Get Mystery Box with random crypto!

ወንዶች ወንዶች አንዴ እንዳታሳልፉት ማግባት ያለብህ ይችን ነው!! ኢንሻአላህ ትጠቀሙበታላችሁ መል | Hanan Alhadra💚

ወንዶች ወንዶች አንዴ እንዳታሳልፉት ማግባት ያለብህ ይችን ነው!! ኢንሻአላህ ትጠቀሙበታላችሁ

መልካም የሆነች ሴት የማግባት ትሩፋት!!

አብዛኛው ወንድ ምን አይነት ሴት ማግባት እንዳለበት እራሱ አያውቅም

አብዛኛችን ምናውቀው አንድ ሀዲስ አለ!!

ረሱላችን አለይሂ ሰላም እንዲህ ይላሉ፦

አንድ ሴት ምትገባው ለ4 ነው
1 ለገንዘቧ
2ለዘመዶቿ
3ለውበትዋ እና
4ለዲንዋም ሲባል ትገባለች ይላሉ።

በመጨረሻም ማስጠንቀቂያ ሲያስቀምጡ፦
#የዲን ባለቤት የሆነችውን ምረጣት
"እጅህ አፈር ይዝገንና" ይህም ማለት ምንም ያክል ደሀ ብትሆን ያቺን ልትመርጣት ይገባል ለማለት ነው!


ነብያችን ሰዐወ የትኛዋ ሴት ናት የተሻለች ተብለው ሲጠየቁ??
እንዲህ ብለው መለሱ፦
-በሚመለከታት ሰአት ምታስደስተው
-በሚያዛት ሰአት ደግሞ እሺ መርሃባ ብላ ምትነሳ ናት
-እሱ በሚጠላው ነገር ላይ ተቃራኒ ሆና ማትመጣ"
በማለት መለሱ

በሌላ ሀዲስ ደግሞ

ሶስት ነገሮች ከመገጠም ውስጥ ናቸው
ሶስት ነገሮች ደግሞ ከእድለቢስነት ውስጥ ይቆጠራሉ ይላሉ

ከመገጠም ውስጥ ካሉት እኮ ፦

መልካም የሆነች ሴት ናት ይላሉ
ስትመለከታት ምታስደንቅህ
ምትታመንልህ
እምነት ጥለህባት የትም ምትሄድ በማለት ይገልፃሉ


እና አህባቢ ለሁላችንም ከኛ የተሻለ አላህ ለኛ ያውቃል እና በዱንያም በአኺራም ምንደሰትበትን ዘውጅ አላህ ይወፍቀን!

አሚንን!!

ለምትወዱት ወጃጅ ጓደኛ ዘመድ ሼር ያድርጉ!!

የኢማን ግማሹ በትዳር ነው እና ኢማናቹን ሙሉ ገና ሚባል ነገር የለም!!

t.me/hanan_Islamic_paje