Get Mystery Box with random crypto!

ባለ ድሎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል በቻን ማጣርያ የሩዋንዳ አቻውን አሸንፎ ለ | ሀዲያ ሆሳዕና

ባለ ድሎቹ አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል


በቻን ማጣርያ የሩዋንዳ አቻውን አሸንፎ ለአልጄርያው የቻን ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምሽት 2፡30 ላይ አዲስ አበባ በሰላም ደርሷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ ፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሸረፋ ደለቾ እና አቶ ሙራድ አብዲ ፣ የቀድሞ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ አበበ ገላጋይ እና የፅሕፈት ቤት ሰራተኞች ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ተገኝተው ቡድናችንን የአበባ ጉንጉን በማበርከት ተቀብለዋል።