Get Mystery Box with random crypto!

ኡለማ ቢናገር እሚሰማው ጠፋ ማን ሰምቶ ማን ተናግሮ ኪታብም ተረፋ ሰው ሚበሳጨው እሚቆረቁረው ዱንያ | Hanan Alhadra💚

ኡለማ ቢናገር እሚሰማው ጠፋ
ማን ሰምቶ ማን ተናግሮ ኪታብም ተረፋ
ሰው ሚበሳጨው እሚቆረቁረው
ዱንያ ሲያጣ ሆነ ገንዘብ ሲቸግረው
ሰው ይበሳጫል ዱንያ በማጣቱ
ይኖር መሰለው ወይ ዘላለም ሀያቱን
ለዱንያው ለዲኑ ሰው ካልተባበረ
ሙዕሚን ተገናኝቶ ካልተመካከረ
ሴት ወንዱ በኢማን ቀልቡ ካልሰበረ
ዱንያውስ ኡክራውስ መቼ ተደፈረ..

ሁሉም ከአንገት በላይ እየተወሻሸ
የወንድሙ ሁላ አይሽ ተበላሸ
አንዱ ለአንዱ ማዘን የለውም መስማማት
ኡምራችን አለቀ በመተማማት....