Get Mystery Box with random crypto!

Harari Mass Media Agency

የቴሌግራም ቻናል አርማ hararimassmediaagency — Harari Mass Media Agency H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hararimassmediaagency — Harari Mass Media Agency
የሰርጥ አድራሻ: @hararimassmediaagency
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 986

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 16:49:47 Itti Aantuun Piresidaantii Naannoo Hararii Aadde Misraa Abdallaa dargaggoonni tajaajila tola ooltummaa irratti dammaqinaan hirmaachuu akka qaban ibsan.
****
Naannoo Harariitti Sagantaan Cufiinsa Hojii Tola Ooltummaa Bonaa bara 2015 fi Baniinsa Hojii tola Ooltummaa Gannaa Dhaadannoo "Tola Ooltummaa Olka'iinsa Itoophiyaaf" jedhuun har'a ifatti eegalameera.

Naannoo Hararitti tajaajilli tola ooltummaa Gannaa 2015 dhaadannoo " Tola Ooltummaa Olka'iinsa Itoophiyaaf " jedhuun ifatti eegalameera.

Keessummaa kabajaa Sagantichaa kan ta’an, Itti Aantuun Piresidaantii Naannoo Hararii Aadde Misraa Abdallaa sagantichi bakka hojiin gaarii fi namummaa itti hojjatamuu fi faayidaa hawaasummaaf wal tumsuu qofa osoo hin taane, jaalalliifi nagaan itti mirkanaa’u ta'uu ibsaniiru.

Tajaajila bara darbe naannicha keessatti hojjetamaa ture irraa muuxannoo fudhachuun rakkoolee gama adda addaatiin mul’atan furuuniifi tumsuun hanqina jiru guutuu, hambaa diinagdee horachuu fi olka’iinsa Itiyoophiyaa mirkaneessuu akka dandeenyu ibsaniiru.

Kana malees, ashaaraa magariisaa irratti hirmaachuudhaan wabii nyaataa mirkaneessuu bira darbee, mana namoota dadhaboo haaromsuun itti gaafatamummaa hawaasummaa bahuu akka qabnuu fi ji’oota 2 dhufan keessatti hojiiwwan tola ooltummaa adda addaa 12 akka raawwataman ibsaniiru.

Itti Aantuun Piresidaantii Naannoo Hararii Aadde Misraa Abdallaan dargaggoonni tajaajila tola ooltummaatiin ashaaraa isaanii kaa’uu keessatti dammaqinaan hirmaachuu akka qaban ibsuun, sochii qaamaa karaa araada irraa bilisa ta’een xiyyeeffachuun lammiilee fayyaa ta’an oomishuuf gahee isaanii akka ba’an waamicha dhiyeessaniiru.

Saganticha irratti dargaggoota waldaalee sagantaa tola ooltummaa kanaan ga’umsa gaarii agarsiisaniif badhaasaafi beekamtii kennaniiru.

Dargaggoonni hojii tola ooltummaa ganna kanaa irratti hirmaatan badhaasa beekamtii argachuu isaaniitti gammaduu isaanii ibsuun, gannaa fi gara fuula duraatti hojii fooyya’aa hojjechuuf qophii ta’uu ibsaniiru.

Itti Aantuun Piresidaantii Naannoo Hararii Aadde Misraa Abdallaan, qondaaltonni olaanoo naannichaa, maanguddoonni, dargaggoonni fi keessummoonni affeeraman argamaniiru.

Naannoo Hararitti tajaajila tola ooltummaa ganna bara kanaa irratti dargaggoonni kuma 40 kan hirmaatan yoo ta’u, hojiiwwan kunneenis lammiilee kuma 49 ol kan fayyadamoo taasisuufi gama kanaan Birrii miiliyoona 19 ol qusachuun ni danda’amu ta’uu odeeffannoon Biiroo Dhimma dubartootaa, daa’immanii fi dargaggoota naannichaa irraa argame ni mul’isa.

Aayishaa Raamadaan’tu gabaase.
29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
89 viewsHarar Mass Media, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 15:41:19 አዜባች ወለባይ ኢባሮታችቤ ሩሕዚዩዛጥ አትታጮቱ የነበሩኩት አቤጆትቤ መትሰአድ ዛልበዩነት ሀረሪ ሑስኒ ሒጋኝ ራኢስ ጊስቲ ሚስራ አብደላ ገለጡ፡፡
**********
ሐረሪ ሑስኒ 2015 ገና ወቅቲ ወለባይ ኢባሮት ዲላጋ መክፈቲ ኢሾት ሚሕሪራ ዞ ‹‹ኦርነት ኢትዮጵያ ለአይነትሌ›› ዩልዛል ሒርቃኦት ጪቅቲቤ ሖጂ ሞይ ዛሒርቤ ተኤገላ፡፡

ሞይዞ ዚጊድረ ኑግዳ ዚሀረሪ ሑስኒ ሒጋኝ ረኢስ ጊስቲ ሚስራ አብደላ ኢሾት ሚሕሪራዞ ኦርነት ኢንሳኒያነት ዛጥ ዲላጋች ዪደለግበዛል አዝዞኩትሶም ዳይ-ሐዋዚያ ፋይዳ ፣አጥጢቤ አጥጢ መትከሐልቲ ሞሸቤ ቃጪ ሳላምዋደድ የቂን ነሽበዛና ኢንተ ባዩ፡፡ሑስኒዞቤ ሑሉፍ ዛዩ አመት ዚትደለጉ ኢባሮታች ሒርፈታቹ መንሰእቤ ኢስበልበላት አትታያችቤ ዛሉ ጪንቂያች መፍታሕቤ መትካሐል ቂበላናቹ ኒማልበዛና፣ኢቅቲሳዲያ ፋይዳ ነገኝበዛና አዝዞኩትሶም ኢትዮጵያ ለአይነቱ የቂን ነሽዛና ኢንተ ባዩ፡፡

ዪቤዲበያ ወሪቅ አሻራ መትሰአድቤ ዚሐንጉር ዳማና የቂን ሞሸቤ ዲባያ ታኽዛሌለያች ጋራቹው መሔጀስቤ ዳይ -ሐዋዚያ መስኡሊዩው መትወጠእ የትኺሽዛልነት ገለጡማ ዪዲጅ 2 ወሕሪ 12 ወለባይ ኢሾትዋልነትቤ ዪትሜሐርዛልነት ገለጡ፡፡

አዜባችዞ ወለባይ ኢባሮታችቤ አሻራዚዩው ሞረድ ገረብቤ ዪትሰአዲኩት ሒጋኝ ረኢስሴ አቴወቁ፡፡ሐረራቤ ዚኔዛፍ ሐለት ፎኝ መቦአሌ ሪያዳ ለአይቤ አቤጆት መትሰጠዞ አፌት ቃም ዘለመዳኒ ሞጨ ገረብቤ ሩሕዚዩዛጥ ሳሙ ዪትወጠኡኩት ሉኽዚዩው አቀረቡ፡፡

ሞይዞቤም ወለበይ ዲላጋ ለአይቤ አማን አሜሐሮት ዛሹ አዜብ ሙጋዳችሌ ሩበትዋ ቢቆት ሰጡ፡፡ዪሩበቱ ዚነሰኡ አዜባቹውም ዪሩበቱ መግኛዚዩቤ ተስዛዬዩነት አሴነኑ፡፡

ዲባያቤም ገናቤ ዪዲጅ ዲላጋች ለአይቤ ዚቅቲቤ መድለግሌ ጠብቲ ለአይቤ ዛሉነት አሰነኑ፡፡በርናሚጅዞ ለአይቤ ሒጋኝ ረኢስ ሚስራ፣ሑስኒዞ ላቂ ኤመሮታች፣ባድ ረጋች፣አዜባችዋ ዚትፌሩ ኑግዳች ተሰአዱ፡፡

ሀረሪ ሑስኒቤ ሖጂ አመት ወለባይ ኢባሮትቤ 40 አልፊ አዜባች ዪትሰአድዛሉ ዪትሴአድዛሉ ዚኻነሰአ ዪትሜሐርዛል ዲላጋችቤ 49 አልፊቤ ላአይ መዳኒያች ተነፋኢ ዪኹንዛሉነትዋ ዪቤዚትሊሓ ሐደቤ 19 ሚሊዮን ብርቤ ለአይ ውጮት መስለጥ ዪትፋረክዛልነት ሑስኒዞ ኢንዶቻች ዊጃችዋ አዜባች ቢሮቤ ዘጋኝ ኔው ማእሉማት የቃናል፡፡

አይሻ ረመዳን
29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
86 viewsHarar Mass Media, edited  12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 15:39:43 የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት ቤቶች ላይ የሚታየውን ህገወጥነት ከመከላከል አንፃር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡
*********
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉ መንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የ2015 በጀት አመት አፈፃፀም እና የ2016 እቅድ ገምግሟል፡፡

የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ በመንግስት ቤቶች ላይ የሚታየውን ህገወጥነት ከመከላከል አንፃር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

ሪፖርቱን ለቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት የሀረሪ ክልል መንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ረመዳን ኡመር ኤጀንሲው አገልግሎቱን ለማስፋፋትና አዳዲስ የሚከራዩ ቤቶችን ግንባታ ለማካሄድ ከባንክ ብድር እንዲመቻች እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ በ06 ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ቤቶች እድሳት ለማካሄድና ቅርስነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲሰራ ከባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን በሪፖርቱ ተገልፃል፡፡

ስራው በ2015 በጀት አመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም የተመደበው በጀት ለስራው ከሚስፈልገው ባለመመጣጠኑ ሳይሰራ መቆየቱ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በሚያስተዳድራቸው መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ህገወጥ ግንባታዎችን ለመከላከል ከደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው መኖሪያ ቤቶችን ወደ ንግድ ቤት የሚቀይሩ አካላትን በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ እርምጃ መውሰዱንም ገልፀዋል፡፡

የመንግስት ቤቶች ካርታ እንዲኖራቸው ለማድረግ እየተሰራም መሆኑንም ተናግረው በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች መሆናቸው አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ የመልካም አስዳር ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋና ምቹ አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን በቀረበው የ2016 እቅድ የተመለከተ ሲሆን በመንግስት ቤቶች ላይ የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በ2015 የታየውን የበጀት ጉድለት በማስተካከል የታዩ ክፍተቶች በማረም ስኬቶችን እናስቀጥላለን ሲሉም የኤጀንሲው ሀላፊ ገልፀዋል፡፡

የዘመናዊ አሰራር ስርዓትን በመዘርጋት በዘርፉ የሚገኘው ገቢ ለማሳደግ እንሰራለን ሲሉም ተናግረው በ2016 ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱንም ገልፀዋል፡፡

የቀረበውን አፈፃጸም ሪፖርት እና እቅድ ያደመጡት የቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄና አስተያየት ያነሱ ሲሆን ኤጀንሲው ከግዜ ወደ ግዜ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ጠቁመው በመንግስት ቤቶች ውስጥ የሚካሄዱ ግንባታዎች ለመከላከል ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል፡

በሰራተኞች አቅም ግንባታ ላይ ስራ መሰራት ያለበት መሆኑን ሀሳብ ሰተው ኤጀንሲው ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽነ ጋር ያለው ቅንጅት ምን ይመስላል የሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡

ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሸ እና ማብራሪያ የሰጡት አቶ ረመዳን ኡመር የውስጥ የማስፈፀም ብቃት ለማሳደግ ስልጠናዎች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀው ሌሎች የተነሱ አስተያቶች በግብዓትነት ወስደው የሚሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢክራም አብዱራህማን ኤጀንሲው ቀደም ሲል ከምክር ቤቱ የተሰጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ ማድረጉ የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡

ጠንካራ የሆነ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ መስራት እንዳለበት እና ለመንግስት ቤቶች የሚደረገው እንክብካቤ ሊጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በጀጎል አካባቢ የሚገኙ ቤቶች አለም አቀፍ ቅርስን በማይጎዳ መልኩ መታደስ እንደሚገባም አሳስበው የቤቶች ኪራይ ማሻሻል ጋር ተያይዞ ጥናት ላይ የተመሰረተ ስራ መስራት እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

የኤጀንሲው የ2016 እቅድ ከፕላን ኮሚሽን ጋር ታይቶ ማሻሻያ እንዲደረግበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ዲኔ መሀመድ
29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
58 viewsHarar Mass Media, edited  12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 15:36:13 ወጣቶች በበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች አሻራቸውን ከማኖር አኳያ በትኩረት እንዲሳተፉ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ጥሪ አቀረቡ፡፡
**********
የሀረሪ ክልል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ‹‹በጎነት ለኢትዮጵ ከፍታ›› በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

በሀረሪ ክልል የ2015 የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በዛሬው እለት ‹‹በጎነት ለኢትዮጵ ከፍታ›› በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ መርሃ ግብሩ በጎነትና ሰዋዊ የሆኑ ስራዎች የሚሰሩበት እንዲሁም በማሕበራዊ ጥቅም እርስ በእርስ ትብብር ከማድረግ ባለፈ ፍቅርና ሰላምን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ባለፈው አመት ከተሰሩ አገልግሎቶች ልምዶችን በመውሰድ በተለያየ አካባቢዎች ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ በመተባበር ክፍተቶችን የምንሞላበትና ፣ኢኮኖሚያዊ ትሩፋትን የሚናገኝበት እንዲሁም የኢትዮጵያን ከፍታ የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአረንጓዴ አሻራ በማሳተፍ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገርና የአቅመ ደካሞችን ቤቶችን በማደስ ማሕበራዊ ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባም ገልፀው በቀጣይ 2 ወራቶች 12 በጎ ፍቃድ ተግባራት እንደሚከናወኑም ገልፀዋል፡፡

ወጣቶች በበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች አሻራቸውን ከማሳረፍ አኳያ በትኩረት እንዲሳተፉ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ገልፀው ከሱስ በፀዳ መልኩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት በማድረግ ጤናማ ዜጋን ለማፍራት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በእለቱም በበጎ ፍቃድ መርሃ ግብሩ ጥሩ አፈፃፀም ላከናወኑ ወጣት ማሕበራት ሽልማትና እውቅና ሰጥተዋል፡፡

በበጋ በጎ ፍቃድ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችም እውቅና ሽልማት ማግኘታቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው በክረምትና በቀጣይ በሚሰሩት ስራዎች ጠንክረው ከዚህ የተሻለ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

በሀረሪ ክልል በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 40 ሺህ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በሚከናወኑ ተግባራትም ከ49 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ከዚህ ጋር በተያያዘም ከ19 ሚሊየን ብር በላይ ወጪን ማዳን እንደሚቻችል ከክልሉ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዘጋቢ ፡- አይሻ ረመዳን
29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
58 viewsHarar Mass Media, edited  12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 14:49:02 ወጣቱ ስለሀገሩ በጥልቅተ እንዲረዳ እና ስብእናውን በመልካም ሀሳቦች እንዲገነባ ሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡
**********
ሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች ከክልሉ ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን በሀረር ከተማ ተገኝተው ችግኝ መትከልን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ተግባራትን ስራዎችን አካሄደዋል።

ሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች ከክልሉ ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን በሀረር ከተማ ተገኝተው ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ፣ ማእድ የማጋራት፣ እንዲሁም የደም ልገሳ መርሃግብርንና በአብረሃ ባታ የአረጋዊያን ማቆያ ማዕከል በመገኘት አረጋዊያንን የመንከባከብና ሌሎች የበጎ ተግባራትን ስራዎችን አከናውነዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ የወጣቶቹ ተግባር የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ እንዲሁም ሰላም፣ ፍቅርና አንድነትን ለማጎልበት እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የባህልና የአኗኗር ልምድ የሚወሰድበት መሆኑን አስታውሰው ይህም ወጣቱ ስለሀገሩ በጥልቀት እንዲረዳ እና ስብእናውን በመልካም ሀሳቦች እንዲገነባ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በወጣቶቹ በበጎ ፍቃደኝነት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትና መልካምነት ድንበር እንደሌለው የሚያመላክት ነው ብለዋል።

የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶቹ ባከናወኑት የበጎ ፍቃድ ስራ እንደተደሰቱ በመግለፅ በሀረር ቆይታቸው ብዙ ትምህርት እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡

የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች በጎ ፍቃደኞች ‹‹ በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ›› በሚል መሪ ቃል በሀረሪ ክልል በተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግት ስራዎች ላይ ተሳትፈው የሀረር ቆይታቸውን በማጠናቀቅ ወደ ሱማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ዘጋቢ ፡- መሀመድ ቶፊቅ
29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
67 viewsHarar Mass Media, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 14:46:41 በሀረሪ ክልል "የወል እውነቶችን የማፅናት ቀጣይ የትግል ምዕራፋ" በሚል ርዕስ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና መጠናቀቁን ብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለጸ።
********
በብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም ኡመር የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ መጠናቀቀን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በውይይቱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን ጨምሮ መላው የፓርቲው አባላት መሳተፋቸውን ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ተወያይቶ ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው መድረክ በስኬት መጠናቀቁን ጠቁመው በመድረኩም ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ማለፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ጥቅል ውይይት መድረጉን ገልጸዋል።

መድረኩ በወል እውነታዎች ላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የፓርቲው አባላት የጋራ አረዳድና አቅም የፈጠረ መሆኑን ጠቅስዋል።

አቶ አብዱልሀኪም አክለውም የክልሉን ህዝብ በማሳተፍ አንገብጋቢ የህብረተሰብ ጥያቄዎችን መመለስ የምንችልበት ፈጥነንና ፈጥረን የብልጽግና አላማዎችን ለማሳካት በቁርጠኝነት ለመስራት ስንቅ የሰነቅንበት ነው ብለዋል።

ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት አሰራር በማጠናከር ለህዝቡ የተገባውን ቃል ለማስፈጸም በክልል ደረጃ ለፓርቲው አመራሮችና አባላት ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በስኬት መጠናቀቁን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን ለማፅናትና የወል እውነትን መገንባት ላይ አመራሩና አባሉ የበኩሉን እንዲወጣ መሰረት የተጣለበት መድረክ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሀገራችንም ሆነ የክልላችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና በሚፈለገው ደረጃና ፍጥነት ለማረጋገጥ ፓርቲው በሁሉም ረገድ አዳዲስ ሃሳቦችን ገቢራዊ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል እንደሚገኝ ገልጸዋል።

29/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
58 viewsHarar Mass Media, 11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:51:32 Bara 2015 ji’oota 11 keessatti birrii biiliyoona 1.59 walitti qabamuu Biiroon Galiiwwan Naannoo Hararii beeksiseera.
********
Koreen Dhaabbii Mana Maree Naannoo Hararii Gabaasa Raawwii Karoora Bara 2015 Biiroo Galiiwwan Naannichaa gamaaggame.

Koreen Dhaabbii Mana Maree Naannoo Hararii Gabaasa Raawwii Karoora Bara 2015 Biiroo Galiiwwan Naannichaa gamaaggame.

Hogganaan Biiroo Galiiwwan Naannichaa Obbo Baqqalaa Tamasgeen gabaasa raawwii hojii kana koree dhaabbiitiif kan dhiyeessan yoo ta’u, ji’oota 11 darban keessatti galii gibiraa fi mana qopheessaa irraa walumaa galatti Birrii biiliyoona 1.59 walitti qabuu danda’uu isaanii ibsaniiru.

Raawwiin kun kan karoorfame caalaa ta’uu ibsuun, bara darbe bara 2014 waliin wal bira qabamee yoo ilaalamu birrii miiliyoona 600 ol caalma akka qabu ibsaniiru.

Milkaa’inni kun kan argame hojii cimaa qindoominaa fi duula qooda fudhattoota adda addaa waliin taasifameen ta’uu ibsaniiru.

Hojimaatni haaraan gargaarsa teeknooloojiin deeggarame jiraachuu fi madda galii dabalataa maddisiisuun akka hojjatame gabaasa kana keessatti ibsameera.

Dura taa’oonni fi miseensonni koreewwan dhaabbii mana maree naannichaa gabaasa kana dhaggeeffatan gaaffilee fi yaada adda addaa kaasaniiru.

Haaluma kanaan maallaqni galii karoora caalaa baay’ee ol’aanaa tahe walitti qabuu danda’e akka gaariitti akka mul’atu gaafateera.

Gama galii sassaabuutiin naannoo baadiyyaas qorachuun barbaachisaadha, magaalaa irraa kan hafe, maammila waliin haala sirrii fi gahumsa qabuun, akkasumas hojiiwwan fooyya’iinsaan hojjetaman waliin hojjechuuf xiyyeeffannoodhaan hojjechuun barbaachisaadha kanneen jedhuufi yaadonni gama hojimaata dhimmoota kanneeniin gaafatamaniiru.

Kaappitaalli gibira gurgurtaa gamoo cimsuuf maaltu hojjetamaa akka jiru koreen dhaabbii kaase.

Ogeeyyiin fi itti gaafatamaan Biirichaa gaaffilee mana keessaa ka’aniif deebii fi ibsa kan kennan yoo ta’u, itti gaafatamtamichi deebii gaaffilee ka’aniif kennaniin karoora isaanii qorannoon walqabate bu’uura godhachuun akka qopheesseefi gara karoorichaatiin, dandeettii naannichaatiin galii hangamii sassaabamuu akka danda’u adda baasuun akka qophaa’e ta’uu ibsameera.

Keessumaa lafa qonnaa fi oomisha qonnaa baadiyyaa irraa gibirri akka sassaabamu eeruun, gibira abbummaa lafaa waliin walqabatu sassaabuu irratti rakkoon akka jiruufi kanaaf gibira sirnaan kaffaluu irratti qormaanni akka jiru ibsaniiru.

Gama hojimaata badaa fi kiraasassaabdummaa ittisuutiin hojjettoonni mana hojicha keessatti hojimaata badaadhaaf saaxilaman lama hojiirraa ari’amuufi namoota biroo itti gaafatamummaa irraa kaasuu dabalatee tarkaanfiiwwan biroo fudhatamaniiru.

Itti quufinsa maamiltootaa guddisuuf tattaaffiin taasifamaa akka jiru Koree Dhaabbii Mana Marichaaf ibsaniiru.

Daldaltoonni seeraan ala hojjachaa turan 1129 koree naannichaa hanga aanaatti hundeessuun seeraan alummaa keessaa bahuun sirna seera qabeessaatti akka deeb’in gochuu ibsaniiru.

kanaan dura naannichatti gurgurtaa gamoo irraa gibirri sassaabamu akka hin jirre ibsuun bara kanas xiyyeeffannoo itti kenninee bu’aa gaarii galmeessisuu dandeenyeerra jedhan.

Dura teessuu koree dhaabbii baajataa fi faayinaansii Mana Maree Naannoo Hararii Aadde Ikraam Abdurahmaan galii naannichaa guddisuuf dandeettii qabnu hundaatti fayyadamuu qabna jedhan.

Dabalataan karoora baasuun qooda fudhattoota biroo waliin qindoomina cimsuun akka barbaachisu hubachiisaniiru.

Rakkoo walxaxaa lafa baadiyyaa hundeerraa hiikuuf hojii gaarii hojjetamaa jiru cimsuun akka barbaachisuullee hubachiisaniiru.

Hamzaa Yuusuf gabaase
28/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
79 viewsHarar Mass Media, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:51:32 የአረንጓዴ አሻራ የግብርና ስነ ምህዳርን በማስጠበቅ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ያነጋገርናቸው የግብርና ተመራማሪዎች ገለፁ፡፡
********
ያለንን የተፈጥሮ ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የግብርና ስነ ምህዳርን በማስጠበቅ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ያነጋገርናቸው የግብርና ተመራማሪዎች ገልፀዋል፡፡

የደን ፖሊሲን ተግባራዊ በማድረግ የአፈር መሸርሸር፣ የውሃ ብክነት፣ የአየር ንብረት መዛባት እና የዱር አራዊት ቁጥር መቀነስን ለመከላከል የአካባቢ ስነ ምህዳርን የሚያስጠብቅ ስራ ማካሄድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ተሰማ ቶሩ ገልፀዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻን የመሰሉ ስራዎች ከፍተኛ ጥቅም እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ተሰማ ገለፃ የለውጡ መንግስት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጀመረውን የችግኝ ተከላ እስከ ፅድቀት መንከባከብ መርሃ ግብር በቆራጥነት ከግብ ለማድረስ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ ተባባሪ መሆን እንደሚኖርበት እና መርሃ ግብሩም የግብርና ስነ ምህዳሩን ጠብቆ መከናወን ይኖርበታል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ሌላው በዩኒቨርሲቲ የግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አቶ ተፈራ ታደሰ እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የነገዋን ውቢቷን ኢትዮጵያ ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡


የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ብቻውን የታቀደውን እቅድ ሊያሳካ አይችልም ያሉት የግብርና ተመራማሪዎቹ ከእንከብካቤው ጋር በተገናኘም አትኩሮት ሊሰጠው እንደሚገባ የህብረተሰብ ተሳትፎ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርዐ-ግብር ሁለተኛው ዙር የችግኝ ተከላ ዘመቻ በያዝነው ሰኔ ወር ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ዘጋቢ ፡- አለም ገመቹ
28/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
76 viewsHarar Mass Media, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:51:32 ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በትላንትናው እለት ሀረር ከተማ ገቡ፡፡
********
በጎ ፍቃደኞቹ ወጣቶች ወደ ከተማው ሲገቡ የሀረሪ ክልል አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በትላንትናው እለት ሀረር ከተማ ገቡ፡፡

በአቀባበሉ ስነ ስርዓት ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የሀረሪ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት በጎ ፍቃደኞችን ወደ የፍቅር ፤የሰላም እና የመቻቻል እንዲሁም የአብሮ መኖር ተምሳሌት ወደሆነችው ሀረር ከተማ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል፡፡

ወጣቶቹም በከተማና እና በክልሉ በሚያደርጉት ቆይታቸው የህዝቡን የእንግዳ ተቀባይነት ተምሳሌትነትን ጨምሮ የጀጎል ግንብና የተለያዩ ቅርሶች እና ሙዚየሞች መገኛ መሆኗን ተዘዋውረው መመልከት እንዳለባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሀገራችን ያላትን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብቶቻችንን የህዝብ የአብሮ መኖር እሴቶችን በሚገባ በማወቅ በቀጣይ የሀገር ግንባታ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ እና የራሳቸውን አስተዋጾ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ ድንበር ተሻጋሪ የበጎ ፍቃድ ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በሰጡት አስተያየት ስለ ሀረር ስንሰማ የቆየነው የፍቅር የአንድነት እና የመቻቻል እንዲሁም የባለብዙ ታሪክ፣ ቅርሶች እና ሙዚየሞች ባለቤት የሆነችው ሀረር ከተማ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ የክልሉን ሀብቶችን ለማየት ተነሳሽነት የፈጠረባቸው መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ወጣቶቹ የተሰማሩበትን የበጎ ፍቃድ ስራ ሀገራቸውን የማያውቁትን አካባቢ እና ህዝብ አልፎም ብዙ ነገሮችን እንዲያውቁ እድል እንደተፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡

በተያዘው እቅድ መሰረት ወጣቶቹ ጀጎልን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙ የተለያዩ ቅርሶችን እንዲሁም የጅብ ማብላት ትርኢትን ጨምሮ ሌሎችን ጎብኝተዋል፡፡

ዘጋቢ መሀመድ ቶፊቅ
28/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
67 viewsHarar Mass Media, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:51:32 በ2015 አመት በ11 ወር ጊዜያት1.59 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የሀረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡
*******
የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2015 እቅድ አፈፃጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2015 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ገምግመዋል፡፡

አፈፃጸም ሪፖርቱን ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት የሀረሪ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ ሀላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ባለፉት 11 ወራት ከታክስ ካልሆኑ እና ከማዘጋጃ ቤት ገቢ ባጠቃላይ 1.59 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ክንውኑ ከእቅድ በላይ መሆኑን እና ከባለፈው አመት 2014 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ6 መቶ ሚሊየን ብር በላይ ብልጫ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይህ ስኬት ሊገኝ የቻለው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትጋር በቅንጅት እና በዘመቻ በተሰራ ጠንካራ ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አዳዲስ አሰራሮችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በመስራት እና ተጨማሪ የገቢ ምንጮች ማፍራት ላይ በስፋት መሰራቱ በሪፖርቱ ተገልፃል፡፡

ሪፖርቱን ያደመጡት የክልሉ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢ እና አካላት የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች አንስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከእቅድ በላይ ሰፊ ብልጫ ያለው ገቢ ሊሰበስብ የቻለው እቅዱ ሊያስቀምጥ ከሚገባው መጠን በሚገባ ታይቶ እንደነበር ጠይቀዋል፡፡

ገቢን ከመሰብሰብ አንፃር ከከተማ ባሻገር በገጠር አካባቢም መቃኘት እንደሚገባ፤ተገልጋይን በአግባቡ በተቀላጠፈ አሰራር ከማስተናገድ አኳያም በትኩረት መስራት እንደሚገባና ከነዚህ ጉዳዮች አንፃር ያሉ አሰራርን በማሻሻል የተካሄዱ ስራዎች ተጠይቀዋል፡፡

ካፒታል የህንፃ ሽያጭ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምን እየተሰራ እንዳለ ከቋሚ ኮሚቴው ተነስቷል፡፡

ከቤቱ ለተነሱት ጥያቄዎች የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ባለሞያዎች እና ሀላፊ ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የቢሮው ሀላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ለጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ከእቅድ ጋር ተያይዞ በጥናት ላይ ተመስርቶ እቅዳቸውን ያዘጋጀ መሆኑን እና ከክልሉ አቅም አንፃር ምን ያህል ገቢ መሰብሰብ እንደሚቻል በመለየት የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በገጠር አካባቢ በተለይ የእርሻ መሬት እና የግብርና ምርት ላይ ግብር የሚሰበሰብ መሆኑን ጠቁመው ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ ግብር ለመሰብሰብ ችግሮች ስላሉ በአግባቡ ግብር ለማስከፈል ተግዳሮቶች የሆነባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ብልሹ አሰራር እና ሙስናን ከመዋጋት አንፃር በቢሮው ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ ሁለት ሰራተኞች ከስራ እንዲባረሩ መደረጉን እና ሌሎች ላይ ከሀላፊነት መቀነስ ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎች መውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡

ተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አስረድተዋል፡፡

ህገወጦች ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡ ከክልሉ እስከ ወረዳ አሰራር በመዘርጋት ኮሚቴ በማቋቋም በተሰራ ዘመቻ ስራ በህገ ወጥ መልኩ ሲሰሩ የነበሩ 1129 ነጋዴዎች ህጋዊ እንዲሆኑ የተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

(ከህንፃ ሽያጭ) የሚሰበሰበው ግብር ቀደም ሲል በክልሉ ተግባራዊ ያልሆነ እና ዘንድሮ ትኩረት ሰጥተን በዚህ ላይ በመስራት መልካም ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢክራም አብዱራህማን የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አንፃር ያለንን አቅም ሁሉ ልንጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

በቀጣይም እቅድ አስፍተን ማቀድ አለብን ከሌሎች ባለድርሻ ጋር የቅንጅት ስራ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተለይ ከገጠር መሬት ጋር የሚታየው ውስብስብ ችግር ከመሰረቱ እንዲፈታ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ እና ባጠቃላይ እየተሰራ ያለው መልካም ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ዘጋቢ ሀምዛ ዩሱፍ
28/10/2015

Telegram https://t.me/hararimassmediaagency

YouTube https://www.youtube.com/channel/UCA5BjF_8thxJUNUriIji2fA6

Facebook https://www.facebook.com/mediaharari
86 viewsHarar Mass Media, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ