Get Mystery Box with random crypto!

....እርግጥ ነው ብዙ ተከታይ ሊኖርህ ይችላል ። አድናቂህም በርካታ ሊሆን ይችላል።  ግና ተከ | °•°ቢስሚከ ነህያ °•°

....እርግጥ ነው ብዙ ተከታይ ሊኖርህ ይችላል ።
አድናቂህም በርካታ ሊሆን ይችላል። 
ግና ተከታይህ ሁሉ አድናቂህ አይደለምና ይህን ማወቅ ይኖርብሃል።
 ስህተትህን ለማጋለጥ፣ ዉድቀትህን ለማሳየት፣ ምን እንዳልክ ለማየት፣ አለማወቅህን ለማስረዳት፣
~ በ ሲ ፈርስት የሚከታተልህ አለ፣
~  በሴቭ ዶክመንት የሚያቆይልህ አለ፣
~ በስክሪን ሹት የሚጠባበቅህ አለ፣
 ~ በተለያዩ ወጥመዶች ሊይዝህ የተዘጋጀ አለ፣

ዛሬ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ለየት ያለ ሀሳብ ፃፍ፣ ወጣ ያለ አቋም ያዝ።
ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል። በአሥር ሺ የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው ግና መቶ ተቀባይና አዳማጭ የሌላቸው ብዙ ናቸው።

ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ግን ጥቂት ብቻ የሆነ ጠንካራ ሠራተኞች አሉ።

ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን የተወበት፣ የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ይልቅ መረጃን ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

አንዳንዱን ሰው ሲከታተልህ እንደነበረ የምታውቀው በኮሜንቱና በስድቡ ነው።


ቁምነገሩ የሰው ክትትል አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ።

t.me/HAYAttuna