2021-10-25 18:32:20
//በውሎዬ አመሻሽ//
ካሊድ (ሀበሺስታን)
ስራዬን ጨርሼ ከአንድ ባለእንጀራዬ ጋር ከስራ ቦታ እየወጣን ነበር።
ወደ ታክሲ ተራ የምታደርሰዋን ቀጭኗን መንገድ በውስጤ <<ታክሲ እናገኝ ይሆን አይይይ አይመስለኝም>> እያልኩ ነበር የወረድናት።
ቀጭኗን መንገድ ጨርሰን ታክሲ ወደመያዣው ልናዘቀዝቅ መንገዴን ሳሰናዳ <<እእእ አንድጊዜ የሆነች ነገር እናስጨርስ>> አለኝ በጠያቂ አንደበት ደግሞ የሆነች ነገር ምንድን ናት? ብዬ እያሰላሰልኩ አስፓልቱን ተሻግረን አንድ ባለ 3 ፎቅ ደርብ ያለው ህንፃ ውስጥ ዘለቅን።
ቤቱ ኢንተርኔት ቤት ነው (ኢንተርኔት ካፌ) የሚሉት። ቤቷ ጠባብ ናት። እንደገባን በስተቀኝ አልጋ የሚያህል ሶፋ ተጋድሞ ተቀመጡ እያለ የሚጋብዝ ይመስላል። ነገር ግን ሶስት ሰዎች ብቻ እንደ ሱሉልታ መሬት አስፍተው ይዘውት ሌላ ሰው ለመጨመር አይጋብዝም
ባለእንጀራዬ ግን ትንሽ ቦታ ስላገኘ ሰርስሮ ገብቶ ተቀመጠ።
እኔም ግራ ቀኝ ስገላምጥ በስተግራ ሶስት ኮምፒውተሮች ተገጥግጠው የተጠቃሚ ያለህ የሚሉ ይመስላሉ። መቀመጫ ወንበር ባለመኖሩ ለኮምፒውተሩ ተጠቃሚ ተብለው የተዘጋጁት ሶስት ወንበሮች ውስጥ ተሽከርካሪዋን ወንበር መርጬ ተቀመጥኩ።
የአጋጣሚ ነገር ሆኖ ዛሬ እጄ ላይ መፅሀፍ ሳይሆን ክስ እንዳለበት ሰው ካኪ ይዤ ነው ከስራ የወጣሁት።
ባለእንጀራዬ ስልኩን ይዞ የማላዬውን ነገር እያዬ ሳቁን ይለቀዋል። እንደገና ቆይቶ የያዘውን መፅሀፍ ገልጦ ሙሉ ትኩረቱን እሱ ላይ አድርጐ ከእኔ ጋር በሀሳብም በመንፈስም ተለያየን ።
በዚህ መሀል አንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ መጣና ተሽከርካሪ ወንበሯን አስለቀቀኝ ተመችቶኝ ስለነበር ቅር እያለኝ ሌላ የማይሽከረከር ወንበር ላይ ተቀመጥኩ።
ከፊት ለፊቴ ያው ሲጋነን የምድር ወገብ የሚያህል ጠረጴዛ የቤቱ ወለል ላይ እንደተጋደመ አስተዋልኩ። ከጀርባው አንድ ቀይ ልጅ የማይገባኝን መዝሙር ይሁን ሙዚቃ ከፍቶ እየተዝናና ደንበኞቹን ያስተናግዳል። ዘፈኑ ወይ መዝሙሩ ብቻ የተከፈተው ነገር ያልገባኝ ልብ ብዬ ስላልሰማሁት ነው።
የቤቱ ደንበኛ ብዙ ነው ደንበኛ ክቡር ነው የሚለው መሸንገያ ቃል ባይለጠፍም ሰው ወደዚህ ቤት መትመሙን አልተወም። እንደዚህ ደንበኛ የበዛው ኢንተርኔት ቤት ሳይሆን ኢንተርኔት ካፌ ካፌ የምትለዋ ስባው ይሆን የሀገሬ ሰው እንደሁ ገር ነው ትንሽ ነገር ትደልለዋለች።
ከደንበኛው መሀል ግማሹ ፅሁፍ ያስፅፋ፣ ግማሹ ኮፒ ይላል፣ እኝን ይህንን ያህል ደቂቃ እንድንጠብቅ ያደረገን የሆነችዋ ነገር ከበድ ያለች ነገር ናት ብዬ መጠባበቅ ጀመርኩ።
በመሀል ሰው እየጨረሰ ሲወጣ ሶፋው ላይ ለመቀመጥ እድል አገኘሁ ሄጄ ሰፋ አድርጌ ያዝኩ። ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለካኪዬም ሰፋ ያለ ቦታ ሰጠኋት።
ለካ ሰው እንደዚህ በወረፋ ይጠባበቅ የነበረው ወደ ውጪ ለመሄድ ዲዢ ይሉትን ነገር ለማስሞላት ኖሯል።
<<……… አሀ ወዳጄ አንተስ ለምን አትሞላም?>> አለኝ ባለ ኢንተርኔት ቤቱ << ለምን ብዬ ?>> አልኩት አይ በቃ ውርስ አለህ ማለት ነው። ብሎ ተሳለቀብኝ
<<አረ ወዳጄ እንኳን ውርስ ስራም የለኝም>> የኔ መልስ ነበር……… <<እና እንዴት መሄድ አትፈልግም? >>አለኝ <<አዎ አልፈልግም ሀገሬን በችግሯ ሰዐት ለማን ጥዬ>> አልኩት የዛኔ እኔ ለራሴ እራሴን እንደ ብዙ ብርጌድ ጦር የተመለከትኩት ስለመሰለኝ ዝም አልኩ።
በዚህ መሀል የአንደኛው ተራ ደረሰ እና አድራሻ መሙላት ጀመረ። ትንሽ ጥያቄዎችን ሲጠያየቁ ሲመላለሱ ቆዩ እና በስተመጨረሻ ባለ ኢንተርኔት ቤቱ <<አድራሻ ኮልፌ ልበለው?>> የሚል ጥያቄ ሰነዘረ።
ትንሽ እንደማሰብ አድርጐ ተስተናጋጁም <<የለ የለ አራዳ አድርገው>> አለ መልካም ብሎ መሙላት ሲጀምር ከደንበኛው እኔን ያስፈገገች ከእኔ ውጪ ባለ ኢንተርኔቱ ሰውዬ እንኳን ሰምቷት ብዙም ቁብ ያልሰጣትን ጥያቄ ጠየቀ
<<አራዳ ሲባል ፒያሳን ይጨምራል?>> አለ ጉድ አልኩ ዞሬ እያየሁት
ባለ ኢንተርኔት ቤቱ ሰውዬ <<አዎ የአራዳ ልጅ>> ብሎ አለፈው ድንቄም የአራዳ ልጅ እኔ ግን አዕምሮዬ ላይ ተመላለሰ አለማወቅ አይሉት ፒያሳን ከአራዳ ነጥሎ ማወቅ ፒያሳን ካለማወቅ በላይ ይከብዳል ታዲያ እንዴት?
ከዚህ ግን ያስፈገገኝ የባለ ኢንተርኔቱ መልስ ነበር። አዎ የአራዳ ልጅ ፎገረው ሰውዬው ግን በአራዳ ልጅነቱ ተመፃድቆ መቀመጫው ላይ ተመቻቸ። አረ እንደውም የአራዳ ልጅ በመሆኑ ተመፃድቆ ዞር ብሎ እኔን ገላምጦ ፋራ ያለኝም ይመስለኛል ያው በውስጡ መሰለኝ ነው ።
ታዲያ እኔ ምኔ ሞኝ እሱ ብቻማ በውስጦ ሰድቦኝ አይቀርም ብዬ እኔም ይሉሽን አልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ ብዬ ገላመጥኩት ያው በውስጤ።
ብዙም ሳይቆይ ሌላ አንድ ሰው መጥቶ አጠገቤ ተቀመጠ። አንድ ነገር አንስቶ መጫወት ጀመረ። <<ንግድ ባንክ ከአስረኛ ክፍል በላይ ያሉ ሰዎችን አወዳድሮ እየቀጠረ ነው ለምን አትሞክርም ?>> አለኝ።
ስራ እንደሌለኝ እንዴት እንዳወቀ ግራ ገብቶኝ ገልመጥ ገልመጥ አድርጌው አልፈልግም አልኩት።
<< ስድስት ሺህ ይከፍላሉ>> አለኝ በደሞዝ ሊያማልለኝ።
<< የለም ይቅርብኝ ምን ጐደለብኝና እሰራለሁ>> አልኩት ግራ ተጋባ መሰለኝ ዝም ብሎ ያዳምጠኝ ጀመር።
ለደሞዝ ብዬ እራሴን የማጣበትን ስራ ስለምን ብዬ እሰራለሁ። ስራ በደሞዝ አይለካም ብዬ አያሌ ክርክሮችን ስራ አለመስራቴንም በመረጃ አስደግፌ ደረደርኩለት ለመከራከር ሲሰናዳ ባለእንጀራዬ <<ተነስ እንሂድ ጨረስኩ>> አለኝ የሆነችዋ ነገር አለቀች ሰውዬው ሀሳቡን ባለመናገሩ በሽቆት አፀፋውን እየገላመጠን ወጣን።
የህንፃውን ደረጃ እየወረድን አንድ ሲቀረን አደናቀፈኝ። ባለእንጀራዬ እይዛለሁ ብሎ ፊቴን ቧጨረኝ። ብወድቅ ይሻል እንደነበር እየነገርኩት እየተሳሳቅን ታክሲ ለመያዝ አስፓልቱን ተሻግረን ቁልቅል ትንሽ ወረድን።
ከብዙ አሰልቺ ጥበቃ ቡሀላ አንድ ባዶ ታክሲ መጥቶ እንደ ማነኛውም አዲስ አበቤ ተጋፍተን ገባን።
ገብተን ከኋላ ወንበር ተቀመጥን ሙሉ ነገሬ እንደገባ እያረጋገጥኩ ሌላ አንድ ከሀሳብ የገዘፈች ሴት መጥታ ሁለት ሰው የሚይዘውን ወንበር ሞላችው። የጉድ ሀገር ብዬ ዞር ስል አንድ ለግላጋ ወጣት ታክሲው ሞልቶበት ብቻውን ቅጭም ቅጭም እያለ ቆሟል።
<< አረ አስገቡት አራተኛ ሰው>> አልኩ ብርዱ እኛን ሰቆጣ ሲያስጨፍረን ስለቆየ የእሱም እጣ ፈንታ እንዳይሆን ብዬ………
ሁሉም ዝም <<አረ ይበቃናል አስገቡት ዝም………… በዚህ ብርድ አያሳዝንም በእናታችሁ አስገቡት>> ስል አጠገቤ የተቀመጠችው ሴትና ከፊት ለፊቷ ያለችው የእርሷ ቢጤ ሴት ጋር ተመሳጥረው <<ምነው ወንድምህ ነው እንዴ>> ብለው ከሩቅ ሊሰማ የሚችል አይነት ሳቅ ሳቁብኝ………
እስኪጨርሱ ዝም ብዬ ተመለከትኳቸውና አንድ ቃል ብቻ እንዲሰሙ አድርጌ ተናገርኩ "መተዛዘን አሳቀ?" አልኩ በጥያቄ መልኩ የሳቃቸው ፍም ላይ ውሀ ተቸለሰበት ዝም አሉ ።
ከዚህ በኋላ ያለውን ይስሙኝ አይስሙኝ ባላውቅም…… ለነገሩ እናንተ ምን አጠፋችሁ መተዛዘን መደጋገፍ ቅንጦት ሆኗል አንዱ ለአንዱ የሚያዝነው የስጋ ወንድሙ ወይ የእሱ ዘር ከሆነ እሱም እድለኛ ከሆነ ነው ። እነዚህን የመሳሰሉትን ግማሹን በውስጤ ግማሹን በአንደበቴ እየተናገርኩ ታክሲው ገሰገሰ። ባለእንጀራዬ ተናደድ እንጂ በደንብ …………በቃ ይህችን ብቻ ነው የምትናደድ………… አለመናደድህ እኔን አናደደኝ………… እያለ ይነዘንዘኛል የሁል ጊዜ ማፅናኛው እንደሆነ ስለማውቅ በእሱ ድርጊት ንዴቴን ዘንጋ አደረግኩና ወደማይመለከተኝ እርዕስ አዘነበልኩከፊታችን ያለው ወንበር መደገፊያው የተገነጠለ
368 views15:32