Get Mystery Box with random crypto!

እርሶ ፣ ቤተሰቦ ወይንም ደግሞ እሚያቁት ወዳጅ ዘመዶ የአይን ህክምና ቦታ ሄደዉ የአይን መድረቅ አ | Hakim @ሐኪም

እርሶ ፣ ቤተሰቦ ወይንም ደግሞ እሚያቁት ወዳጅ ዘመዶ የአይን ህክምና ቦታ ሄደዉ የአይን መድረቅ አለብዎ ፤ ይህንና ያንን ያድርጉ ተብለዉ ይሆናል።

ለመሆኑ የአይን መድረቅ ምንድነው? በምንስ ይመጣል? መከላከያዉና ህክምናዉስ ምንድነዉ? ስለሚሉት ነገሮች በትንሹ ጀባ እንበላችሁ።

ከሳይንሳዊ ትርጓሜዉ ስንነሳ የአይን መደረቅ ማለት እንባችን በተገቢው መጠንና ስሪት አለመመንጨት ወይንም ደግሞ ከመነጨ በኋላ የዉጨኛው የአይን ክፍላችንን አረስርሶ ተረጋግቶ አለመቆይትና እነዚህን ተከትሎ እሚፈጠር የአይን ምቾት ማጣት ፣ የእይታ መረበሽና የዉጨኛዉ የአይን ሽፋን መቁሰልን ያካተተ የአይን ህመም ነዉ።

ስንት አይነት የአይን መደረቅ አለ?
በአጠቃላይ ስንመለከት ሁለት አይነቶች ሲኖሩን

1. ዉሀማዉ የእንባችን ክፍል በተገቢዉ መጠን አለመመንጨት እና
2. እንባችን ከሚገባው መጠን በላይ መትነን
3. ከላይ ያሉት የሁለቱን ያጣመረ**

ምልክቶቹ ምንድን ናቸዉ?
አይናችን
* ምቾት ማጣት፣ የመቆጥቆጥና የማቃጠል ስሜት
* መቅላት
* መቆርቆር
* ብርሀን መፍራት
* የእይታ መደብዘዝና መዳከም
* ከተገቢዉ በላይ ቶሎ ቶሎ መጨፈንና ማልቀስ
* Mucus ያዘለ ፍሳሽ የአይናችን ጥግ ላይ መኖር

ምክንያቶቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

* በተለያዩ ምክንያቶች የእንባ እጢ ላይ በሚደረስ ጉዳት ሳቢያ የሚመነጭ የእንባ መጠን መቀነስ
* የእንባ እጢዎች እንባ ማስተላለፊያ ትቧዎች መዘጋት
* Sjogren syndrome

* የነርቯች በተገቢዉ ሁናቴ አለመስራት (refex block due to contact lens wear, laser eye surgery or trauma to the nerve itself)

* ለተለያዩ ህመሞች እመንወስዳቸዉ መድሀኒቶች (systemic medication) (antihistamines, decongestant, hormon replacement therapy, antidepressant....)

* ለእንባችን መሸፈኛ እሚያገለግለውን ዘይታማ ክፍል እሚያመነጩ እጢዎች መዘጋትና እሚያመነጩት መጠን መቀነስ
* የአይን ቆብ ችግሮችና ዝቅተኛ የሆነ የመጨፈን መጠን

* የVitamin A እጥረት
* ለረጅም ገዜ ማቆያ ኬሚካል(preservative) ያላቸዉ ጠብታዎች
* Contact lens ማድረግ

ከነዚህ ምክንያቶች በተጨማሪነት የአካባቢዎ ሁኔታ እሚያደርሰዉ ተፅዕኖም አለ። እንደምሳሌ
* ለረጅም ሰዓት ማንበብ እና መኪና ማሽከርከር
* ንፋሳማና ዝቅተኛ እርጥበት አዘል የአይር ሁኔታ
* እርጅና
* ሲጃራ ማጤስ ወይንም እሚያጤስ ሰው አካባቢዮ ላይ መኖር... እንደምክንያት ይጠቀሳሉ።

መቼ ሀኪሞትን ያማክሩ?

ከላይ የተገለፁት ምልክቶች ካለዎት አቅራቢያዎ ወዳለ የአይን ህክምና አገልግሎት ሰጪ ክፍል በመሄድ አይንዎን ቢታዩ ይመከራል።

ህክምናው ምንድን ነዉ?

የአይን መድረቅ ህክምና ታካሚዎች እንዳሉበት የበሽታዉ ደረጃ እሚወሰን ሲሆን በአጣቃላይ ግን ህክምናው ቀጥሎ ያሉትን ነገሮች ያጠቃልላል

1. ታካሚዎችን ስለበሽታዉ ባህሪ ፣ ዘላቂነት (chronic) ና ማድረግ ስለሚገበቸዉ ጥንቃቄ ማስተማር

2. የእንባ እጢዎች እንባ እንዲመነጩ ማበረታታት፣ መተካትና ማቆየት

3. የአይን መቁሰልን መቆጣጠርና ማከም
4. የአይን ቆብ ችግሮችን ተገቢዉን ህክምና መስጠት

ታካሚዎች ማድረግ ያለባቸዉ ጥንቃቄ

* እየወሰዱ ያሉትን ማንኛዉንም መድሀኒቶች ለአይን ሀኪሞ ያሳዩ
* ሲጃራ እሚያጤሱ ከሆነ ያቁሙ
* ኮምፒውተር ና ስልክ ሲጠቀሙ የብርሀን መጠኑን ይቀንሱ
* በሚያነቡበት ጊዜ በየመሀሉ እረፍት ይውሰዱ
* ሲያነቡ ፣ ኮምፒውተር ና ስልክ ሲጠቀሙ ቶሎ ቶሎ መጨፈኖን አይዘንጉ
* አካባቢዎት ደረቅ እና ንፋሳማ ከሆን መቀየርን ያስቡ።

ከሚያባብሱ ነገሮች ለምሳሌ ceiling fan ካለ ያስወግዱ።
* ከቤት ዉጪ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መነፀር መጠቀምን ይልመዱ
* የአይኖትን ንፁህና መጠበቅ ፈፅሞ አይዘንጉ።

ዶ/ር በእምነት ተረዳ ፤ የአይን ህክምና ስፔሻሊስት

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena