Get Mystery Box with random crypto!

የአላህን መቼ ጠየቅኩሽ?? አንድ ጓደኛችን ነውኮ ( አላህ ይጠብቀውና ) የሆነ ሰርግ ላ | ሀላል ፈገግታ 😂

የአላህን መቼ ጠየቅኩሽ??

አንድ ጓደኛችን ነውኮ ( አላህ ይጠብቀውና ) የሆነ ሰርግ ላይ አጃቢ ሆኖ ይታደማል ፣ መንዙማ እየተባለ አይኑ ከአንዷ አጃቢት ላይ ይወድቃል ፣ ሳያስበውም ልቡንም እዛው ጣለው ( አብሽሩ ይገጥማል አትደንግጡ ) ።

እናማ ...በባህሪው የተሰማውን ፊት ለፊት ሚናገር ነበርና ምንም ሳያንገራግር ልጅቱ ጋ ጠጋ ብሎ ..

" ለአላህ ብዬ ወድሻለሁ! " አላት ።

ልጅትም የተለመደውን መልስ ..
" አላህ ይወደድህ! " አለችው ።

ታድያ ይህ ያልተዋጠለት ጓደኛችን ..

" የአላህን መች ጠየቅኩሽ ፣ የአንቺን ንገሪኝ ! " ብሏት እርፍ ።
ኡመር ያሲን

@muslims_couple || ፍቅር ሰባኪ TemUd