Get Mystery Box with random crypto!

Hasen Injamo

የቴሌግራም ቻናል አርማ haseniye — Hasen Injamo H
የቴሌግራም ቻናል አርማ haseniye — Hasen Injamo
የሰርጥ አድራሻ: @haseniye
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.26K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-05 13:33:18
ለወርቅ አቅራቢዎች
ይህ አሠራር ተግባራዊ እንዲሆን ከዐመት በፊት ሐሳብ ሳቀርብ የእብደት ይመስል ነበር:: ብዙ ሰው ላይገባው ይችላል:: ብሔራዊ ባንክ ብቻ ሳይሆን ግብርና ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ነገር ቢያደርግ ከብቶቻችን በኮንትሮባንድ ከመውጣት ይታደጋል:: ከዚህ ጎን ለጎን ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥሩን ካላጠናከረ ውኃ ቢወቅጡት እምቦጭ እንዳይሆን::
(ዝርዝሩ መ-ገንዘብ መጽሐፍ ላይ አለላችሁ)::
1.1K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 15:16:57 መንግሥት የፖለቲካ ሥራ ይሠሩልኛል ብሎ በመት^ረየስ አጅቦና አዝሎ መጅሊስ ያስገባቸው ኡስታዞች አንድም የፖለቲካ ሥራ ሳይሠሩለት ጭራሽ አክስረውት ቁጭ አሉ:: ምዕመኑን ከማረጋጋት ይልቅ መስጂድ መሄድ እስኪያስፈራ ድረስ ኢማሞችን በመደ^ብደብ በማሳ^ፈን ከፍተኛ ስጋት ሆኑ:: መደበኛ ሥራ አድርገው የያዙት መዋጮ እያሉ ምእመኑን መግፈፍ ሆነ::

እነሆ ውጤቱ ዛሬ ታየ:: ለብቻቸው ስቴድየም የሚሞሉ ዑለሞች ውስጥ አንድ እንኳ ለዓይነት አልተገኘም:: ዑለማው ማንም ቀስቅሶት ወይም አቀናጅቶት ሳይሆን ያቀናጀው ግፍ አቀናጀው:: በእርግጥ የሀበሻ ዑለማ ወትሮም በአላህ ገመድ የተቀናጀ ነው:: ደረሳው በሸይኹ አጠገብ ሊንጫጫና ሊጮኽ ቀርቶ የቁርአን ገጽ ሲገልጽ እንኳ <<ክሿ>> አያደርግም:: ጉልበት ስሞ ይቀመጣል:: ከፊደል በፊት አደብ (ሥርዓት) ነው የሚቀራው:: ደረሳው ስላልጮኸ ሙያ የሌለው ይመስላል:: ሸይኹ ሁላ ዝም ሲል ምንም የማያውቅ ይመስላል እንጂ ሊቀ ሊቃውንት ነው:: ማንነቱ ምላሱ ላይ ሳይሆን ግንባሩ ላይ እንደ ጨረቃ ይበራል::

ሙሉ የሀበሻ ዑለማእ ያደመበት መንግሥት ሒሳቡን ያስላ:: ወይም እንደ አብራሃ ዝሆኑን ጋልቦ በትእቢት ይቀጥል::
689 views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:34:19
1.5K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:13:01
1.2K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:07:11 ኢማሙን የማያውቅ
በክ^ህደት እንደሞ^ተ ነው
==================
መንገዱ ቀጥ ያለ ነው:: ምርጫው ለግለሰቡ ተትቷል::
ጌታችን አላህ
ነብያችን ሙሐመድ ﷺ
ኃይማኖታችን ኢስላም
ኪታባችን ቁርአን
የዘመኑ ኢማም (ከነቢያችን ﷺ በሗላ)
_____
አላህ ለየሕዝቡ ነብይ ልኳል:: ለዚህኛው ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ናቸው:: እሳቸው ከበስተሗላቸው ለሚመጡ ሕዝቦች ኢማሞቻቸውን እንዲያውቁ አደራ ብለዋል::

مَنْ مَاتَ وَلَمْ يَعْرِفْ اِمَامَ زَمَانِه مَاتَ مِيْتَةً جَاهِلِيَّةً
ኢማሙን ያላወቀ በድንቁርና (ኩፍ^ር) እንደሞተ ነው:: (ሀዲስ ኢማም ሙስሊም, አህመድ, አቡዳውድ ሲሆን የጦበራኒ ላይ << ቢሻው አይሁd ቢሻው ነሷራ ሆኖ ይሙ^ት>> ) ይላል::

መሪ የሌለው መሪው ወይ ሸይጧን ወይ አይሁd ወይ ነሷራ ነው:: መንግሥት የሌለው ሀገርና ሕዝብ የማንም መጫወቻ እንደሚሆነው ሁሉ ኢማም የሌለው ሕዝብም የኩ^ፍር መጫወቻ ይሆናል::

ኢማም ካዘዘ ማመጽ ከኃይማኖት ያወጣል:: ውጊ^ያ ውስጥ ገብቶ መሸሽም ከእስልምና ያወጣል:: ኢማም ሳያዝ ው^ጊያ ከትዕዛዝ በሗላ << አላሁ አክበር>> እያሉ መሮጥ አይቻልም:: በወረርሽኝ ወቅት ኢማም ውጡ ካለ መውጣት, ከከለከለም መቀመጥ ነው:: ያ ሰው በወረርሽኙ ቢሞት እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::

ስለዚህ እያንዳንዳች ኢማሞቻችንን ማወቅ በእስልምና ግዛት ውስጥ መሆን/አለመሆን ይበይናል:: ኢማሞቻችን ማለት ዑለሞች ናቸው:: ሌላው እንኳ ግርግርና የሸይጧን ፈስ ነው::

በቁርአንና በሀዲስ መሠረት ኢማሞች አምስት ናቸው::
1) ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ
2) ቁርአን
3) የዘመኑ ኢማም (ኸሊፋ)
4) እናት
5) የራስ የሥራ መዝገብ (ማንም አያውቀውም)

ኢማምነት በጩኸት የበለጠው ሳይሆን በዕውቀትና በስነምግባር የላቀው ... ልምራችሁ ያለው ሳይሆን እንዲመራ የተገደደው ነው::
1.2K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 17:04:35
ጨረቃ በአሁን ሰዓት የአዲሱ ወር (የሸዋል) ሆና 0.3% Waxing ላይ ነች:: ዋክሲንግ ማለት ከአዲስ ጨረቃ በሗላ እስከ ግማሽ ጨረቃ ወይም የመጀመሪያው ሩብ ድረስ ማለት ነው::
በአዲስ አበባ አድማስ ላይ 21 ደቂቃ ትቆያለች:: ዒድ ነገ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ቢሆንም ግን ይህንን የሚከታተሉ ዑለሞች ሲነግሩን ብቻ ፆማችንን እንፈታለን::
998 viewsedited  14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 18:06:56
ነገ ሀሙስ ጨረቃ ከፀሐይ መጥለቅ በሗላ 20 ደቂቃ ትቆያለች::
ፀሐይ 18:34
መግሪብ 18:35
ጨረቃ 18:55
ድምቀት 0.1% (እጅግ አነስተኛ ቢሆንም ለመታየት በቂ ነው)

ሆኖም ለ20 ደቂቃ አድማስ ላይ ስለምትቆይ ለማየት በቂ ነው:: ከጨለመና ካልታየች በሀዲሱ መሠረት ጁማዓ መፆም ግዴታ ይሆናል::
ግን ግን ጁማዐ የምትጠልቀው ከዒሻ በሗላ 20:05 በመሆኑ በጣም ሩቅ ክፍተት ነው:: በመሆኑም ዒድ ጁምዓ የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው:: ሌላ ግን ... ያው ዐይተናል ፍቱ ሲሉን ነው የምንፈታው::
1.3K views15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 13:09:43 በምንዛሪ ለውጡ
ምን እናድርግ ለምትሉ
(Abdulkadir Hajj Nureddin)
===============
ብሎላችሁ ከባንክ የተበደራችሁ ብድር አዘግዩ:: ድሮም የሚጎዳው መንጋው ነው:: ሰው መንጋ መሆን የሚጀምረው ለሀብታም ሲቆጥብ ነው:: አንዳንድ ላም ይቅርታ ማይም Intellect Free ላይ ይቆጥባል

ያልተጌጠ ጥሬ ወርቅ መያዝ ይመከራል:: ውጭ ያላችሁ ስትመጡ ፍተሻው ኃያል ስለሆነ አስቡበት:: ምክንያቱም መንግሥትም ወርቅ እየሰበሰበ ስለሆነ:: ሁሉንም መ-ገንዘብ መጽሐፌ ላይ ታገኙዋቸዋላችሁ)

ዕቃ በዱቤ አትሽጡ:: ከሸጣችሁም ሰብስቡ::

መሬት መግዛት ብዙም አይመከርም:: ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች ላይ መዝመቱ አይቀርም:: ምክንያቱም ሰው ከባንክ የሚበደረው ለሥራ ሳይሆን ግሽበትን ተማምኖ ነው:: ተበዳሪ የሚያተርፈው ሠርቶ ሳይሆን የሞኝ ቆጣቢዎችን ገንዘብ ከባንክ ተበድሮ መሬትና ዕቃ ገዝቶ መልሶ ለቆጣቢ ሲሸጠው ግሽበት ይፈጥራል:: ጭራሽ እሱ ለባንክ ከሚከፍለው ወለድ ላይ ታክስ ይቀነስለታል:: በአንድ ድንጋይ ሁለት ትርፍ::

ደሞዝተኞች በደመወዛችሁ አስቤዛ ግዙ:: ለረጅም ጊዜ የማይበላሹና ለወደፊት የምትጠቀሙባቸውን ቁሳቁሶች ያዙ::

ዕቁብ መጀመሪያ ብሉ:: መጀመሪያ የማይደርሳችሁ ከሆነ ዕቁቡን ግዙና ዕቃ ግዙበት::

ውጭ ሀገር የምትሄዱ ሰዎች ከአሁኑ ትኬት ቁረጡ

ቶሎ ለመሞት ያልፈለጋችሁ ዘና በሉ:: መታነ^ቅም መጨነቅም መፍትሔ አይደለም:: የማን ቤት ፈርሶ ማን በቪላ ይኖራል?

አክሲዮን የምትገቡ ሰዎች በጣም በማትፈልጉት ብር ብቻ ይሁን:: በመቋቋም ላይ ያሉ አክሲዮኖችን አትዳፈሩ:: የቆዩት ላይ ባለሙያን አማክሩ::

በግና ፍየል ገጠር ላይ ገዝታችሁ ተውዋቸው:: ሁለት ሁለት ስለሚወልዱ ከአውሬ የተረፉት ይበቃሉ::

ይቀጥላል
1.7K viewsedited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:31:12 ተውሂድ በጣም ቀላል
እጅግ በጣም ጥልቅ ነው
==================
መስተካከልና መደላደል (ኢስቲዋእ) ለፍጡር (መኽሉቅ) እንጂ ለፈጣሪ (ኻሊቅ) ተገቢ አይደሉም::

አላህ ውሃን ፈጠረ, ዐርሹን (ዙፋኑን) በውሃ ላይ አደረገው:: ቀለምን ፈጥሮ ጻፊ አላት:: ሁሉንም ተከሳቾችን ጻፈች:: (ቀለም ካልገባችሁ አርክቴክቸራል ዲዛይን በሉት:: ግን ይህም አይገልጸውም)::

ከዚያ ልክ ቤት መሥራት ከመሬት እንደሚጀመረው የጠፈሩ ቤት ምድሮችን በመዘርጋት ተጀመረ:: ሰማያት ጭስ ነበሩ:: ከጭሱ አንስቶ ጣራ አደረጋቸውና ሕዋውን በከዋክብት (ፕላኔቶችም ጭምር) ፈጥሮ እንደ አምፖል አስጌጣቸው::

ሰማይም ምድርም ከዋክብትም በውድ ወይስ በግድ ትስተካከላላችሁ ብሎ ጠየቃቸው:: <<ቃለታ አተይና ጧኢኢን - ወደን ተደስተን ቦታ ቦታችንን እንይዛለን>> ብለው ልክክ አሉ:: ልክ እኛም ለሶላት ኢስተው ስንባል ቦታ ቦታችንን እንደምንይዘው:: እነዚያ እስካሁን አላመጹም:: እኛም አማፂ መሆን የለብንም::

ከቀደማቸው ከዐርሽ (ዙፋን) ጋር ተስተካከሉ:: ተደላደሉ:: በአላህ ዘለዓለማዊ የራኅመት (ርኅራሄ) ሥልጣን ስር ሆኑ:: አላህ ለፍጡሩ ሁሉ አዛኝ ነው:: የቁርአን 114 ምዕራፎቹ 113ቱ በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሚል ይጀምራሉ::

የአላህ ራህመት, ሥልጣን, መፍጠር, ማዘዝ መነሻና መድረሻ የሌለው, ዐርሹንም ሌሎች ፍጡራንንም የቀደመና አበዲይ (ጊዜና ቦታ የማይቀድመው, መጥፋት የማይከተለው) ነው::

ሥልጣኑ በፍጡሩ ዐርሽ የሚገደብ, የሚገመትና የሚመተር አይደለም:: ዐርሽም, ኩርሲይም, ሰማያትና ምድሮች ከመኖራቸው በፊት የነበረ, የሚኖር, ከየትኞቹም የማይፈልግ in respect of ፍጡር የማንመጥነው አምላክ ነው አላህ::

የደመ ነፍስና የሸይጧን የአዕምሯዊ <<ኸያል-ውልብታ>> ስዕሎቻችንና ጣዖታችንን ስንቀድ ወደ ተውሂድ መንገድ እንጀምራለን:: አላህን በእርሳስም ይሁን በጭንቅላት ግድግዳ አንስለውም:: የነፍሲያ ኸያል (Illusions) ማስወገድ ግድ ነው::

አላህ ዋሂድ (1) ሳይሆን አሃድ ነው:: ዋሂድ (1) ስንል ኢሥነይን (2), ሠላሳ (3), 4,...1,000 ቁጥሮች ይከተሉታል:: አሃድ ብለን ግን ከሗላው ኢሥነይን ከፊቱም ዜሮ የለም:: አሃድ አሃዱን አሃድ!

ለዚህም ነው ቁርአን <<ቁል ሁወሏሁ አሃድ - አላህ አሃድ ነው በል ...>> የሚለው:: ዐማርኛው ትርጉም ላይ አሃድም ዋሂድም <<አንድ>> ይላቸዋል:: የቋንቋው አለመስፋት ወይም የእኛ መግባባት ድክመት ሊሆን ይችላል::

ቁርአን ለምታውቁ ሰዎች:-
<<ዋሂድ>> ግን አላህን አስመልክቶ ሲመጣ ሌላ የአላህ ስሞችን ለማብራራት ነው:: ዋሂዱል ቀሃር እንደሚለው:: አላህ <<እኛ>> ሲል እና <<እኔ>> ሲል የተለያየ መልዕክት እንደሆነው:: <<እኛ>> ካለ አድራጊነታዊ ንግሥናና ኩራት ሲሆን <<እኔ>> ካለ አምልኮታዊ ብቸኝነት ሲነግረን ነው:: ሁለቱ በአንድ አጭር አንቀጽ ተያይዘው የመጡበት አለ:: እንዳይረዝም ልቋጨው::
-> አንድም የቁርአን አንቀጽ የሌለው መልዕክት አላስተላለፍኩም::
1.5K viewsedited  06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 04:15:54 አሜሪካ ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የዶላር ጉዳይ ትንሽ አሳሳቢ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ:: ከፊያት ዶላር ወደ ዲጂታል ዶላር የሚደረገው ሽግግር መናጦች ይኖሩታል:: ኤቲኤሞች ብዙም ፋይዳ ላይኖራቸው ይችላል:: አሜሪካ ለ80 ዓመታት ዐለምን አሞኝታ አሁንም ለዳግም ማሞኘት ዝግጅቷን ጨርሳለች::

የወርቅ ሳንቲሞች ለHedging በጣም ጥሩ ቢሆኑም ግን Convertibility ላይ ችግር ይኖረዋል:: መልሳችሁ ወደ ካሽ መቀየር ልትቸገሩ ትችላላችሁ:: ምክንያቱም ዲጂታል ዶላር ቦታውን እየተካ ነውና:: ይዛችሁ ወደ ኢትዮጵያ ስትመጡ ከዚያም ላያስወጡዋችሁ ይችላሉ:: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም ወርቅን በብዛት እየገዛ ስለሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ ከፍተኛ ቁጥጥር አለው:: ምክንያቱም በልዋጩ ዶላር ስለሚያሸሽ ነው::

ስለዚህ ሀበሾች ተሰብስባችሁ ተወያዩ:: ዜናዎችን አንብቡ:: ተንትኑ:: ከአሜሪካ ውጭ ንብረት ያዙ:: What’s the future of money ላይ የሚነግሩዋችሁን ሁላ አትመኑ:: ዘላችሁም አትግቡላቸው:: ብዙ scammers አሉ::

(ቋሚ የዙም ውይይቶችን እናመቻች ይሆናል)::
1.3K views01:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ