Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ የቀ | Health info & vacancy news (HIVN)

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን፤ ሪፖርቱን ተከትሎም ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ከምክር ቤቱ አባላት እንዲሁም ከህብረተሰቡ የተሰበሰቡት ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴው በኩል ቀርበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ለሚኒስቴር መስርያ ቤቱ የቀረቡት ጥያቄዎችም ጭብጥ የሚከተሉት ናቸው፦

- በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ በመገንባትና በማቋቋምን በተመለከተ
- የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እና የህክምና ግብዓቶችና የአምቡላንስ ችግር
- የመሰረተ-ልማት ባለመሟላቱ በጤና አገልግሎት ላይ የሚደርሱ እንግልቶች

- የህክምና ተቋማትን ደረጃ ማሻሻል
- የህክምና አሰጣጥ ጥራትና ተደራሽነት
- ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የጤና ተቋማት
- በአንዳንድ የጤና ተቋማት የጤና ባለሙያዎች እጥረት
- የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያ

- የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ ለማደስ የሚገጥማቸው ችግር
- የጤና ባለሙያዎች ዝውውር ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች
- የጤና ኤክስቴንሽን አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን

- የጤና ባለሙያዎች ጥቅማጥቅም አለመፈጸሙ
- የጤና መድህን ተደራሽነት አለመሟላቱ
- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የወባ ወረርሽኝ እየተባባሰ ስለመምጣቱ ከምክር ቤቱ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች ናቸው።

የተለያዩ መረጃዎችን የሚያደርስበት ሚድያዎቻችንን 3 የቴሌግራም ቻናሎችና 2 ግሩፖች ከ 220ሺ በላይ አባል ያላቸው የ #HIVN ቻናሎች  በአንድ ላይ https://t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0  ላይ ያገኙናል::