Get Mystery Box with random crypto!

Hahu Motivation

የቴሌግራም ቻናል አርማ hahumotivation — Hahu Motivation H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hahumotivation — Hahu Motivation
የሰርጥ አድራሻ: @hahumotivation
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 32.08K

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 10:09:40 መላውን ዓለም ከመጨበጥ ይልቅ ራስን መጨበጥ የተሻለ ነው

ምንጭ ፦ ህያውነት ፫ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ
ተስፋሁን ምትኩ

ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው - እንደ አንድ እምቅ አቅም፡፡ ሲወለድ ልከኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ልዩ ነው - ምክንያቱም በመላው ህልውና ውስጥ ሰው ብቻ ነው አንድ አቅም ሆኖ የሚወለደው፤ ሌሎች እንስሳት ልከኛ ሆነው ነው የሚወለዱት፡፡

አንድ ውሻ ሲወለድ ውሻ ሆኖ ነውና መላ ህይወቱንም እንዲያ ሆኖ ይኖራል። አንድ አንበሳ ሲወለድ አንበሳ ሆኖ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ ግን ሰው ሆኖ አይደለም፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው። ሰው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ሰው የወደፊት ተስፋ አለው! ሌሎች እንስሳት ግን ተስፋ የላቸውም፡፡ ሁሉም እንስሳት ሲወለዱ በደመነፍስ ፍፁም ሆነው ነው፡፡ ሰው ብቸኛው ፍፁም ያልሆነ እንስሳ ነው። ስለዚህም በሰው ላይ እድገት፣ ዝግመተ - ለውጥ ይቻላል።

ትምህርት በእቅምና በልከኝነት መካከል ያለ ድልድይ ነው። ትምህርት በዘር መልክ ራሳችሁን እንድትሆኑ ያግዛችኋል፡፡ በተራ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት አይደለም። በእነዚህ ተቋማት የምታገኙት ትምህርት ጥሩ ስራ፣ ጥሩ ገንዘብ እንድታገኙ የሚያደርጋችሁ ብቻ ነው:: እውነተኛ ትምህርት አይደለም፤ ህይወትን አይሰጣችሁም። በቃ የኑሮዋችሁን ደረጃ ከፍ ቢያደርገው ነው፤ ነገር ግን የተሻለ ኑሮ የተሻለ ህይወት አይደለም፤ ሁለቱ አንድ አይደሉም።

በዓለም የሚሰጠው ትምህርት ተብዬ ነገር ዳቦ እንድታገኙ ብቻ የሚያዘጋጃችሁ ነው። ኢየሱስ እንዳለው «ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም::>> ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ ደግሞ ይህን ነው እያደረጉ ያሉት - በተሻለ፣ በቀለለ፣ በተመቸ፣ ጥረት፣ ድካም በሌለበት መንገድ ዳቦ እንድታገኙ ያግዛችኋል። ስራቸው በሙሉ እናንተን ዳቦና ቅቤ እንድታገኙ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትምህርት በጣም፣ በጣም ኋላቀር ነው:: ለህይወት አያዘጋጃችሁም፡፡

ስለዚህም ብዙ ሮቦቶች ሲረማመዱ ታያላችሁ:: እንደ ተላላኪዎች፣ የጣቢያ ተቆጣጣሪዎች፣ ዋና ሰብሳቢዎች ብቃት አላቸው:: ፍፁማን ናቸው፣ ጥበበኞች ናቸው:: በጥልቀት ብትመለከቷቸው ግን ለማኞች እንጂ ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ትረዳላችሁ፡፡ የህይወትን እንዲት ቅንጣት እንኳን አልቀመሱም፡፡ ህይወት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ብርሃን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ስለ እግዚአብሄር ምንም አያውቁም፣ ህልውናን አልቀመሱም፣ እንዴት መዝፈን፣ መደነስ፣ መደሰት እንዳለባቸው አያውቁም:: የህይወትን ሰዋሰው የማያውቁ መሀይማን ናቸው። አዎ፣ ከሌሎች የበለጠ ያገኛሉ፤ ከሌሎች የበለጠ ብልጣ ብልጦች ናቸው፤ በስኬት መሰላል ከፍ ብለው ይወጣሉ - በውስጣቸው ግን ባዶ፣ ምስኪኖች ናቸው፡፡

ትምህርት ውስጣዊ ብልፅግናን ያጐናፅፋል፡፡ የበለጠ መረዳ መስጠት በጣም ኋላቀር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ኋላ ቀር ነው ያልኩት በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፤ ካልተማርኩ በህይወት መቆየት አልችልም፣ በሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ሗላቀር ነው ያልኩት በውስጡ ነውጥን ስላዘለ ነው፤ ውድድርን ያስተምራችሗል፣ ምኞታም ያደርጋችኋል። ሌላ ምንም ሳይሆን ሰዎች እርስ በርስ የሚጠላሉበት የውድድር ዓለም ለመፍጠር የሚደረግ ዝግጅት ነው።

ስለዚህም ዓለም የእብዶች መኖሪያ ሆናለች። በዚህ ሁኔታ ፍቅር ሊወጣ አልቻለም። አንዱ የሌላኛውን ጉሮሮ በሚበጥስበት በዚህ ነውጠኛ፣ ምኞታም የውድድር ዓለም ውስጥ እንዴት ፍቅር ሊታይ ይችላል? ሗላ ቀር ነው ያልኩት «በደንብ ካልተማርኩ፣ በቂ ከለላ ካላገኘው፣ ደህና መረጃ ካልያዝኩ በህይወት ፈተና ውስጥ አሸናፊ አልሆን ይሆናል>> በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ህይወትን እንደ ትግል ብቻ ነው የሚመለከታት፡፡

እኔ ትምህርትን የማየው ህይወትን እንደ ትግል ሳይሆን እንደ ደስታ ሲቀርፅ ነው፡፡ ህይወት ውድድር ብቻ መሆን የለባትም፣ ደስታ ጭምር እንጂ፡፡ ትምህርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ዘፈን፣ ዳንስ፣ ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፤ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ሰማይ፤ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሊያዋህዳችሁ ይገባል፡፡

ትምህርት ራሳችሁን እንድትሆኑ ሊያዘጋጃችሁ ይገባል። አሁን ግን አስመሳዮች እንድትሆኑ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ሌሎችን እንዴት መምሰል እንዳለባችሁ እያስተማራችሁ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ማሳት ነው፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ራሳችሁን በእውነተኛ መንገድ እንዴት እንደምትሆኑ ያስተምራችኋል። እናንተ የተለያችሁ ናችሁ። እናተን የሚመስል ማንም የለም ፡ ወደፊትም አይኖርም። ይህ እግዚአብሄር ያጐናፀፋችሁ ታላቅ በረከት ነው። ይህ የእናንተ ክብር ነው! ልዩ መሆን ነው፡፡ አስመሳይ አትሁኑ፤ የካርቦን ቅጂዎች አትሁኑ።

እናንተ ትምህርት የምትሉት ነገር ግን ይህን እያደረገ ነው፡፡ የካርቦን ቅጂዎችን ይፈጥራል፤ እውነተኛ መልካችሁን ያጠፋል። <<ትምህርት>> የሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት፤ ሁለቱም ደግሞ ውብ ናቸው። አንደኛው ትርጉሙ ተግባር ላይ ባይውልም በደንብ ይታወቃል- አንድ ነገር ከውስጣችሁ ማውጣት። <<ትምህርት» ማለት በውስጥ ያለን ማውጣት፣ ውሀን ከጉድጓድ እንደ ማውጣት አቅምን በተግባር ማውጣት ነው።

ይህ ግን አልተተገበረም፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ እንጂ እንዲወጡ አልተደረገም። ህብረተሰብ እና ታሪክ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ወደ ውስጣችሁ ያንቆረቁርላችኋል። እናም ፓሮቶች ትሆናላችሁ። ልክ እንደ ኮምፒዩተር ይጉሰጉሱባችኋል:: የእናንተ የትምህርት ተቋማት ነገሮች በጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ የሚታጨቁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

እውነተኛ ትምህርት በውስጣችሁ የተደበቀውን (እግዚአብሔር በውስጣችሁ እንደ ሃብት ያስቀመጠውን) አውጥቶ፣ ገልጦ አንፀባራቂ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡

ትምህርት ሌላም ትርጉም አለው:: ትምህርት (Education) የሚለው ቃል የመጣው Educare ከሚለው ቃል ነው:: ትርጉሙም ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት እንደማለት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት በጣም አስፈላጊ ትርጉም አለው፡፡ ዮፓኒሻዶች እንዲህ ይላሉ «ጌታችን ሆይ፣ ከሃሰት ወደ እውነት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ፣ ከሞት ወደ ህይወት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ ከጨለማ ወደ ብርሃን ምራን፡፡» ይህ ነው «የትምህርት» ትክክለኛ ትርጉም፡- ከጨለማ ወደ ብርሃን።

ሰው ግን በጨለማ፣ ባለመንቃት ውስጥ እየኖረ ነው:: ሆኖም በብርሃን ምሉዕ መሆን ይቻላል፡፡ ነበልባሉ እዚያ አለ፡፡ ይሁንና መንበልበል፣ ወደ ውጭ መውጣት አለበት፡፡ ንቃት እዚያ አለ፤ ይሁን እንጂ መቀስቀስ አለበት:: ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል! ስትወለዱ ይዛችሁት መጥታችኋል፡፡ ሰብአዊ አካል ስላለን ብቻ ሰው ነን ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ለዘመናት ለብዙ መሳሳቶች መንስኤ የሆነው ይህ አስተሳሰብ ነው፡፡

ሰው ሲወለድ እንደ አንድ እድል፣ ሁኔታ ሆኖ ነው። ይህን የተጠቀሙበት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው - ኢየሱስ፣ ቡድሀ፣ መሐመድ፣ ባሃውዲን። እውን ሰው የሆኑት እጅግ ጥቂቶች ናቸው- በብርሀን ሲመሉ የቀረ ጨለማ አይኖርም፣ በነፍስ ውስጥ የሚተርፍ አለመንቃት አይኖርም- ሁሉም ነገር ብርሃን ሲሆን፣ እናንተ ንቃትን ስትሆኑ...

ንቃት፣ ንቃት ብቻ፣ ንፁህ ንቃት... ይህ ያለው ብቻ ምሉዕ ይሆናል። ይሄን ጊዜ ህይወት ቡራኬ ትሆናለች።

ትምህርት ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወስዳችኋል።

manyazewaleshetu

SHARE @hahumotivation
SHARE @hahumotivation
1.3K viewsአብዲ ኪያ የፍቅር አስተማሪ , edited  07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 19:35:53 ሳልፈልግ ልርሳሽ


ወራቶች አልፈዋል እኔ አንችን ሳፈቅርሽ
ድፍረትን አጥቼ በአካል ባልነግርሽ
በቴክስት ፃፍኩልሽ ፍቅሬ ቢገባሽ
ግን አሁን አዘንኩኝ መልስሽን ሳነበው
አንቺን አላገኝም ሁሉንም ሳስበው
ለኔ ላትሆኝ ነገር ለምን ላስቸግርሽ
በዱአ በፆም ሳልፈልግ ልርሳሽ

Maya

SHARE @hahumotivation
SHARE @hahumotivation
2.1K viewsአብዲ ኪያ የፍቅር አስተማሪ , 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 15:26:08
"ታገሱ ለሊቱ ቢረዝምም ከመንጋት አይቀርም እጅግ ትልቅ የተባለውም ቁስል እያደር ይደርቃል በትእግስት ያንኳኳችሁት በርም ይከፈታል ስትፈተኑ ሊሰጣችሁ የታሰበ በረከት እንዳለ አስቡ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ነገ የምትሰጣችሁ ስጦታ ነች በመልካም መቀበል በመጥፎም መቀበል መብታችሁ ነው ግን የወለወላችሁትን ቤት ሰው ሲያጨቀየው እንደማትወዱት የትላንት መጥፎ ነገራችሁ ዛሬያችሁን እንዲያጨቀይ አትፍቀዱ ንጋት እና እውነት እያደር ይጠራል "

ብሩህ ቀን ተመኘሁላችሁ

@hahumotivation
2.4K viewsSal, 12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 09:59:52 የመፍትሄ ሰው ሁን !

ማደግ ከፈለግህ የመፍትሄ ሰው ሁን "መፍትሄ ወዳለበት ገንዘብ ይፈሳል " ስለዚህ ምንም የምሰራው አጣው ካልክ ውጣ እና ዞር ዞር ብለህ አካባቢህን ቃኝ ምን ምን የጎደለ ነገር አለው? ሰዎች ምን አስፈልጎቸዎል? በዚህ ምድር ላይ ያለ ስራ ሁሉ የተፈጠረው መፍትሄ ለመስጠት ነው ህክምናው፣ ትምህርቱ ፣ ምግብ ቤቱ ፣ ልብስ ሰፊው ፣ ሊስትሮው ሁሉም የሰዎችን ችግር በመቅረፋቸው ሰው ወደ እነርሱ እየሄደ ገንዘቡን ያፈሳል ! እድለኛነታችን የእኛ ሀገር ብዙ መፍትሄ የሚፈልጉ ጥያቄዎች መኖራቸው ነው ስለዚህ የመፍትሄ ሰው እንሁን! ያኔ ከእኛም ተርፈን ለብዙው እንሆናለን!

@hahuethiopia
2.3K viewsአብዲ ኪያ የፍቅር አስተማሪ , 06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 08:16:23 ከ ታሪክ መዛግብት:
ምርጥ አባባሎች!

1. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ
ከፍተኛ ይሆናል፡፡
2. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር
ይወዳል፡፡
3. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም
የሚጠፋባቸው
በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ
በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡
4. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን
መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
5. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን
ብዛት
ይቀንሳል፡፡
6. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ
ተነሳህበት ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ
ካሰብክበት ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡
7. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡
8. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ
አትርገጥ፡፡
9. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት
እግሮቻቸው
ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡
10. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡
11. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/
ከማሸነፍ
ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡
12. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ
እየሆነ ይሄዳል፡፡
13. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡


@hahumotivation
2.7K viewsአብዲ ኪያ የፍቅር አስተማሪ , 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 15:58:55 #ለፈተና ተዘጋጅ

የውስጥ ስብዕናህን በየቀን መገንባት አለብህ! የህይወት ፈተና መቼ እንደሚመጣ፥ ከየት እንደሚመጣ አታውቅምና ሁለም ዝግጁ ሁን! የተሠራ ስብዕና በፈተና ሰዓት ትምከት ነው።
ትናንት የምትፈራቸውን ሰዎችና ነገሮችን ዛሬ አትፈራቸውም ተመስገን ይህ የእድገት ማሳያ ነው። አሁንም ግን ማደግ አለብህ!

የውስጥ ስብዕና እድገት ለስኬትህና በፈተና ቀን መቋቋም ትችል ዘንድ ጸኑ የኃይል ምንጭ ነው።

@hahumotivation
2.3K viewsLecture, 12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 12:14:59 ስኬት አይወረስም!

የወላጆቻቸውን ገንዘብ ከወረሱ በኃላ ፣ ሥጋቸው በመቃበር ሳይበሰብስ መንገድ ዳር ወጥተው የሚለምኑ ፣ያልተሰራ ስብዕና ማሳያ ናቸው።

ከስብዕናህ በላይ የተኛውንም ነገር
መሸከም አትችልም።
ከሆንከው በላይ የሆነ ነገር ቢመጣ ፣ የአይገባኝም ስሜት ድምጥማጡን ያጠፋዋል።

አሁንም ወዳንተ ሁሌም እድልም ገንዘብም እየመጣ ይገኛል፤ ካንተ በላይ እንደሆነ ስለሚሰማህና ተቀብሎ የሚያስተናግድ ስብዕና ስላልገነባህ ሁሌም ተመልሶ ይሄዳል።

ውጫዊ የሆነውን ነገር ለማግኘት ጠንክረህ ከመስራት ይልቅ የውስጥ ስብዕናህ ላይ ጠንክረህ ሥራ!
የሆንከውን ነው የምትስበው!

የምትፈለገውም ሰው ወዳንተ መጥቶ እሱን የምመጥን ስብዕና ከሌለህ ተመልሶ ነው የምሄደው።


ስብዕና መሠረት ነው!
ዕዝራ ዘ-ፕሪንስ

ይቀላቀሉን @hahumotivation
3.0K viewsBe positive, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 22:18:39 ክፍል ሁለት ተለቀቀ

ኦሮሚኛ ቋንቋን መማር ለሚፈልጉ ቤተሰቦች ትምህርት መስጠት ተጀምሯል።

ክፈል ሁለት ተለቋል ገብታችሁ ማየት ነው።

የሚለቀቅበት Youtube Channel #ATCTube ነው። Telegram @atc_afaanoromoo

የአፋኖ ኦሮሞ ትሞህርት ክፍል ሁለት


2.2K viewsBe positive, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 11:31:53 አፋን ኦሮሞ መማር ለሚፈልጉ ቤተሰቦቻችን በሙሉ

አፋን ኦሮሞ Tutorial ክፍል አንድ

በዚህ መልኩ ቀን በቀን እንማራለን ። መማር እና ለውጥ የምትፈልጉ በሙሉ ተቀላቀሉን።

የሚለቀቅበት Youtube Channel #ATCTube ነው። Telegram @atc_afaanoromoo

ክፍል አንድ


1.7K viewsBe positive, 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 12:40:31 የመረጥከውን ነው የምትኖረው

ህይወትህን ጣፋጭም መራራም ማድረግ ትችላለህ፦ ሁለቱም የለው ባንተው እጅ ላይ ነው።ከሁለቱ አንዱን ስተመርጥ፤ለመረጥከው ነገር የነገ ህይወትህን አሳልፈህ እየሰጠሀው እንደሆነም እወቅ።

የዛሬ ምርጫህ የነገ ህይወትህን ይወስናል።ስለዚህ ዛሬ የምመርጠው የህይወት ጎዳና፤ወደፊት ህይወቴ ላይ ምን አይነት ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል የሚለውን ከግምት በማስገባት፣ እንዴትና ምን መመረጥ እንዳለብህ በደንብ አስብበት።

ዛሬ በንዴትና በምሬት ተነሳስተን የምንመርጠው መንገድና የምንወስነው ውሳኔ ነገ ዋጋ እያስከፈለ ብኩን አድርጎ ከሚያስቀረን፤ነገሮች እኛ እንዳሰብነው ባለመሆን የጋለውን ስሜታችንን ተቆጣጥረን፣በተረጋጋ መንፈስ የሚጠቅመንን መመረጥና መወሰን ይኖርብናል።

ነገህ ውብና የማረ እንዲሆን እየፈለክ ዛሬ የምታልፍበት ውጣ ውረድ ህልምህን ሊያስረሳህም አይገባም።

ደስ የሚል ቅዳሜ ተመኘን
@hahumotivation
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
5.0K viewskiyaye , 09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ