2022-06-14 19:17:54
ተውሒድ የ2ት ሀገር የስኬት ቁልፍ
#ክፍል 11
#6:-
"ቅድሜያ ለተውሒድ" እንላለን ምክንያቱም #ተውሒድ ከትዕዛዝ ሁሉ በላጭ ነውና
የተውሒድን ታላቅነት ከሚያሳዩ ጠቋሚዎች ውስጥ አንዱ ነብዩ.:
.:
.:
(صلىالله عليه وسلم)
እንዲህ ማለታቸው ነው፡-
[{ኑህ ሊሞቱ ሲሉ ለልጃቸው "በላኢላሀኢለላህ አዘሀለሁ፡፡ 7ቱ ሠማያትና 7ቱ መሬቶች በአንዱ የሚዛን ክፍል ላይ ቢቀመጡ፡ #ላኢላሀኢለላህ ደግሞ በሌላኛው የሚዛኑ ክፍል ላይ ብትቀመጥ፡ #ላኢላሀኢለላህ በነሱ ላይ ሚዛን ትደፋ ነበር፡፡}]
[ሸይኹልአልባኒይ "ሶሒሕ" ብለውታል፡፡ [ተሕቂቅ ከሊመቲልኢኽላስ፡57]
"የሀይማኖት መሠረቱ #በመልካም ማዘዝና #ከመጥፎ መከልከል ነው፡፡ #የመልካም ሁሉ ቁንጮ #ተውሒድ ነው፡፡ #የመጥፎ ሁሉ ቁንጮ #ሺርክ ነው፡፡" [አለፈታዋ፡ 27/442]
ስለሆነም #ኢስላማዊ ህግጋትና ተግባራት በሙሉ #ከትልቅ እስከ #ትንሽ #የተውሒድ ቅርንጫፎች ናቸው፡፡ ዋናው ግንዱ #ተውሒድ ነው፡፡ ይህን አስመልክተው ኢብኑልቀይዪም ረህ እንዲህ ይላሉ:-
"#ኢኽላስና #ተውሒድ በልብ ውስጥ የሚበቅሉ #ዛፎች ናቸው፡፡ መልካም ተግባራት ቅርንጫፎቻቸው ሲሆኑ #ፍሬዎቻቸው ደግሞ በዱንያ #ጣፋጭ ሂወት ሲሆን በአኼራ ደግሞ ዘውታሪ #ፀጋ ነው፡፡ #የጀነት ፍሬዎች የማይቋረጡና የማይከለከሉ እንደሆኑት ሁሉ #የተውሒድ እና #የኢኽላስ ፍሬም በዱንያ እንዲሁ ነው፡፡
#ሽርክ፡ #ውሸት:ና #ይዩልኝም እንዲሁ በልብ ውስጥ በልብ ውስጥ የሚበቅሉ #ዛፎች ናቸው፡፡ የዱንያ ፍሬያቸው #ፍርሀት፡ #ሀሳብ፡ #ጭንቀት፡ #የደረት መጠበብ፡ እንዲሁም #የልብ ፅልመት ነው፡፡ #የአኼራ #ፍሬያቸው ደግሞ #አዝዙቁም እና ዘውታሪ የሆነ ቅጣት ነው፡፡ [አልፈዋኢድ፡ 200]
(አዝዘቁም ከጀሀነም አዘቅት ስር የምትወጣ አመፀኞች በመመገብ #የሚሰቃዩባት አስፈራሪና አሰቃቂ #ዛፍ ነች፡፡
{አስሷፋት፡ 62-66; አድዱኻን፡ 43-46}
#7:-
"ቅድሜያ ለተውሒድ" እንላለን ምክንያቱም #ያለተውሒድ በጎ ስራ ሁሉ ከንቱ ነውና
እርግጥ ነው
#ሶላት የኢስላም ምሰሶ ነው፡፡ ሶላት የሌለው በእስልምና ምንም ድርሻ የለውም፡፡
#ሰደቃ ፈተናን የሚመክት ሁነኛ ጋሻ ነው፡፡
#ሐጅ የወንጀል ሸክምን አራግፎ ንፅሕናን የሚያላብስ ልዩ #የፈጣሪ ፀጋ ነው፡፡
#ትዕግስት ሰፊ የአላህ ችሮታ ነው፡፡
#መልካም ስነምግባር ከቂያማ የሚዛን ጭንቅ የሚያተርፍ ልዩ #ስብእና ነው፡፡
#ትዳር ሀሳብን የሚሰበስብ #ልብን የሚያረጋጋ #የኢማን ግማሽ ነው፡፡
#ዚክር የልብ ህይወትን የሚሰጥ ከልብ ድርቀት የሚከላከል ፍቱን #መድሐኒት ነው፡፡
ሌላም ሌላም ብዙ መዘርዘር ብዙ ማለት ይቻላል፡፡
ግና ይሄ ሁሉ ዋጋ የሚኖረው መሠረቱ ሲስተካከል #ተውሒድ ሲያምር ብቻ ነው፡፡
#ተውሒድ በሌለበት #ሶላቱ፡ #ፆሙ፡ #ዘካው፡ #ሐጁ፡ #ዚክሩ፡ #መልካም ስነምግባሩ፡ #ትዕግስት፡ #ዝምድና፡ መቀጠሉ፡ ,,,,,,
ባጠቃላይ መልካም የሚባል ሁሉ #ከራብ አያስጥልም፡ #ከጥም አያድንም፡፡
ምክንያቱ እጅግ ግልፅ ነው፡ ተውሒድ በሌለበት ሁሉም ዋጋ ቢስ ስለሆነ ነው፡፡ አዎ ያለ #ተውሒድ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡
የፈለገ #በጎ ቢሰራ፡ የፈለገ #ከወንጀል ቢረቅ #ተውሒድ ከሌለ #ባዶ ነው፡፡
#ዉሀ ወቀጣ፡፡
ኢብኑተይሚያህ ረህ
""ተውሒድ ተበላሽቶ ከነዚህ ወንጀሎች ነፃ ከመሆን ይልቅ #ተውሒድ ጤነኛ ሆኖ እነዚህ ወንጀሎች ቢኖሩ የተሻለ ነው፡፡""[አልኢስቲቃማህ፡1/466]
ስለዚህ ሌሊቱን #በሶላት ቀኑን በፆም ብናሳልፍ፡
#ዘካን በአግባቡ ብንከፍል፡ከግዴታውም አሳልፈን,,,,
በየ አመቱ #ለሐጅ ብንመላለስ፡
#ተውሒድ ከሌለ፡ መሠረቱ ካልተሰተካከለ ከንቱ ልፋት ነው፡፡
አልአስ ኢብኑ ዋኢል
በጃሂልያ 100 ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር፡፡
#ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ #ልጁ ሂሻም የድርሻውን 50 ግመል አረደ፡፡
ሌላኛው ልጅ #ዓምር ግን የአላህ መልዕክተኛ.:
.:
.:
(صلىالله عليه وسلم)
ስለ ጉዳዩ ሲጠይቅ
[{አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ #ብትፆምለት: #ብትሰድቅለት፡ ይጠቅመው ነበር}]፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 1/180}
ይሄ የነብዩ .:
.:
.:
(صلىالله عليه وسلم)
ንግግር የተውሒድን ምንነት፡ መስፈርቱንና፡ አፍራሹን ለይቶ ለማያውቅ ሁሉ አስደንጋጭ #ደወል ነው፡፡
#ሰሚ ጆሮ; #አስተዋይ ልቦና ካለ፡፡
#ጌታችን አላህ በሱረቱል አንዓም 18
ነብያቱን ዘርዝሮ ካደነቀ በኀላ እንዲህ ይላል:-----
(ቢያጋሩ ኖሮ ይሰሩት የነበረው በርግጥ በተበላሸ ነበር!!) {አንዓም፡ 88}
ክፍል 12 ይቀጥላል
152 views𝐒𝐮𝐡𝐚𝐢𝐛 𝐚𝐥_𝐰𝐞𝐝𝐮𝐝, 16:17