Get Mystery Box with random crypto!

🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨

የቴሌግራም ቻናል አርማ haniya_calligraphy — 🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨 H
የቴሌግራም ቻናል አርማ haniya_calligraphy — 🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨
የሰርጥ አድራሻ: @haniya_calligraphy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.59K
የሰርጥ መግለጫ

ውድና ተወዳጅ ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ብዙ ነገሮችን እናገኛለን የ calligraphy ጥበቦች ያልተነበቡ አዳዲስ ታሪኮች ያገኛሉ ቀለል ያሉና አስተማሪ video ወ.ዘ.ተ
ለማንኛውም አስተያየት @hanuni_calligraphy_bot
የመወያያ ግሩፕ @hanan_calligraphy
እንዲሁም Instagram ላይ @Hanuni_h123follow በማድረግ አባልነታችሁን አሳዩን

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 17:40:51 አንዳንድ ሰው እየተበደለ ችሎ ሚኖረው
አፀፋውን መመለስ አቅቶት ሳይሆን
አስተሳሰቡ ከበዳዩ ስለ ሚሻል ነው ።
      መልካም  ቀን

SEmir ami
221 viewsSemir ايمي سمير, 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 13:17:24 የሰው ጣፋጭ ቃላቶች ብቻ አትመኑ
አፉ ማር ልቡ መርዝ የሆነ ብዙ ሰው አለ!
350 viewsSemir ايمي سمير, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:53:46 ሱኒዮች(ሰለፊዮች) ነን የሚሉ ግን ሱኒዮች(ሰለፊዮች) ያልሆኑ!!!!!!
ينتسبون إلى السلفية وهي منهم براء!!
قال الشيخ/ سليمان الرحيلي وفقه الله:
وفي هذا العصر في بعض بلدان المسلمين يوجد أفراد ينتسبون إلى السلفية وهم من أهل البدع والأهواء، فهؤلاء شوّهوا السلفية؛ لأنهم ينتسبون إليها وهي منهم براء؛ لأن ظاهرهم يكذب دعواهم وانتسابهم، فهؤلاء يُبيَّن كذب كلامهم في الانتساب إلى هذا الاسم الشريف.
شرح فضل الإسلام صـ ١٧٤
ባለንበት በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ሙስሊም ሀገራት የሚገኙ አንዳንድ ሙስሊሞች ሰለፊዮች ነን የሚሉና ራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉ ነገር ግን የለየላቸው ቢዳዓ አራማጆችና ስሜታቸውን ፍላጎታቸውንና ዝንባሌያቸውን የሚራምዱ ናቸው እንደነዚህ አይነት ስብስቦችና ግለሰቦች ናቸው ሰለፊያን የሚበረዙና የሚቀይሩ ምክንያቱም ሰለፊዮች ነን ይላሉ ይሁንና የሰለፊያ ሚንሀጅ ከእነሱ ጋር አንዳች ግንኙነት የለውም።
ሸርሁ ፈድሊልኢስላም(174)
قال ابن سهل بن عبد الله 《عليكم بالاثر والسنة فاءني أخاف أنه سيأتي عن قليل زمان إذا ذكر إنسان النبي والإقتداء به في جميع إحواله ذموه،ونفروا عنه وتبرأوا منه، وأذلوه وأهانوه.
فتح المجيد(26)
ሳህል ኢብኑ ዐብዲላህ አላህ ይዘንላቸውና
《 የነብዩን صلى الله عليه وسلم ሱናንና ፈለጋቸውን በሚገባ በማወቅና አጥብቆ በመያዝ ላይ አደራችሁን ከትንሽ ግዜ በወኀላ ስለ ነብዩን ሱናና ሱናቸውን ስለመያዝና ስለመከተል እንዲሁም የነብዩን ሱና በትክክለኛው አቅጣጫ በመተግበር ላይ የሚያዝና የሚያወሳ ሰው የሚወቀስበት፣የሚዋረድበት፣ሰዎች ከእሱ የሚሸሹበትና ሌሎችም ከእሱ እንዲሸሹ የሚያደርጉበት ወቅት ይመጣልና።》ብለዋል

ፈትሁንመጂድ(26)
1.2K viewsibro smile , 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:53:39 {أَلا بِذِكرِ اللَّهِ تَطمَئِنُّ القُلوبُ}

ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላሁ እንዲህ ይላሉ፦

“እንደ ኢብኑ ተይሚያ ዚክር የሚያበዛ አላየሁም፡፡ በአንድ ወቅት ፈጅር ከሰገደ ጀምሮ ዚክር ያረጋል፡፡

ባለበት ሁኔታ ላይ እያለ ሰዐቱ በጣም ሄደ፣ ረፈደ

በሁኔታው ተገርሜ እያየሁት ነው፡፡ እንደተገረምኩ ገብቶታል፡፡

ዘወር ብሎ እንዲህ አለኝ፡- “ይሄ ቀለቤ ነው፡፡ እሱን ካላገኘሁ ብርታት አይኖረኝም።

አላህ ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን ኣሚን ፡፡

ሱብሃና ረቢ
819 viewsibro smile , 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:53:30 ሲጋራ ማጨስ ክልክል ነው።


ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

«ሲጋራ ማጨስ ሀራም "የተከለከለ ተግባር" ነው። በውስጡ ብዙ ጉዳቶች ይገኙበታልና። ሁሉም አይነቱ የተከለከለ ነው። ሙስሊም የሆነ አካል ሊተወው፣ ሊርቀውና ከአጫሾች መራቅ (ከነሱ ጋር አለመቀማመጥ) ግዴታው ይሆናል።»

مجموع فتاوى ومقالات الشيخ ابن باز 23/49

ሌሎችም ከሲጋራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገሮች ለምሳሌ ትንባሆ መንፋት፣ ሽሻ ማጨስ፣ አሽሽ መውሰድና በከንፈር ስር የሚደረገውም ባጠቃላይ የተከለከሉ ናቸው።

752 viewsibro smile , 14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 20:52:11
762 viewsĤĄŊÏŸª, 17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:39:59 መህሬ "ተውሒድ" ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ሳቢት ኢብኑ አነስ እንዲህ አሉ፡-
አቡ ጦልሓ የተባለ ሰው ኡሙ ሱለይምን የትዳር ጥያቄ ያቀርብላታል ፡

ከዚያ ኡሙ ሱለይም እንዲህ ብላ መለሰችለት ፡

☞ " አንተ አቡ ጦልሓ ሆይ ! (ወላሂ) በአላህ ስም ይሁንብኝ የአንተ አይነት ሰው ለትዳር ጠይቆ እምቢ የምትባልና የምትመለስ ሰው አልነበርክም " ነገር ግን አንተ ካፊር/ካሃዲ ነህ ፡ እኔ ደግሞ ሙስሊም ሴት ነኝ ፡ እኔ አንተን ማግባት አልተፈቀደልኝም ፡ ከሰለምክ እሱ ነው መህሬ ከዚያ ውጭ ምንም አይነትን መህር አልፈልግም ፡
ከዚያም አቡ ጦልሓ ሰለመና ተጋቡ መህሯም ይሄው ሆነ ። አላህ አክበር

በሌላም
የኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) መህሯ ምን ነበር?!
አነስ _ረዲየላሁ ዐንሁ _ እንዲህ ይላሉ፦
"አቡ ጠልሓ ኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) ለማግባት የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ።
ኡሙ ሱለይም፦ "አንተ የምትገዛው ጣኦት እነ እገሌ… የሚባሉ ጎሳዎች መንደር ሐበሻዊ ሰው ከእንጨት እንጠረበው አታውቅምን?"ስትል ጥያቄ አቀረበችለት።
አቡጠልሓም፦"አዎን።ጠንቅቄ አውቃለሁ።"ሲል ምላሹን ሰጣት ።
ኡሙ ሱለይም፦"ታዲያ ሐበሺያዊው ሰው ከእንጨት የጠረበውን ጣኦት ስታመልክ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን?!!"አለችው።
በመቀጠልም፦
"እስልምናን ከተቀበልክ ከሱ ውጭ ሌላ ሰዳቅ ፣ጥሎሽ የምጠይቅህ ነገር አይኖርም።"
አቡጠልሐ፦"እስኪ የማስተውለበትና ከራሴ ጋር የምነጋገርበት ጥቂት ቀናትን ስጪኝ።"ብሏት
ወደ ቤቱ አቀና ብዙም ሳይቆይ ወደርሷ ተመለሰና፦
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ፣ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉላህ"በማለት እስልምናን መቀበሉን ከፊትለፊቷ አበሰራት።
ከዚያም፦

ኡሙ ሱለይም፦"አንተ አነስ ሆይ! ወልይ(ሐላፊ)ሆነህ ከአቡ ጠልሐ ኒካሁን ተቀበል።"አለችኝ።"
ሣቢት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም የላቀ እና ውድ መህር የተሰጣት ሴት ሰምተን አናውቅም፣ምክንያቱም የርሷ መህር አቡ ጠልሐ ኢስላምን መቀበሉ ነበርና።"
【ሲፈቱ ሰፍዋ"(2/247)】
760 viewsibro smile , 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:39:44 አምላኬ ሆይ!

በሰዎች መካከል አቆምከኝ፣ ወዳንተ እንዳመላክትም ዕድል ሠጠኸኝ፣ እኔም ስላንተ ተናገርኩ፤ ስለታላቅነትህም መሰከርኩ።  ሰዎችም በመልዕክትህ ላይ ታማኝ እንደሆንኩ አሰቡኝ፣ አምነውኝም ወደኔ ቀረቡ፣ እኔ ራሴን የማውቅ፣ በራሴ የኢማን ሁኔታም የማፍር ሆኜ ሳለሁ ከኔ ብዙ ነገር ጠበቁ።
ኢላሂ ...ከአሳሳቾች አታድርገኝ፤ በምላስ ወዳንተ  ከሚጠሩት በተግባር ግን ከዲን ከሚያርቁት አታድርገን፤  ለሌሎች መካሪ ራሴን ግን ዘንጊ አታድርገኝ።

ሰዎች ከሚያስቡኝ በላይ አድርገኝ። ከዕለት ወደ ዕለትም ብርታትና ፅናቱን ስጠኝ።
ጥሩ ሙስሊምና ጎበዝ አማኝ አድርገህ ግደለኝ። ከደጋጎች ጋርም ቀስቅሰኝ።
625 viewsibro smile , 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:39:39 አንዳንዴ
,....
ዝም ብሎ አንዳንዴ
ዝም ብዬ አስባለሁ
አብሰለስላለሁ
ከራሴ አወራለሁ
በሀሳብ እሄዳለሁ
ምን እሆን! እላለሁ
እጨናነቃለሁ
ተስፋም አደርጋለሁ …
……
የደረሰ ለታ የዚያ ሞት ቀጠሮ
ጌታዬ ሲጠራኝ ተራህ ደርሷል ብሎ
አውጥቶ ሲጥለኝ አንጀቱ ጨክኖ
ወገን ሲጨምረኝ ከጉድጓድ ቆፍሮ
አፈር ሲቆልሉ ድንጋይ ሲጭኑብኝ
ለናኪር ለሙንከር ብቻዬን ሲተዉኝ
ትተውኝ ሲሄዱ በነበር ተሣፍሮ
እላመደው ይሆን ያንን ከባድ ኑሮ!!
…..
ምን ይሆን ፈንታዬ ምን ይሆን ዕድሌ!
ጀነት ወይስ እሣት መግቢያ መቃብሬ?
ጠባብ ወይስ ሰፊ ጥቁሩ ማረፊያዬ?
ብርሃን ወይስ ፅልመት የብቻ ጓዳዬ?
ታየኝ በሀሳቤ ያ መጪዉ ሁናቴ
ሥጋዬ ፈራርሦ ስቀር በአጥንቴ
አጥንቴ አፈር ሲሆን ሲደቅ ሰውነቴ
ይመች ይሆን በርግጥ ሁለተኛው ቤቴ!!
……
እየቀረብኩ ነው ሳልወድ በግዴ
ጥርጥር የለውም እውን ነው መሄዴ
ቢደላኝ ባይደላኝ ጎጆዬን ልረከብ
ባሳለፍኩት ሁሉ አምላኬ ፊት ልቀርብ
……
የዱንያ ሁካታ ሩጫና ዉዥንብር
አስረስቶኝ እኔን የአኺራን ነገር
ጉራዬን ስጎርር ወሬዬን ስነዛ
ጊዜዬን ጨረስኩት በዋዛ ፋዛዛ

ወይ አለማወቄ ከንቱ ቢስ ልፋቴ
ብርሃን በእጄ የለኝ ለመሬት ሥር ቤቴ
ስንቅ አላሰናዳሁ ለረጅም መንገዴ
ትርፍ ሥራ የለኝ ኪሣራ ነው ንግዴ
….
አትጣለኝ ያ ረቢ አትራቀኝ በረሕመት
ምን አለኝና ካለአንተ እዝነት
የፊትናዋን አገር ዱንያን ለቅቄ
በስንብት ስሄድ ዘመድ ወዳጅ ርቄ
ኮንትራት ጨርሼ አልቆ ቆይታዬ
እንደ ሌሎች ሁሉ እኔም በተራዬ
ነጥለው ሲወስዱኝ ከሀብት ንብረቴ
በአንዲት አቡጀዲ ሲያስወጡኝ ከቤቴ
አጥበው ሲከፍኑኝ ለረጅም ጉዞዬ
ቀብር የገባሁ ለታ ጀናዛ ተብዬ

afdel
680 viewsibro smile , 08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:58:52
990 viewsĤĄŊÏŸª, 11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ