዷን ወር ምሽቶች ላይ በጋራም ይሁን በተናጠል የሚሰገድ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦቻቸው ያደረጉት "ሱና" ነው

በርካታ ጠቀሜታዎችና ምንዳዎችም አሉት
ከነዚህም በጥቂቱ:

① ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን

② ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን

③ ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን

④ ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን

⑤ ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን

⑥ ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን

⑦ በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "ኣሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል

⑧ መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል

⑨ ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል

①∅ የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን

①① ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል

①② ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን

①③ ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን

①④ ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን

①⑤ በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "ኣሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን

①⑥ ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን

①⑦ የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም

①⑧ ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታ እናገኛለን

ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊሕን አንተው!
አላህ ያግራልን

اللهم أعز الإسلام والمسلمين وأذل الشرك والمشركين ووحد صفوفنا وقنا شرور أنفسا يارب العالمي


https://t.me/hebre_muslim