Get Mystery Box with random crypto!

ቀያይ ሴጣኖቹ መድፈኞቹን ረተዋል! በስድስተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግ | ሀዲያ ሆሳዕና

ቀያይ ሴጣኖቹ መድፈኞቹን ረተዋል!

በስድስተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የአርሰናልን #ያለመሸነፍ ጉዞ ገተዋል።

√ ማርከስ ራሽፎርድ ( 2X ) እንዲሁም አዲሱ ፈራሚ አንቶኒ የቀያይ ሴጣኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ ቡካዮ ሳካ የመድፈኞቹን ብቸኛ እና አቻ ያደረገች ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

√ ቡካዮ ሳካ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊጉ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

√ ማርከስ ራሽፎርድ ባለፉት አራት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ሶስት ጎል ሲያስቆጥር ሁለት ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።

√ አንቶኒ በመጀመሪያ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለ በእድሜ ትንሹ ብራዚላዊ ለመሆን ችሏል።

√ #አርሰናል አሁንም ሊጉን #ሲመሩ ከተከታያቸው ማንችስተር ሲቲ በአንድ ነጥብ በልጠው ይገኛሉ።

√ ተከታታይ ጨዋታዎችን ያሸነፉት ማንችስተር ዩናይትዶች በአስራ ሁለት ነጥብ #አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

√ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር #አርሰናል ከ ኤቨርተን እንዲሁም #ማንችስተር_ዩናይትድ ከ ክሪስታል ፓላስ የሚገናኙ ይሆናል።