Get Mystery Box with random crypto!

#ጸጋ #ለእኔ “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአል” (ቲቶ 2፥11) እንደሚል | Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

#ጸጋ #ለእኔ

“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአል” (ቲቶ 2፥11) እንደሚል ቃሉ የተገለጠው ጸጋ ካዳናቸው ሰዎች አንዱ ነኝ!

“ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን" እንዳለ ጸጋው እግዚአብሔር የማይከብርበትን አኗኗር ካስጣላቸው፣ ከኃጢአት እስራት ከፈታቸው ሰዎች ዋናው ነኝ!

"ይህም ጸጋ ... የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤” (ቲቶ 2፥12-13) እንደሚል ቃሉ እንዲህ እየሆነላቸው ካሉ የጸጋ ተማሪዎች አንዱ ነኝ!

“ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፥10) እንዳለ ጳውሎስ አገልጋይነትን የተቀበልኩት በጸጋ ነው! በተገለጠው ጸጋ ለብዙዎች መትረፍ እና ማረፍ ምክንያት ከሆኑት አንዱ ነኝ!

ጥቅምት 2011 ዓም  "ያንተ መልእክት ጸጋ ነው" የሚል ምሪትን ከመንፈስ ቅዱስ ተቀብያለሁ!. ጸጋ የምኖርበት አቅም ብቻ ሳይሆን የምኖርለት መልእክቴ እንደሆነ የተረዳሁት ጸጋን እንዳሁኑ ባልተረዳሁበት ሁኔታ ነበረ!

ጸጋ መልእክቴ እንደሆነ ከተረዳሁበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ከሁሉም የጸጋ አስተማሪዎች ተምሬያለሁ!

የጸጋን መልእክት በጸጋ ላለፉት 2 ዓመታት ብዙዎች ጋር አድርሻለሁ! በጸጋ ከመዳን ጀምሮ ጸጋን በመረዳት ወደ ማካፈል ያደገ ትውልድ አለኝ!

ጥቂት ከመባል የሚያልፉ አገልጋዮች የጸጋን ቃል ተቀብለው አገልግሎታቸውን እንዲያስተካክሉ ምክንያት ሆኛለሁ!

በቀሪው ዘመኔም በጸጋ እኖራለሁ! ለጸጋ እኖራለሁ!

በጸጋ የተጠቀማችሁ ቀጣዩን ሊንክ በመጠቀም ሌሎችን ጋብዙ!

በርናባስ ዘመነ
#Grace #Commission

https://t.me/gracecom