Get Mystery Box with random crypto!

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ | Christ Exalting Channel

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

Artios Devotion
ⒺⓅⒽⒺⓈⒾⒶⓃⓈ
ⒹⒶⓎ #2

አስቀድሞ መርጦናል

የኤፌሶን መልዕክት 1:4-6
===================================
"በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ይኸውም፣ በሚወደው በእርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው።"
===================================

ሐዋርያው ጳውሎስ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ በቁ.3 ላይ የተናገረውን መንፈሳዊ በረከት መነሻና ዓላማ ያሳያል። የበረከቱ እቅድና ዝግጅት ጅማሬው ምድር ሳይሆን ሰማይ እንደሆ ጊዜውንም ደግሞ አሁን ሳይሆን ከፍጥረት በፊት እንደነበር ይናገራል።

እግዚአብሔር በራሱ ሉዐላዊነት በክርስቶስ በማመን ብቻ የሚገኘውን ድነት የሚቀበሉ ቅዱሳንን አስቀድሞ መወሰኑንና መምረጡን፣ ጊዜው ሲደርስ ደግሞ አስቦት የነበረውን እቅድ መተግበሩን ያሳያል።

አስቀድሞ ወስኖ መረጠን የሚሉ ቃላት ድነታችን በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫና ቸርነት ላይ የተጠነሰሰና የቤዛነት ፕሮግራም ጀማሪና ተቆጣጣሪ እርሱ ራሱ መሆኑንን አጉልቶ የሚያሳይ ነው።

ይህ ሲባል ከሰው የሚጠበቅ አንዳች ነገር የለም ማለታችን ግን አይደለም። ሰው ይህንን ትልቅ ግብዣ አውቆ፣ ፍቃዱን ተጠቅሞ በእምነት ተቀብሎ እያመሰገነ መኖር አለበት።

ድነት ሰው ነጻ ፍቃዱን ተጠቅሞ በክርስቶስ ሥራ ሲያምን የሚያገኘው ሕይወት ነው ወይስ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ አካል ተደርጎ አስቀድሞ የተመረጡ ሰዎች ብቻ የሚታደሉት ሲሳይ ነው? የሚለው ጥያቄ የሥነ መለኮት አጥኚዎች በየዘመናቱ የተለያየ ጎራ ፈጥረው የሚከራከሩበት ጉዳይ ነው።

ክቡር የሆነው ፀጋ እንዲመሰገን ታስቦ የተሠጠውን የዘላለም ሕይወት አውርደው ቋሚ የመከራከሪያ ርዕስ በማድረግ በተገናኙ ቁጥር በዚያ የሚበሻሸቁ አማኞችን ሳይ አዝናለሁ።

በእኔ እምነት ቃሉም የሚለው ድነቱ በትክክል የገባው ሰው ጎራ ፈጥሮ፤ የሙግትና የክርክር ችሎት ሰይሞ የሚቧቀስበት ጊዜ አይኖረውም። ስለ መዳን ሲታሰብ ክርክርና ሙግት ሳይሆን ምስጋናና አምልኮ ነው ከአማኙ ሕይወት ውስጥ የሚፍለቀለቀው። እግዚአብሔር ድነትን ሲሰጠኝ ምርምር የምሰራበትን ርዕስ ሳይሆን መቼም ተዋኝቶ በማያልቅ የምስጋና ባህር ውስጥ እንዳስገባኝ ነው የማስበው።

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የድነቴ ፕሮግራም ተነድፎ ነበር!

የዛሬው ፀሎቴ፦ "ጌታ ሆይ መመረጤንና መዳኔን እያሰብኩ ሁሌም በአምልኮና በውዳሴ በፊትህ የምሆን አመስጋኝ ሰው አድርገኝ"

ነገ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!!

ባይሣ ገመቹ
ሰኔ 11, 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን

@artios_media
@artios_media
@artios_media