Get Mystery Box with random crypto!

❝እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግ | የእግዚአብሔር ወንጌል

❝እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።❞
—ኤፌሶን 2: 19
×××××××
በሃጢአታችን ምክንያት መላ ማንነታችን የተበላሸ እና ከእግዚአብሔር ክብር የጎደለ በመሆኑ ለእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን እንኖር ነበር። እግዚአብሔር ቃልኪዳን ካደረገላቸው እስራኤል በመራቃችን ደግሞ ከተስፋም ፈጽሞ ርቀን ነበር። ነገር ግን አሁን እኛ ራሳችን በመንፈስ እስራኤል ሆነን ከቃልኪዳን ማህበረሰብ ተቆጥረን የአንድ ሃገር ዜጎች ሆነናል። ዜግነታችንም ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ሠማያዊ ነው። አስደናቂው ነገር ይህ ብቻ አይደለም።የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሆነናል። ልጆች በመሆናችንም ወራሾች ተደርገናል። ስለዚህ 'ከእንግዲህ ወዲህ' ተብሎ ታሪክ ይጻፍልናል። ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ አንዱ ቅዱስ በመስቀል ላይ የተቀበለው ስቃይ ነው።

__ተስፋጽዮን አለማየሁ (መጋቢ)

@Gospel_of_God @Gospel_of_God
@Gospel_of_God @Gospel_of_God