Get Mystery Box with random crypto!

Oh' allah ወላሂ ኢላሂ ድንቅ ነው!! ቦዶ ሆኜ አውቃለሁ! ሰው ሞቶብኝም ያውቃል ተበ | Hanan Alhadra💚

Oh' allah

ወላሂ ኢላሂ ድንቅ ነው!!

ቦዶ ሆኜ አውቃለሁ! ሰው ሞቶብኝም ያውቃል
ተበድዬ ከሰው ተገልዬ ብቻዬን አንብቼ የሆዴን በሆዴ አሳልፌም አውቃለሁ
እኔ ለእኔ ብቻ የቀረሁ እስኪመስለኝ እራሴን በራሴ ሞቴን ልሸልመው ገዳይ በሌለበት ታግዬም አውቃለሁ

በዚህ ሁሉ መሀል ድንገት አጎንብሼ.....
ቀና ስል.. ኢላሂ መልስ አለው።

በቃ ሁሉን አስረስቶ
ቀልቤን አረጣጥቦ
እምባዬን ጠራርጎ
የሌለኝን ማዕረግ መልሶ ይሰጠኛል


ታድያ ለዚህ ሁሉ መልስ ምን ይሆነኛል?

ወላሂ ኢላሂ ድንቅ ነውው!!!!!

Https://t.me/hanan_Islamic_paje