Get Mystery Box with random crypto!

#የጉራጌ ሕዝብ ለሺ ዘመናት የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ዋልታ የነበረ፣ የራሱ የሕዝብ አስተዳደር | Zebidar Tube (ዘቢዳር)

#የጉራጌ ሕዝብ ለሺ ዘመናት የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ዋልታ የነበረ፣ የራሱ የሕዝብ አስተዳደር ስርዓት የነበረው ሰራተኛ ሕዝብ ነው እንጂ ጉራጌ በዛሬ ሚዛን ብቻ ከመዘነው በዛሬ አይን ብቻ ካየነው ህዝቡን አናውቀውም ማለት ነው፡፡

#የጨቦ ተወላጁ አቶ ምስጋናው በላቸው በመጽሐፋቸው ገጽ 66 እንደሚገልጹት እስከ መካከለኛው ዘመን የማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ዋልታ የነበረው ጉራጌ ከግራኝ ወረራ በኋላም ለኢትዮጵያ ቤተመንግሥት በጣም ቅርብ ነበር። ከግራኝ ዘመቻ በኋላ ዋናኞቹ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ራሶች ጉራጌዎች ነበሩ።

#ከኢማሙ አህመድ ጦርነት በኋላ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የመንግሥት ስልጣን ከነበራቸው አራጊ ፈጣሪ ጉራጌዎች መካከል በዐፄ ያዕቆብ [ እ.ኤ.አ. ከ1597 ዓ.ም. – 1603 ዓ.ም.፤ እንዲሁም ከ1604 ዓ.ም. -1607 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ] እና በዐፄ ዘድንግል [ እ.ኤ.አ. ከ1603 ዓ.ም. – 1604 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ) ዘመናት የነበሩትን ራስ ዘሥላሴን ለአብነት መጥቅስ ይቻላል። የጉራጌ ተወላጁ ራስ ዘሥላሴ ዐፄ ዘድንግል “መልከ ሐራ” በሚል ያቋቋሙትን የንጉሥ ሠራዊት ይመሩ ነበር። ዐፄ ሰርጸ ድንግል እ.ኤ.አ. በ1597 ዓ.ም. ከሞቱ በኋላ ደግሞ ለሚቀጥሉት 10 ዓመታት ኢትዮጵያን የገዙት ራስ ዘሥላሴ ነበሩ ማለት ይቻላል።

-----------------
#የበለጠ መረጃ ለማግኘት

Telegram;- https://t.me/gurageZ

YouTube;- https://youtube.com/channelUCspMeuO6nhHHOHZpVA1ZSSQ

Facebook;- Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ

tiktok;- tiktok.com/@zebedir

#ኢትዮጵያን እንገንባለን #ጉራጌ ክልላዊ አስተዳደር ይኖረዋል #ጎጎት በዘቢዳር እውን ይሆናል!