Get Mystery Box with random crypto!

ተይ አታልቅሽብኝ እማየ በሞቴ፣ አንችን ከፍቶሽ ማየት አይችልም አንጀቴ። አንች የኔ ስስት ስቀቀን | ||HARIS TUBE||™

ተይ አታልቅሽብኝ እማየ በሞቴ፣
አንችን ከፍቶሽ ማየት አይችልም አንጀቴ።
አንች የኔ ስስት ስቀቀን ናፍቆቴ፣
እመጣልሻለሁ አታልቅሽ እናቴ።

ሀሎ ስልሽ ጊዜ ድምፅሽን ስሰማ፣
ናፍቆቴ ጨመረ ሆደ ባባ እማ፣
አንችም ሆደ ባሻ እኔም ሆደ ባሻ፣
አይዟችሁ ባይ የለ ሁለት አልቃሻ፣
እንጀራ ለይቶን የእለት ከለት ጉርሻ፣
የመለየት እጣ የሌለው መሸሻ፣
ፀድቆ እንዳይቀርብን እስከ መጨረሻ፣

እማ ፀሎት አርጊ በፍፁም አታልቅሽ፣
ወደሱ ተማፀኝ ይሰማሻል ጌታሽ።
ሀሎ ስልሽ እማ ስትሰሚ ድምፄን፣
ያለያየን ጌታ ደግሞ እንዳገናኘን፣

ስቀሽ አነጋግሪኝ እንባሽን ዋጥ አርገሽ፣
ተስፋሽን መግቢኝ አይዞሽ አይዞሽ ብለሽ።
እድሌ ባይቀና ባልገባ ከእቅፍሽ፣
ጆሮየ ይስማልኝ ስትስቂ ደስ ብሎሽ።
ከልጆችሽ መሀል እኔ ተለይቸሽ፣
ድምፅሽን ስሰማው ገና ሀሎ ስልሽ፣
የናትነት ሽታ ማራኪ ጠረንሽ፣
የሚደባብሡኝ ለስላሳ እጆችሽ፣
ጠንካራ ክንዶችሽ የሚሞቀው ጉያሽ፣
ድቅን ይልብኛል ይመጣል ትዝታሽ።

እማ አታልቅሽ በፀሎት ጠንክሪ፣
አምላክ ከፈቀደ ካደረገን ኗሪ፣
አመት እለት ሁኗል እማ አትጨነቂ፣
እመጣልሻለሁ በተስፋ ጠብቂ።

እናቱን የሚወድ ሼር ያድርግ

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @haris_tube1  
JOIN: @haris_tube1      ╚════════════╝