Get Mystery Box with random crypto!

ስድስት ሰአት በፈጀው የልብ ቀዶ ጥገና Healing Valves Ethiopia (HVE) በዛሬው እለ | Healing Valves Ethiopia

ስድስት ሰአት በፈጀው የልብ ቀዶ ጥገና Healing Valves Ethiopia (HVE) በዛሬው እለት 11ኛውን የነፃ የህይወት አድን የልብ ቀዶ ጥገና አከናወነ::

የ14 አምቷ ልጃገረድ ከወራቤ አካባቢ የመጣች ሲሆን በተፈጥሮ ካለባት የልብ ችግር (PDA) በተጨማሪ ከተንሲል ጋር ተያይዞ በሚከሰት የልብ በር በሽታ (Severe Mitral Valve regurgitation secondary to RHD) በከፍተኛ የልብ ድካም ውስጥ ነበረች:: በአንደኛ አመት የ Healing Valves Ethiopia ምስረታ ክብረ በአል ላይ በኦድዮ ቪዥዋል አርቲስት ሳምኤል ሀይሉ ተበርክቶ በጫረታ በ250,000 ብር የአዳማ ነዋሪ በሆኑት በአቶ ተስፋዬ ባሌማ አሸናፊነት መወሰዱ ይታወሳል::

Healing Valves Ethiopiaም ይህንን ገቢ ለዚህ የልብ ቀዶ ጥገና በመጠቀም እንዲሁም ሌሎች በረከቶቻችንን አክለን የዚህን ፈታኝ የልብ ቀዶ ጥገና ማከናውን ችለናል:: ልዬ ምስጋና ለአቶ ተስፋዬ ባሌማ እና ለሳምኤል ሀይሉ::