Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለቋሚ ሲኖዶስ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀሩ! | የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለቋሚ ሲኖዶስ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀሩ!

በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ቋሚ ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ጋር ዛሬ ጥር 25/2014 ዓ.ም ሊያከናውነው የነበረው ውይይት ከንቲባዋ በጠየቁት የውይይት ቦታ ለውጥ ምክንያት ሳይደረግ ቀርቷል።

ቋሚ ሲኖዶሱ መንበረ ፓትርያርክ ውስጥ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ውይይቱን ለማድረግ እየተጠባበቀ የነበረ ቢሆንም ከንቲባዋ ቦታው ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ይቀየር በማለታቸው ምክንያት ውይይቱን ለማድረግ እንዳልተቻለ ታውቋል።

ከ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር የሚኖራቸውን ውይይት ወደ መንበረ ፓትርያርክ በመመጣት ሲያከናውኑ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን የዛሬው የከንቲባዋ ድርጊት ሊቃነ ጳጳሳትን ያሳዘነ ደርጊት ሆኗል።

ምንም እንኳን ከንቲባዋ በውይይቱ ላይ ባይገኙም ቋሚ ሲኖዶሱ ግን ስብሰባውን እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን እኛም ጉዳዩን እየተከታተልን አስፈላጊውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።