Get Mystery Box with random crypto!

.... ያንተ ድካም ከርሱ ስቃይ አይበልጥም.... ወንድሜ በየትኛውም አይነት ድካ | SEER SUNESIS // WISDOM & POWER🦁

.... ያንተ ድካም ከርሱ ስቃይ አይበልጥም....

ወንድሜ
በየትኛውም አይነት ድካም እና ስህተት ውስጥ ብትሆን አይዞህ እግዚአብሔር አሁንም ይወድሃል እግዚአብሔር አሁንም ይወድሻል እግዚአብሔር አንተን እና ድርጊትህን ለይቶ ነው የሚያየው እግዚአብሔር የሰው አይን የለውም እኛ እንደምናየው አያይም ለዚህም ነው እግዚአብሔር ልዩ አምላክ የሆነው ደካማውን የሚወድ ብርቱ ነኝ የሚለውን ደግሞ የሚያሳፍር

“ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤”
1ኛ ቆሮንቶስ 1፥27


እግዚአብሔር ከመጀመሪያውኑ ብርታትህን አይቶ ካልመረጠህ ብርታትህን አይቶ ምርጫውን አይቀጥልም ድካምህንም አይቶ ከፊቱ አይጥልህም ያንተ ድካም የእሱን ምህረት አይበልጥም ለዚህ ነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የምድራችንን የመጨረሻ ስቃይ በመስቀል ላይ የተሰቃየው ያንተ ድካም ያንቺ ድካም ያለልክ ካፈቀረህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ አይበልጥም
ዛሬም በየትኛውም ሁኔታ ብትሆን ፃድቅ ነህ በክርስቶስ ተወደሃል ተፈቅረሃል በእግዚአብሔር ፊት ቆመህ ከርሱ ጋር ማውራት ትችላለህ ምሕረቱን እና ፀጋውን ያለልክ መቀበል ትችላለህ

አንተ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ፅድቅ ነህ


Sunesis