Get Mystery Box with random crypto!

1) ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለፅነው ምክንያት ብንዘገይም በየትኛውም የዝውውር አመት ተዛውሮ የማ | Health info & vacancy news (HIVN)

1) ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በገለፅነው ምክንያት ብንዘገይም በየትኛውም የዝውውር አመት ተዛውሮ የማያውቅ በቁጥር ከፍ ያለ 1800 ባለሙያዎች ከቅሬታ በፊት ተዘዋውረዋል ።

2) ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ዛሬ ፎ-15 ተፈቅዶልን ይኸው የተፈቀደውን ፎ-15 ጭምር አያይዘናል።

3) ዞኖች የባለሙያው ጥያቄ እንዲመለስ በመፈለግ ያሳያችሁትን ትግስት እያመሰገን በዝውውር የሚመጡትንም ሆነ  የሚገቡትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንድታስተናግዱልን አደራ ማለት እንፈልጋለን

4) የቅሬታ ጊዜው በቴሌግራም ኦንላይን ስለሆነ እና ቀኑ እናዳይራዘም በሚል ዕረቡ ከሰዓት የመጨረሻ ውጤት ስናሳውቅ የተዘዋወራቹህት በፍጥነት ወደተዛወራቹህት ተቋም በመሔድ ሪፖረት ማድረግ ነገር ግን ዘግይቶ ለሚሔድ ኃላፊነት ራሱ ይወስዳል።

5) የተዘዋወሩትን ማስቀረት አይቻልም

6) በጊዜያዊ የተመደቡትን እስከ ቀጣይ ሐሙስ ቋሚ ምደባ በዝውውር ኮሚቴው ምደባ የሚሠጥ ይሆናል
7) እንደአምናው ሁሉ በዚህ አመትም ሁሉንም የህክምና ማስረጃ ያጣራን ሲሆን 19 ፎረጅድ አግኝተናል። ከውድድር ውጭ ያደረግን ሲሆን ቀጣይ ክስ የሚመሠረት ይሆናል።
8) ረጅም ዓመታት ያገለገሉ ባለሙያዎች ባሉበት በቋሚነት ከተመደቡ 5ወር የሆነን እያለን ሌላ ባለሙያ ሊዛወርበት አይገባም እኛ ባለንበት መመደብ አለብን በሚል የቢሮውን መልካም ስራዎች የምታጠለሹ አካላት ተገቢ አለመሆኑን አውቃቹህ ተጠያቂ የምናደረግ መሆኑን እንገልፃለን።

አማራ ክልል ጤና ቢሮ @healthinovation