Get Mystery Box with random crypto!

Word of GRACE Believers

የቴሌግራም ቻናል አርማ gospelofgrace — Word of GRACE Believers W
የቴሌግራም ቻናል አርማ gospelofgrace — Word of GRACE Believers
የሰርጥ አድራሻ: @gospelofgrace
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 141
የሰርጥ መግለጫ

WGGMtelegram channel is created to spread Zword of GraceGospel to every part of the world.lf U learn U can Change Ur Self& ZRest of Z world. @IKNOWWHOIAMINCHRIST ✟👈BY Z Word of Grace👑MINFESTING THE SUPER ABOUNDAT GRACE OFGOD.🌍

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 17:43:03
በቅርብ ቀን በዚህ የቴሌግራም ቻናን ላይ አዲስ ትምህርት ይጀመራል።

ምዕራፍ አንድ
#የእግዚአብሔር_ጽድቅ

በቅርብ ቀን #የእግዚአብሔር_ጽድቅ የሚል ትምህርት በቴሌግራም ቻናን ይተላለፋል።

Join and follow
https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8
16 views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 15:16:14
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል ቴሌግራም ቻናን ላይ ቤተሰብ የሆናችሁ ወንድሞች እና እህቶች በአዲስ መልክ ለመጀመር እናስባለን። ከዚህ ቀደመ በነበረው አገልግሎት Order ጠብቀን ማስተማር እንጀምራለን።

በዚህ የቴሌግራም ቻናን ላይ የሚተላለፉ ትምህርቶች፦

የእግዚአብሔር ጽድቅ

ጸጋ

አዲስ ፍጥረት

እምነት

በሕግ እና በጸጋ መካከል ያለው ልዩነት

የእግዚአብሔር መልካምነት

ትንሣኤ

የክርስቶስ ደም እና ሌሎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልዕክቶች እንማራለን።

Join and follow
https://t.me/+RadfKjJvYdaWhzed
28 views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 01:56:34
❝በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤
እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ
ከሞግዚት በታች አይደለንም።❞
--ገላትያ 3:24-25


የፀጋ ተቃዋሚ ሰይጣን ሳይሆን ሐይማኖት ነው።
የፀጋን ጉልበት የሚያዳፍኑ በአዲስ ኪዳን እየኖሩ በብሉይ ኪዳን ሕግ መገዛት ተገቢ እንደሆነ የሚቆጥሩ ሐይማኖተኞች እንጂ ሰይጣን ፀጋን የማዳፈን አቅም አልተሰጠውም።
ጌታ ኢየሱስ በምድር ባገለገለበት ዘመን ዋነኛ ተቃዋሚዎቹ ፈሪሳዉያን(ሐይማኖተኞች)ነበሩ።
ከአሮጌው ሥርዓት(ከብሉይ ኪዳን) ሕግ ሙሉ በሙሉ ያልተላቀቀ አዕምሮ በአዲሱ ሥርዓት(በአዲስ ኪዳን) የፍቅር ሕግ እንደሚገባ መመላለስ ስለማያስችል ፀጋን በሙላት ሊገለገልበትም ሆነ ሊያገለግልበት አይችልም።
ፅድቅን በተመለከተ፤ሐይማኖተኞች እንደሚሉት በኢየሱስ ተጀምሮ በሰው ሥራ የሚቀጥልና ከፍፃሜ የሚደርስ ለሰው የቀረ ድርሻ የለም።
የሰው አስተዋፅዖ ያልተጨመረበት እውነተኛው የእግዚአብሔር ፅድቅ ክርስቶስ ራሱ ነው።
ያ ፅድቅ ደግሞ የሚገኘው ሕግን በመጠበቅ በሥራ ሳይሆን በእምነት ነው።

❝አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት #የእግዚአብሔር_ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥
እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።❞
ሮሜ 3:21-22

የእግዚአብሔር ፅድቅ የሚገኘው ❝ለሚያምኑ ሁሉ እንጂ ለሚሰሩ(ሕግን ለሚጠብቁ ሁሉ)❞ አልተባለም።
በፀጋ ሥር ሆኖ፤ሕግን በመፈፀም(በሥራ) ጽድቅን መፈለግ
የክርስቶስን ሞት ከንቱ ማድረግ ነው።
❝ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።❞
—ገላትያ 2: 21


የመረጃ ምንጭ Milka Yonatan Facebook page የተወሰደ ነው።

http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
44 views22:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 16:50:24
የልጅነት ዘር ሃይል - Sneak peak videos ll Apostle Zelalem Getachew

http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
35 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 16:08:03 #ምን_ታስባለህ???

#ትኩረትህን_ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት
#በክርስቶስ የሆነው ማንነትህ ላይ አድርግ።

#ከሚያጉረመርሙና ስንፍናን ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ከመዋል ይልቅ ራስህን #በእምነት በበረቱ እና እምነትን_በሚናገሩ_መልካምን_ነገር_በሚያውጁ እና #በክርስቶስ በሆኑት ነገር ላይ በሚያተኩሩ ሰዎች ክበብ።

#እንግዲያስ_እምነት:ከመስማት ነው:መስማትም:በእግዚአብሔር _ቃል :ነው።
ሮሜ 10፦17

LET THE REVOLUTION BEGIN

የጸጋ አብዮት በክብርና በኃይል https://t.me/revolutionbygrace
45 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 19:36:58
...ቃሉ በሕይወቴ ለምን አይሰራም???

“የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ ስለታም ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።”. ዕብ 4:12

የሚሰራው የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሰው ልጆች መጥቶ በሰው ልጆች ህይወት ውስጥ ለምንድን ነው ለውጥ የማያመጣው? የሚል ጥያቄ በርካታ ሰዎች ያነሳሉ።
እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል ስሰበክ እና በተለያየም መልኩ ስማር ቆይቻለሁ ነገር ግን የሰማኋቸው ቃሎች በአመታት ውስጥ በእኔ ህይወት ላይ ለውጥን ለምንድን ነው ያላመጡት? የሚል ጥያቄ መጠየቁ የማይቀር ነው።

ታዲያ መልሱ ምን ይሆን?

“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።”
ዕብ 4፥2

የእግዚአብሔር ቃል በራሱ የማይጠቅም ቃል ስለሆነ አይደለም! የእግዚአብሔር ቃል ይጠቅማል። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል ከመጣ የሚፈልገውን ነገር ሳያደርግ፣ ነገሮችን ሳይለውጥ እና የመጣበትን አላማ ሳይፈፅም አይመለስም።

የሰማነው ቃል ያልጠቀመን ምክንያት ከእኛ ጋር በእምነት ስላልተዋሃደ ብቻ እና ብቻ ነው!

የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰል በክርስትና ህይወታችን ላይ መተኪያ የሌለው በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ነው፤ ምክንያቱም የሰማነውን ቃል በማሰላሰል እና ቃሉን ከእኛ ጋር በማዋሃድ በህይወታችን ላይ ውጤት እናመጣለን።

በመጨረሻም ከእኛ ጋር የተዋሃደው የእግዚአብሔር ቃል ተመልሶ ከአንደበታችን ሲወጣ ከፍተኛ የሆነ ለውጥን ያደርጋል። ስለዚህ ከቃሉ ጋር መዋሃድ ለመዋሃድ ደግሞ ማሰላሰል ውጤት ለተሞላ ህይወት መሰረት ነው።

መልካም ቀን!
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ


@GospelTvEthiopia
57 views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:38:33 አነቃቂ ንግግሮች Vs የእግዚአብሔር ቃል
********

ሳይኮሎጂ እንደመማሬ ብዙ አነቃቂ ንግግሮችን አውቃለሁ!! ነገር ግን ብዙ አነቃቂ ንግግሮችን አንድ ሺህ ጊዜ ከምናገር ይልቅ አንዱን ኢየሱስ አንድ ሺህ ጊዜ መናገር እመርጣለሁ!!

በአነቃቂ ንግግሮች የሚነቃቃ ሰው እንጂ አንድስ እንኳ ሕይወት የሚያገኝ ፣ ጸጋ የሚካፈል ሰው የለም!!

ኢየሱስ የሌለበት አነቃቂ ወሬ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የለም!!

አነቃቂ ንግግሮች ራስህን እወቅ ፣ አቅምህን እወቅ!!
የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስን እወቅ አቅምህ እሱ ነው!!

አነቃቂ ንግግሮች ሰው ተኮር ናቸው የተናጋሪውን ብቃት አጉልተው ያሳያሉ!!
የእግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ተኮር ነው እግዚአብሔርን ያከብራል!!

አነቃቂ ንግግሮች የችግርህ ቁልፍ 17 መንገዶች በእጅህ ናቸው ይልሀል!!
የእግዚአብሔር ቃል የችግርህ ቁልፍ አንዱ ኢየሱስ ነው ይልሀል!!

አነቃቂ ንግግር ከሰማህ በሗላ ለተናጋሪው ታጨበጭባለህ!!
የእግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ በሗላ ለኢየሱስ ታጨበጭባለህ!!

አነቃቂ ንግግር ፍርሀትህን የምታሸንፍባቸው 13 መንገዶች ይልሀል!!
የእግዚአብሔር ቃል አትፍራ እኔ ላንተ ጋሻህ ነኝ ፤ የፍርሀት መንፈስ አልተሰጠህም ይልሀል!!

አነቃቂ ንግግር የራስህ ረዳት ራስህ ነህ ይልሀል!!
የእግዚአብሔር ቃል የራስህ ረዳት ራስህ ሳትሆን እኔ ነኝ ይልሀል!!

አነቃቂ ንግግር በራስህ ተማመን ይልሀል!!
የእግዚአብሔር ቃል በእኔ ተማመን ይልሀል!!

አነቃቂ ንግግር ራስህን ከጣልክ ማንም አያነሳህም ይልሀል!!
የእግዚአብሔር ቃል አልጥልህም አልተውህም ይላል!!

አነቃቂ ንግግር በቃልና በጥበብ ብልጫ ይነገራል!!
የእግዚአብሔር ቃል መንፈስንና ሀይልን በመግለጥ ይነገራል!!

እስኪ ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈውን እንመልከት፦
❝እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም።በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና።❝እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።❞
— 1ኛ ቆሮንቶስ 2 ፥ 1-5

❝ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም።❞
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4 ፥ 2

ልንነቃቃም ልናነቃቃም አልተጠራንም!!

የምንሰብከው የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ራሱን ክርስቶስ ነው!!



#ሄኖክ_አሸብር
53 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 22:00:05
....ምስጋና ማንነቴ!!!

“.... በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
— ሶፎንያስ 3፥20

“ይኸውም በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።”
ኤፌሶን 1:12


ምስጋና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናደርገው ነገር ብቻ ሳይሆን የተደረግነውም ነገር ነው። እግዚአብሔር ምስጋና ከእኛ የሚፈልገው እኛን ለምስጋና ስላደረገን ነው። እግዚአብሔር ያለደረገልንንና ባላደረገን ነገር ሁኑ ብሎ አይጠይቀንም፣ ባደረገን ነገር ግን ምስጋናን አቅርቡ ብሎ ይጠይቀናል!

“ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው።”
— ኤፌሶን 1፥12


እግዚአብሔር በቃሉ የሚነግረን አመስጋኞች ብቻ ሳይሆን ራሳችን ምስጋና እንድንሆን ነው። ስለዚህ ምስጋና ለአማኞች በመደረግ እና ባለመደረግ የሚመሰረት ሳይሆን ስብእናችን ወይም ማንነታችን ነው። ስብእናችን የሆነ ነገር ማንም ከእኛ ሊወስድብን አይችልም ፤ ማንነታችን በሆነ ነገር ላይ ልንታገል አይገባም።

#እግዚአብሔር_የምስጋናን_ስብእና_እኛ_ጋር_ሳይፈጥር_አመስግኑኝ_አይለንም

እግዚአብሔር አባታችን ራሳቸው ምስጋና እንደሆኑ በተረዱ ሰዎች ማንነቱን መግለጥ ይፈልጋል ። ምስጋና መሆናቸው የተረዱ ሰዎች ዘወትር ሲያመሰግኑ እግዚአብሔር ቀጥታ በምስጋናቸው ውስጥ ይመጣል።

“ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”
— መዝሙር 50፥23


ምስጋና ማንነታቸው እንደሆኑ የተረዱ ሰዎች እግዚአብሔር የሚያመሰግኑት አመስግኑት ተብለው ተቀስቅሰው ሳይሆን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ስለሆነ ነው።

መልካም ቀን
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

@GospelTvEthiopia
@GospelTvEthiopia
78 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 17:43:26 @whoweareinchrist
#መከራን_እንታገስ_ወይስ_በመከራ_ውስጥ_እንታገስ????
በተለያየ መንገድ መከራ አማኞች ላይ ሊደርስ ይችላል ነገር ግን መከራውን እንድንሰብክ አልተጠራንም(ዮሐ 16:33)
አንድ ባህላዊ(Traditional) አባባል አለ መከራ እና ችግር እምነትን ያሳድጋል የሚል ይህ ግን መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም

#እምነት_የሚያድገው_በእግዚአብሔር_ቃል_ነው። (ሮሜ 10:17፤ እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።) እምነት በእግዚአብሔር ቃል የሚመጣ ከሆነ በደንብ(More) #የእግዚአብሔር_ቃልን_ስንሞላ_እምነታችን_ያድጋል።
ነገር ግን መከራ እና ችግር እምነታችንን ይፈትናል(Challenge ያደርጋል) የዛኔ ግን የተፈተነው እምነታችን ትዕግስትን ያስገኝልናል።
ያዕቆብ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤
³ ምክንያቱም #የእምነታችሁ_መፈተን #ትዕግሥትን_እንደሚያስገኝ_ታውቃላችሁ።
“በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ #ምክንያቱም_መከራ_ትዕግሥትን_እንደሚያስገኝ_እናውቃለን።”ሮሜ 5፥3 (አዲሱ መ.ት)
#ስለዚህ_መከራ_ሲደርስብን_መከራውን_ሳይሆን የምንታገሰው የተነገረን የተስፋ ቃል ላይ ሙጭጭ ብለህ በትዕግስት እምነታችንን ሳንጥል እንድንኖር ነው መፅሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን። #ምክንያቱም_ትዕግሥት_ማለት_ቁጭ_ብሎ_መጠበቅ_ማለት_ሳይሆን_ትዕግሥት_ማለት_ፅናት(#endurance) #ማለት_ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር አለምን በወንጌል ትዞራለህ ካለህ #ትዕግሥት ማለት በቃ አንድ ቀን ቀኑ ሲመጣ እዞራለው ብሎ #መቀመጥ #ሳይሆን_እግዚአብሔር_የተናገረውን_የተስፋ_ቃል_ይዞ_እዛ የተስፋ ቃል #ላይ_መፅናት_ማለት_ነው።
“#በእምነትና #በትዕግሥት_የተስፋውን #ቃል_የሚወርሱትን_እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።” ዕብ 6፥12 (አዲሱ መ.ት)
“#አብርሃምም #በትዕግሥት_ከጠበቀ #በኋላ_የተሰጠውን_ተስፋ_አገኘ።”ዕብ 6፥15 (አዲሱ መ.ት)
አንድ የእግዚአብሔር ሰው ስለ ትዕግስት እንዲህ ብሎ ነበር "#ትዕግስት_የመንፈስ_ፍሬ_እንጂ_የመከራ_ፍሬ_አይደለም።" ገላትያ 5:22፤ #የመንፈስ_ፍሬ_ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ #ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት.......
#ትዕግስት_የእግዚአብሔር_ባህሪ #ነው "
እግዚአብሔርም በፊቱ አልፎ። እግዚአብሔር፥ #እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ #ታጋሽም፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፥" (ዘጸ 34:6)
".....#ማንም_እንዳይጠፋ_ወዶ_ስለ_እናንተ_ይታገሣል።"(2ኛ የጴጥ 3:9)
ስለዚህ እምነት ከፍቅር ጋር እንደሚሰራ ሀሉ ከትዕግስትም ጋር ይሰራል
ስለዚህ ሁልጊዜ ስለ ትዕግሥት ስናስብ ማሰብ ያለብን ትዕግሥት በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚመሠረት ነው። #ስለዚህ_ትዕግሥት_ማለት_በእግዚአብሔር_ቃል_ላይ_መፅናት_ነው።
#ለምሳሌ የስንዴ ዘር ዛሬ ዘርተህ ነገ መብቀል አለበት አትልም መሬቱ የፈለገ አመቺ ቢሆንም ዝናቡ በትክክል ቢዘንብም ስንዴ አድጎ ለማፍራት የሚፈልገው ጊዜ አለ ስለዚህ ገበሬው መታገስ አለበት ማለት ነው።
ስለዚህ በትዕግስት በመፅናት በእግዚአብሔር ላይ ባለን እምነት ሳንጠራጠር እንድንኖር መፅሐፍ ቅዱሳችን ያስተምረናል።
ዕብ 6:12-18( ህያው ቃል)
እንዲሁም እግዚአብሔር ተስፋ ለሰጣቸው ሰዎች የተናገረውን #ቃሉን #የማያጥፍ #መሆኑን በዕርግጥ #አውቀው #በትዕግስት እንዲቆዩ ቃሉን በመሃላ አረጋግጦላቸዋል።****እግዚአብሔር መዋሸት ስለማይችል በተስፋውና በቃል ኪዳኑ #የማይናወጥ_እምነት_ሊኖረን_ይገባል።(Emphasis added)

ያዕ 5:11፤ እነሆ፥ #በትዕግሥት_የጸኑትን_ብፁዓን_እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።
ቡሩካን ናችሁ!!!!!!!!!!!!!!

@whoweareinchrist
72 views14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 20:12:37 የትንሣኤ በአል በአለም ዙሪያ እንዴት ይከበራል?
በክርስትና እምነት ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው በአላት መካከል ዋንኛ የሆነው የትንሣኤ በአል ነው፡
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰለሰው ልጆች ኃጢያት በመስቀል ላይ መሞቱንና መነሳቱን ለማሰብ በመላው አለም ያሉ ክርስቲያኖች የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በአልን ያከብራሉ፡፡
ይህ የትንሳኤ በአል አከባበር በየአካባቢው የተለያየ ሲሆን ከሃይማኖት ይልቅ ባህልነቱ ጎልቶ የሚታይባቸው አካባቢዎች በረካታ ናቸው ፡፡
እስኪ በተለያዩ የአለም ሃገራት ያለውን የበአሉን አከባበር እንመለከት፦
የፓስፊክ ሃገራት፡በሆኑት አውስትራሊያና ኒውዚላንድ የትንሣኤ በአልን የሚያከበሩት በእነርሱ የበልግ ወራት ሲሆን ለበአሉ ያዘጋጁትን ትኩስ ዳቦ በመብላት ያከብሩታል፡፡
አፍሪካ፡ በአብዛኛው የአፍሪካ ሃገራት የትንሳኤ በአል ከሃሙስ ጀምሮ እስከ እሁድ ለተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡አብያተ ክርስቲያናት በእነዚህ ቀናት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ የሚዘክሩ የተለያዩ መረሃግብሮችን የሚያከናውኑ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ከትንሳኤ እሁድ ቀጥሎ ያለው ሰኞ በብሄራዊ ደረጃ “ የቤተሰብ ቀን” የሚል ስያሜ ተሰቶት ሰዎች ከቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡
እስያ፡ የተለያዩ ህዝቦችና ባህሎችን ያቀፈ ሰፊ አህጉር እንደመሆኑ የትንሣኤ በአለም በተለያዩ መልኩ ይከበራል፡፡ከ 7000 በላይ ደሴቶች ስብስብ በሆነችው ፊልኪፒንስ የሚደረገው ለየት ያለ የትንሳኤ በአል አከባበር አለ፡፡በዚህ ቀን በጎዳናዎች ላይ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ህማማት የሚያሳዩ የተለያዩ ትሪኢቶች ይካሄዳሉ፡፡በመጨረሻም ወንዶች የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ የሚያሳይ ምስል ሴቶች ደግሞ ማርያምን በመወከል ጥቁር የለበሰች ሴትን በመከተል በሰልፍ ወደ ቤተክርስቲያን ያመራሉ፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥም የጌታን ትንሣኤ የሚያሳዩ የተለያዩ ትዕይንቶች በማከናወን በአሉን ያከብራሉ፡፡ውስን የክርስቲያን ቁጥር ባለባት ህንድና በሌሎች የእስያ ሃገራት ትንሣኤ በባህላዊ መልኩ የሚከበር ሲሆን “ የጸደይ በአል” ብለውም ይጠሩታል፡፡
አውሮፓ፡ የኦርቶዶክስ ክርስትናን በሚከተሉ ሮማኒያ፤ሰርቢያ እና ግሪክ በመሳሰሉ የአውሮፓ ሃገራት የትንሣኤ በአልን ከሌሎቹ የአውሮፓ ሃገራት ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ዘግይተው የሚያከበሩ ሲሆን በበአሉ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርአቶችን ይፈጽማሉ፡፡ በጀርመን ትንሳኤን ለማክብር እንቁላሎችን የተለያዩ ቀለማትን በመቀባት የማስዋብና በዛፍ ቅርንጫፎች ላይ የማንጠልጠል ባህል አላቸው፡፡ በፈረንሳይ ባስሪ ከተማ ለትንሣኤ በአል ህዝቡ ተሰብስቦ በእንቁላል የሚዘጋጅ ትልቅ ኦምሌት የተሰኘ ምግብ ያዘጋጃሉ፡ ለዚህም በሺ የሚቆጠሩ እንቁላሎችን ይጠቀማሉ፡፡
አሜሪካ፡ በአሜሪካ አህጉር የተለያዩ የትንሣኤ በአል አከባበሮች አሉ ፡፡ ቤርሙዳ በሚባለው የአህጉሩ ክፍል በስቅለት ቀን በወረቀት ላይ የ’ኢየሱስን’ ምስል በመሳል በአየር ላይ እንዲንሳፈፍ ያደረጋሉ፡፡ይህንንም የጌታን እርገት ለማሰታወስ ነው ይላሉ፡፡በኮሎምቢያ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት አብዛኛው ስው ከስራ ውጪ በመሆን የቤተክርስቲያን መረሃግብሮችን በመካፈልና ወዳጅ ዘመድን በመጎብኘት ያሳልፋሉ፡፡በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የቤተክርስቲያናትን ፕሮግራሞች በመታደም፤ እንቁላሎችን ቀለም በመቀባትና ጣፋጭ ምግቦችን በመመገብ ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ በአሜሪካ በ2018 አ.ም ለዚህ በአል የጣፋጭ ምግቦች ዝግጅትና ግዢ ከ 2.8 ቢሊየን ዶላር በላይ ውጭ እንደተደረገ የሃገሪቱ የግዢ ተቋም አሳውቆ ነበር፡፡
በአብዛኛዎቹ የአለም ሃገራት ያለውን ይህንን የትንሣኤ በአል አከባበር ስንመለከት ከክርስትና እምነት ይልቅ ባህላዊ እሴቱ የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በትንሣኤው ለሰው ልጆች ያደረገውን ታላቅ የማዳን ስራ ከማጉላት ይልቅ በምግብ፤ በመጠጥና በፈንጠዝያ የተሞላ አከባበርን እናስተውላለን፡፡ ይህም በጣም በርካታ ህዝብ ከጌታ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ እውነት ምን ያህል ርቆ እንዳለ እንረዳለን፡፡
1ኛጴጥሮስ 1፡3-4 ‘ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።’
እንደሚል በዚህ ወቅት ትንሣኤው ለህያው ተስፋ ና ለማያልፍ ርስት ዳግም የተወለድንበት መሆኑን ልናስብና እግዚአብሄርን ልናመሰግን ሰዎች ሁሉ ወደዚህ እውነት እንዲመጡም ልንጸልይ ይገባናል እንላለን፡፡
78 views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ