#የተሻሻለው የጆካ ቂጫ (የጆካ ባህላዊ አስተዳደረ ሸንጎ) ፀደቀ።
#በተለያየ ምክንያት የሰው ህይወት ሲያልፍ በየጆካ ቂጫ መሰረት የደም ካሳ በግፍ ወይም ሙራ ደም 3መቶ ሺ በስህተት ወይም መዳራ 150 ሺ ፣በአጋጣሚ/በጥቂት ስህተት 75 ሺ ብር እንዲከፍል ተወስኗል።
#በተያያዘም በመኪና የሚጠፋ ክቡር የሰው ልጅ ህይወት በግፍ ያጠፋ (ሙራ ደም) 2መቶ ሺ በስህተት 1መቶ ሺ ፣በአጋጣሚ 50 ሺና የአካል ማጉደል ሙሉ የህክምና ወጪ ሸፍኖ ቅጣቶች እንደየሁነታዉ የሚቀጣ ይሆናል።
#የአባላዘር ማበላሸት በተመለከተ የወንድም ሆነ የሴት አባላዘር ሆን ብሎ ያበላሸ መሆኑ ከታወቀ በሆስፒታል እና በሃኪም ከተረጋገጠ በብር 2መቶ ሺ መቀጣት እንዳለበት ተገልጿል።
#የመግድል ሙከራ ያደረገ ወይም የሰነዘረ (የቁም ደም) በብር 1መቶሺ ብር ይቀጣ ተብሏል በቂጫው።
#በግፍ ቤት ያቃጠለ 2መቶ ሺ፣ በስህተት 1መቶ ሺ፣ በፍጹም ስህተት 50 ሺ ሆኖም የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ከተቃጠለ ከመርፌ እስከ ትልቁ ንብረት ተደምሮ ይከፈል ሲል ቂጫው አስታውቋል።
#የቸግ ስራአቱ የማሻሻያው አካል ሆኗል። በዚህም የጆካ ባህላዊ አስተዳደር ሸንጎ የወንድ ቤተሰብ ለልጁ የትዳር ጓደኛ ለመጠየቅ ወደ ሴቷ ቤት የሚሄድ ሽማግሌ በቁጥር 7 ብቻ እንዲሆን የወንድ እና የሴት አጃቢ 10 ብቻ እንዲሆን ውሳኔ አስተላልፏል።
#በእለቱ ለሚፈጸመው የቸግ ስርአት አንድ በግ ወይም ፍየል ብቻ እንዲታረድ ተወስኖአል።ሆኖም ይህ ቂጫ የጣሰ ከወንዱ ወገን 25ሺ ከሴቷ ወገን 25 ሺ በድምሩ 50 ሺ እንዲቀጣ ተደንግጓል።
#በአሁን ሰአት የለቅሶ ስርአቱ በህብረተሰቡ ጫና አሳድራል ያለው የጆካ ባህላዊ አስተዳደረ ሸንጎ በለቅሶ ለእንግዳ መቀበያ በሚል የእርድ ከብት እንዲሁም እንጀራ እና እሽግ ውሃ ማቅረብ በቂጫው ተወግዞ እንዳይፈጸም የተወሰነ ሲሆን እንግዳ መሸኛ በንፍሮ ቢቻ እንዲሆን በቂጫ ተቀምጧል።
#በመሆኑም ይህንን የተቀመጠውን ቂጫ የሻረ ሃዘንተኛው በብር 50 ሺ መክፈል አለበት ተብሏል።
#በጉራጌ ብሄርረሰብ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ እድሜ ጠገብና ዘመን ከማይሽራቸው ቅርሶች ውስጥ አንዱ ጀፎረ ነው።
#ይህን ለግል ጥቅሙ ቆፍሮ ጭቃ ያቦካ፣ጎርፍ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ የቆፍረ፣አፈር ቆፍሮ ወደ ግቢ ያስገባ፣ የቆፋረው አፈር መልሶ እንዲሞላ የሚያደርግ ሲሆን ለዚህ ለሰራው ከፍተኛ ጥፋት 20 ሺ ብር ካሳ የሚከፍል ይሆናል።
#የጀፎረ መሬት አጥሩ አስገብቶ ቤት የሰራ፣ዛፍ የተከለ ንብረቱ ተወርሶ ለቀበሌ ገቢ እንዲሆን ከዚያ ተለክቶ የድንበር ድንጋይ ተተክሎ ካስረከበ በኋላ ካሳ 10ሺ መክፈል እንዳለበት ተቀምጧል።
#ሰብል ማቃጠል ወይም መንቀል በታዋቂ ባለሙያ ተገምቶ እንዲከፈል ተደርጎ በተጨማሪ የሞራል ካሳ ከ30ሺ እስከ 60ሺ እንዲከፈል ውሳኔ አስተላልፏል።
#የወግ ምስ በተመለከተ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን ሃላፊነቱ በአግባቡ እንዲወጣ የጆካ ሸንጎ ዉሳኔው አሳርፎአል።በዚህ መሰረት በሸማግሌ ያለቀ ጉዳይ ማጠቃለያ ለመስጠት በሳምንት ሁለት ቀን ቅዳሜና እሁድ አገልግሎት እንዲሰጥ ለሰጠዉ አገልግሎት በእያንዳንዱ ባለጉዳይ 3መቶ ብር ብቻ ይሰጠዋል።
#በጉራጌ ብሄር ተስካር ለሟችም ሆነ ለቀሪው ቤተሰብ አላስፈላጊ ወጪ ከማዉጣት በስተቀር የሚጠቅም ነገር እንደሌለ ይታመናል።ስለሆነም በቤተ እምነቶች የሚደረገው ስርአት እንዳለ ሆኖ ይህን ቂጫ በመጣስ ተስካር ያወጣ
50 ሺ ብር መክፈል እንዳለበት ቂጫ ያስገድደዋል ማለት ነው።
#ማንኛውም የጉራጌ ተወላጅ ራስንና ቤተ ዘመድን የሚያዋርድ ጋብቻ የሚያስከለክል ያልሆነ እና ያልተደረገ መጥፎ ነገር በመጥራት ለምሳሌ ኦዘ (ኦዛይ) /ዘረ ቢስ በማለት የተሳደበ መሆኑን በማስረጃ እና በሽማግሌዎች ከተረጋገጠ በኋላ 1ዐሺ ብር እንዲቀጣ በቂጫ ተቀምጧል።
#የጆካ ቂጫ በመተላለፍ በቸግ፣በለቅሶ፣በጀፎረና በመሳሰሉት ከቅጣት የተገኘ ገቢ 50 ፐርሰንቱ ለጆካ ባሀላዊ ሸንጎ፣50 ፐርሰንቱ ለየወረዳዉ ባህል ሸንጎ በደረሰኝ ገቢ ይደረግ ያለው የጆካ ባህላዊ አስተዳደረ ሸንጎ ይህን ጉዳይ ለማስፈጸም ተባባሪ አካላት የየወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ጸ/ቤት፣ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት፣የቀበሌ አስተዳዳር እንዲሁም እንደቀበሌዉ ብዛት የሚዋቀር ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
#ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በመጀመርያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማሯቸው ተማሪዎች ዛሬ አስመርቀዋል፡፡
-----------------
#የበለጠ መረጃ ለማግኘት
#Share #like #Subscribe
ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/channel/UCspMeuO6nhHHOHZpVA1ZSSQ
የቴሌግራም ቻናልም https://t.me/gurageZ
በፌስቡክ ገጻችን Zebidar Tube/ ዘቢዳር ቲዩብ
ይወዳጁን!