Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ጥቅሶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ gtem_na_tks — ግጥም እና ጥቅሶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ gtem_na_tks — ግጥም እና ጥቅሶች
የሰርጥ አድራሻ: @gtem_na_tks
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.87K
የሰርጥ መግለጫ

creator @henajs

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-10 19:11:39 #ትዝታ

በተስፋ በጉጉት ቢፈልግ ትዝታ
ትውስታ ሆናለች ምዕራፏን ዘግታ
ጠላት ብቶንበት ለናፋቂው መቀስ
ልቡን ብታወርድም ንግስት አትከሰስ

ግና ባይተዋትም አሁንም ይጥራል
ገንጣይ ተዋጊው መሆኗን ዘንግቷል
አልቀደስ ያለች የማትገባ ከብል
እምነት የለሽ ባሪያ ቃሏን የምታጐል

የትዝታን መፅሀፍ አንዱም አይገለጥ
ያለመሰልጠኗን ታሪክ አይሸመጥጥ
ብቻ እንደምድመው ታሪክ ትሁንና
ደመኛው ጠላቱ ትዝታ ናትና

ፂዮን ምትኩ
..................................

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
959 viewsZion, 16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 16:23:40 ቀጥረሽኝ....
ፈላስፋ አደረግሽኝ(ርእሱ ነው)
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ላገኝህ ስትዪኝ...
በፊትሽ ለማመር ፣ በፊትሽ ልነጣ
ልብሴን አጣጥቤ ፣ ገመድ ላይ ሳሰጣ
ደመናው ኬት መጣ?
አርፍጄ እንዳላጣሽ ፣ ስፈራ ስሳቀቅ
ልብሴን በላዬ ላይ
በእግር መንገድ ላደርቅ
ስራመድ እየሮጥኩ
መንገዱ አጠረ ፣ ካልሽኝ ቦታ ደረስኩ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰአቱ እስኪደርስ ፤ ሰአት እየፈጀሁ
በምናብ ገፄ ላይ
ስትመጭ የምልሽን ፣ ቃል እያዘጋጀሁ
ካንቺ ጋራ ስሆን...
እንዴት እንደምሔድ ፣ አካሔድ ሳጠና
አንዴ አንገት ስሰብር ፣ አንዴ አንገት ሳቀና
አንዴ እግሬን ስጎትት፣ አንዴ እግሬን ሳነጥር
ቀፈቴን ስደብቅ ፣ ደረቴን ስወጥር
እንደድሮ ለኪ ፣ እርምጃ ስቆጥር
ጫማዬን ነደለው ፣ አገኘኝ እንቅፋት
ሰአቱ ገና ነው...
ኒስትሮ ጋ ሔድኩኝ ፣ ጫማ ለማሰፋት፡፡
ሊስትሮው...
በወስፌ መንጠቆው ፣ ጅማቱን ይጠልፋል
ቀዳዳ እያበጀ ፣ ቀዳዳ ይሰፋል
ይለኛል ጫማዬ...
"የህይወት ትንሽ ሽንቁር...
ጊዜና ግመልን ፣ እኩል ያሳልፋል፡፡
ሰአቴን አየሁት ፣
ከቀጠርሽኝ ሰአት ፣ ጥቂት ደቂቃ አልፏል፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።፣።።፣።፣
እየተጣደፍኩኝ...
ያልሽኝ ቦታ እስክደርስ
እስካገኝሽ ድረስ
ቅድም ያጠረብኝ...
እዛው በዛው ሆኖ ፣ ራቀኝ መንገዱ
መድረስ ተረት ሆነ ፣ "ሲሔዱ ሲሔዱ
ሲሔዲ ሲሔዱ
ሲሔዱ ሲሔዱ ፣ መንገዱ አያልቅም
ሳጣሽ ተፈላሰፍኩ...
መፈለግ ነው ብዬ ፣ የፍልስፍና አቅም፡፡
፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ!
ልብሴን ስዳብሰው ፣ እላዬ ላይ ደርቋል
ሰማዩን አየሁት ፣ ደመናው ተፍቋል
መንገዱ ቅድም ላይ ፣ ልሔደው ስል ያልቃል
አሁን ላይ ስሔደው...
ስሔደው ስሔደው ፣ ስሔደው ይርቃል፡፡
ወደ ጫማዬ ሳይ ፣ አንድ እግሬ ነው ባዶ
ሊስትሮው እጅ ላይ....
ትቼው መጥቻለሁ ፣ ያልሽኝ ሰአት ሔዶ
የህይወትን ሽንቁር...
ላይጠግን ይሰፋል ፣ በወስፌ ተቀዶ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜ መጥቼ ፣ በማርፈዴ ሳጣ
በጣም ከቀደመ....
እጅጉን ይሻላል ፣ አርፍዶ የመጣ፡፡
ሰው የሚሉት ፍጡር...
ነፍስ ከስጋ ጋር ፣ እኩል ሲሞግተው
ፍፁም ልሁን ሲል ነው ፣ ፍፁም የሚስተው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እፈላሰፋለሁ...
ቀድሜሽ መጥቼ ፣ አርፍጃለሁ ሳውቀው
እፈላሰፋለሁ!
ቀድመው ሲያረፍዱ ነው ፣ መንገድ የሚርቀው
እፈላሰፋለሁ!!!
የሚጠነቀቅ ነው ፣ ማይጠነቀቀው!!!

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
@lula_al_greeko
1.1K views £NƏ`"`"`"`"`"`, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 12:15:27
አንዳንድ ጊዜ ምክር አያስፈልገንም
የሚሰማን ሰው ብቻ

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.0K views £NƏ`"`"`"`"`"`, 09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 11:50:55
አዋቂ የሚያደርጋችሁ
እድሜ ሳይሆን
ሀላፊነት ነው

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.0K views £NƏ`"`"`"`"`"`, 08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 23:26:40
ፀሀይ ስትገባ አታልቅስ
ምክንያቱም እንባው
ኮከቦችን እንድታይ
አይፈቅድልህም

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.2K views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:33:46 "አልሰማም ሙት ወሬ
አልሰማም ግርግር
እንኳን ሰው ይቅርና
ይጋጫል አንድ እግር"
ብለን ንቀናቸው ሴረኞችን ሁሉ
ሊያጠፉን ተነሱ ሰው እየገደሉ

መጀገን መስሏቸው የሰው ነብስን መብላት
ልታገስ ባለ ክር ቃልኪዳኔን በሏት

ሁለት አይነት ኑሮ በምትኖረው አለም
የጊዜ ነው እንጂ የሰው ጀግና የለም።

#ጊዜ_ርዕስ_ነው

ዮኒ
ኣታን @Yonny_Athan

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.5K viewsYonny Athan, 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:27:41 ትልቅ ሰው ነው ያልኩት!
ሀገር ማለት ትቶ ብሄሩን ሲጠራ
.
አዋቂ ነው ያልኩት!
ህዝብ ማለት በቅቶት በጎሳው ሲኮራ
.
ምሁር ነው እሱ ያልኩት!
ድብብቆሽ ይዞ ሰው ከሰው ሲያባላ
.
ዳኛ እኮ ነው ያልኩት!
ቋንቋውን ለቻለ ፍትህን ሲያዳላ
.
እያየው አድጌ ከእርሱም ይባስ ብሎ
ሀገርህን ውደድ ይሉኛል ዘንድሮ!

የቷን???

በ ኪሩቤል አሰፋ
@gtm_na_tks
@gtm_na_tks
1.2K views£di, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 21:23:42 ባክህ ቶሎ አትምጣ...
--------------------------
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
.
ጥሩ እንዳደረጉ እንደሰሩ ደህና
ብለው ይፀልያሉ ጌታ ሆይ ቶሎ ና
እኔ ግን ምስኪኑ ሀጢያተኛ ልጅህ
ይችን ፀሎት ፀለይኩ ወድቄ ከደጀህ
አምላኬ፣
ካለሁበት ሀጢያት ነብሴን ሳላወጣ
በንስሀ ፀፀት እራሴን ሳልቀጣ
ባክህ ቶሎ አትምጣ!

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
@lula_al_greeko
1.1K views £NƏ`"`"`"`"`"`, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 18:40:01
ህይወትን ውደዱት
ምትወዱትን ህይወት ኑሩት

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.1K views £NƏ`"`"`"`"`"`, edited  15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 17:57:27 ሀ ልበል

ማፍቀር ምንማለት ነው እያልኩ የነበረ
በኔ ሲደርስብኝ ገባኝ እያደረ

ለካ ማፍቀር ማለት ስለሰው መኖር ነው
ከራስ ላይ ቀንሶ ለሰው መጨነቅ ነው

አይመስለኝም ነበር ተችሎ የሚኖር
የራስን ፍላጎት የትም ሚወረወር

ሳፈቅር ግን ገባኝ ላንቺ ብቻ ሳስብ
ማፍቀር እንደሚልቅ ከሰው አስተሳሰብ

አወ ዛሬ አወኩኝ የፍቅርን ትርጉም
ለካ የተፈቃሪን ህመም ነው አብሮ መታመም

አሁን ግን ኮራሁኝ አፍቃሪ ስለሆንኩ
ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሰውም ስለኖርኩ

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks
1.1K views £NƏ`"`"`"`"`"`, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ