Get Mystery Box with random crypto!

ሃይማኖት አንድ ናት

የቴሌግራም ቻናል አርማ haymanotanednat — ሃይማኖት አንድ ናት
የቴሌግራም ቻናል አርማ haymanotanednat — ሃይማኖት አንድ ናት
የሰርጥ አድራሻ: @haymanotanednat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.45K
የሰርጥ መግለጫ

ኤፌሶን ፬ ፡፭አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።ይቀላቀሉ በዝክ ቻናል የአባቶች ምክርና ተግሳፅ ተለያዩ በሃይማኖት ዙሪያ
ትምህርት አዘል ይለቀቃል ።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:56:24
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥቷል ለመቀላቀል ከስር ያለውን ሊንክ ንኩት።




https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI




.
23 views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:41:50
እማምላክ አሳስቢ ምድር ተጨቃለች
@haymanotanednat
@haymanotanednat
125 viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:54:50 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።  ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።  ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥  ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።  ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።  እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።  ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።  ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። 

ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። 

                          የዩሐንስ ራዕይ 13÷1-9


የ 666 ትርጉሙ ምንድ ነው

ማይክሮ ቺፕስ የሚባለውስ ምንድ ነው

የአለም ፍፃሜስ መቼ ነው

ስለ አለም ፍፃሜ የሚያትተው የራዕይ መፅሐፍስ ትርጉሙ ምንድነው

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
Ŝúbŝčŕibé our youtube channel











26 views20:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:51:34 ዕረፍቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት"
ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተክለሃይማኖት ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክለ፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ
›› ማለት ነው።እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት
ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅዱስ እግዚእ ሐረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀፅንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1207 ዓ.ም ተወለዱ። ጻድቁ በተወለዱበት ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ
ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ
›› በማለት የፈጠራቸውን አምላኬ አመስግነውታል ። ወላም ስማቸው ፍሥሐ ጽዮን አሳብ። የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው።
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ድኩናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲያጠኑ ቆይተው ከእስክንድርያው
ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናና ቅስናን ተቀብለዋል
የፃዳቁ አባታችን ፀሎታቸው በረከታቸው ረድኤታቸውና ምልጃቸው ከእኛ ጋር ይሁን አሜን።
@haymanotanednat
@haymanotanednat
135 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:58:56
እንጸልይ ጸሎት ከሁሉም ነገር በላይ ዋነኛ የክርስቲያን መሳሪያ ነው። ጸሎት የማንኛውም ችግር መፍትሄ ነው፤ ጸሎት በልጅነት ሥልጣን ያከበረንን አባታችንን የምናናግርበት መንገድ ነው። ልጅ አባቱ ቅርቡ እያለ እንዴት ዘወትር አያናግረውም? እንዴት ዘወትር ጭንቀቱን አይገልጽለትም? እንዴት መሻቱን አይጠይቀውም?
አቤቱ ፈጣሪያችን አምላካችን አባታችን
በአንተ ላይ ነው ዘላለም ተስፋችን
@haymanotanednat
@haymanotanednat
329 viewsedited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:15:48
እጅግ የበረታው የፀናው እምነትህ
በምግባር እንድቆም ስቦኛል መንፈስህ
በረከትህ ሞልቶ ፀጋህ እንዲተርፍኝ
ዘወትር በምልጃህ ጊወርጊስ አትራቀኝ
በእውነት ቅዱስ ጊዬርጊስ ታላቅ ቃልኪዳን ከጌታ የተቀበለ ቅዱስ ሰማዕት ነው። ጌታችንም፣ ስምህን የጠራ፣ ዝክርህን የሚዘክር፣ ደጅህ መጥቶ የሚማፀን፣ በስምህ ቀዝቃዛ ውሃ ያጠጣ፣ በቃልኪዳንህ ለሚታመን ሁሉ ያንተን ዋጋ ያገኛል ብሎ ነው ቃልኪዳን የገባለት። ቅዱስ ጊዬርጊስ ይህን ሁሉ ለመስማት እንኳን የሚከብድ አሰቃቂ መከራ ደርሶበት ያገኘውን ዋጋ እኛን ግን በቃልኪዳኑ ብንታመን ስሙን ብንጠራ ብንዘክር እሱ የተቀበለውን ዋጋ እናገኛለን። አይ የእግዚአብሔር ቸርነት። ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዬርጊስ፣ የኢትዬጵያ ጠባቂ፣ ለሰው የሚራራ ሲጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ በምልጃው የሚታመን ሰማዕት ነው። በህይወታችሁ ጉዳይ ሁሉ አማክሩት ችላ ሳይል ይራዳችኋል። የቅዱስ ጊዬርጊስ በረከቱ ይደርብን። ሀገራችንን ከክፉ ይጠብቅልን፣ ለሁላችንም ሰላም ፍቅር አንድነትን ያድለን። የሚዋጉንን የሚፈታተኑንን አጋንንትን ድል የምንነሳበትን ኃይል ያሰጠን። አሜን አሜን አሜን
442 views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:25:06 ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ፤ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም። እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል፤ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል።
"መጽሐፈ ምሳሌ 30፣7፦9 "
487 views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:28:56
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ ባአል በስላም አደርሳችሁ አደርስን አሜን፫
የአምላክ እናት የማያቋርጥ ደስታችን ድንግል ሆይ በድጋሚ ወደ አንቺ በመዞር ለዘላለሙ ምስጋና አቀርብልሻለሁ አንቺ የበዓላችን መጀመሪያ መካከለኛ ና መጨርሻ ነሽ በንጉስ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ከፍተኛ ዋጋ ያለው የከበር ማዕድን አንቺ ነሽ የተጎዳ ማንኛውም አካል የሚጠገንብሽ ስብ የሕይወት ምግብ ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠብሽ ሕይወታዊት መስዊያው አንቺ ነሽ የእግዚአብሔር የፍቅሩ ሀብት ነሽና ደስ ይበልሽ።
@haymanotanednat
@haymanotanednat
535 viewsedited  14:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:10:48
መጨረሻየን አሳምርልኝ
እድሜ ዘመኔን አንተ ባርክልኝ
@haymanotanednat
@haymanotanednat
637 viewsedited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:30:09 #እኔ ማመን የምፈልገውንና ማወቅ ያለብኝን የማስታውሰው ፣ ስደክም የምበራታውና ዝወዛወዝ የምረጋጋው ፣ ስጨነቅ ለራሴ ፋታ የምሰጠውና ወደ ወደቡ የምደርሰው የኖህን መርከብ በማስታወስ ነው።
" ለአንተ ለወዳጄም እልሃለሁ፦ በመጀመሪያ ደረጃ መርከቡ እንዳያመልጥህ፣ ሁላችንም የመርከቡ ተሳፋሪ መንገደኞች መሆናችንን እወቅ። ነቅተህ ጠብቅ ፣ ወደ መርከቢቷም ግባ። ነገ እንደሚመጣ እመን ፣ እርግጥኛ ሁን የኖህ መርከብ የተገነባችው ዝናብ እየዘነበና መጥለቅለቅ ስለነበረ ሳይሆን ወደፊቱ ለሚመጣው የጥፋት ውሃ ነበር። በጤንነትና በጥንካሬ ኑር፤በምድር ላይ ጥፋት በሆነ ጊዜ ኖህ የ600 ዓመት ነበር ። አንተ 60 ዓመት ሆኖህም ቢሆን ለጠንካራ ሃላፊነት ልትታጭ ትችላለህና አትድከም ፣ ጠንክር ተበረታታ። የማይገቡ አሽሙሮችንና በስራህ ላይ የሚደረጉ ቀልዶችን አታድምጣቸው። ዝም ብለህ ስራ ፣ገንባ። የወደፊት ተስፋህንና ህይወትህን በከፍታ ላይ አስቀምጥ። የጥፋት ውሃ ወደ ተራሮች እንደወጣ ሁሉ አንተ ደግሞ ጥፋት ከማይደርስበት የመንፈስ ከፍታ ተቀመጥ።
ለሰላምና ለጤንነትህ ሲባል ጥንድ ሁን። ውደድ ፣ ውሰድ አጥብቀህ ያዝ።(ከንጹሕ እንስሳት ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹህ እንስሳም ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕስትና እንስት .... ተወስዶ እንደተረፈ ሁሉ ለማንኛውም ዘርህ ይተርፍ ዘንድ ጥንድ ሁን ።) ፍጥነት ሁል ጊዜ ይጠቅማል ብለህ አትንቀዥቀዥ። አስታውስ ቀንድ አውጣም ይሁን አቦሸማኔ መርከቧ ላይ ወጥተዋል። ተንኮል ብቻ ያዋጣኛል አትበል!
ፍየልም ይሁን በግ በዚያው ነበሩ፣ ውበት ያድነኛል አትበል ጃርትም ይሁን እባብ ፣ አዞን ይሁን ጉማሬ ፣ ፒኮክም ይሁን ርግብ በዚያው ነበሩ። ስትጨነቅ ገለል ብለህ ተንሳፈፍ፣ እየቀዘፍክ አስብ፣ ተረጋግተህ ውረድ። ልብ በል የኖህ ምክር የተሰራችው በፕሮፌሽናል ገንቢዎች አልነበረም፣ እንዲያም ሆኖ ከዚያ ሁሉ መአት ተረፈች፤ ታይታኒክ ደግሞ የተሰራችው በድንቅ ማሃንዲሶች ነበር፤ እንዲያም ሆኖ በዚያች ኢምንት አደጋ ወደቀች።
ምንም አይነት ዶፋ ቢወርድ፣ ምንም አይነት ወጀብ ቢመጣ፣ ምንም አይነት ጎርፍ ቢጎርፍ #እግዚአብሔር ካንተ ጋር ከሆነ የሚጠብቅህ መሰባበርና መስመጥ ሳይሆን ቀስተ ዳመና ነው። ተስፋ አድርግ ፤ እመን** ወዳጄ (ኦሪት ዘፍጥረትን ከምዕራፍ 7 ጀምሮ ለምን አታነብም!)
አባት ሆይ የኖህን ታዛዥነትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁንና በመርከቡ ገብተን እንድንሄድ የተጠራንና የተዘጋጀን ያድርገን!!!!
@haymanotanednat
@haymanotanednat
574 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ