Get Mystery Box with random crypto!

አቡነ ሼኖዳ ሳልሳዊ #Ethiopia | የዚህ መጽሐፍ ታሪክ **** #Ethiopia | ከእዚ | 💯

አቡነ ሼኖዳ ሳልሳዊ

#Ethiopia | የዚህ መጽሐፍ ታሪክ

****
#Ethiopia | ከእዚህ መጽሐፍ ላይ የተፃፉት ነገሮች በሙሉ ከ1951 ዓ.ም ጀምሮ “የመንፈስ መውጣት” በሚል ርዕስ በወቅቱ የገዳማዊ ሕይወቴን ከመጀመሬ በፊት የ መጽሔት አዘጋጅ በነበርኩበት ጊዜ ላይ፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቶች መጽሔት ላይ ሲፃፉ የነበረ የመጣጥፍ ጽሑፎች ስብስብ ነው ።

እነዚህ መጣጥፎች እና የተወሰኑት በመጽሔቱ ላይ ስፅፋቸው ከነበሩ ግጥሞች ጋር በ1957 ዓ.ም ላይ በመፅሐፍ መልክ ታትመው ለመጽሐፍትነት በቅተዋል።

ይህን መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳተምኩት መጽሐፍ ሲሆን በብዙዎች የመጽሐፉ አንባቢዎች ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ ስለነበረ ለብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ሲታተም የነበረ መጽሐፍ ነው።

በዚህ አይነትም አራተኛው የመጽሐፉ ህትመት፣ እንደ ኤጲስ ቆጶስነት ከመሾሜ በፊት እና ገና መነኩሴ እያለሁ የጻፍኳቸውን አንዳንድ ማሰላሰያዎችን (ተመስጦዎችን) እና ግጥሞችን በውስጡ አካትቶ ከመያዙም በላይ " የመንፈስ መለቀቅ"ን በተመለከተ የፃፍኩት መጣጥፍን እንደ መፅሐፉ መግቢያ አካትቶ ለህትመት በቅቷል።

በዚህ አምስተኛው የመጽሐፉ ዕትም ላይም ቢሆን በተመሳሳይ ርዕስ የተፃፈ ሌላ መጣጥፍ እንደ መግቢያ ተጨምሮበት ለ ህትመት ሊበቃ ችሏል።

በሚቀጥሉት የመጽሐፉ ህትመቶች ላይም ቢሆን ሌሎች በ "የመንፈስ ነፃ መውጣት " ርዕስ ላይ የተፃፉ መጣጥፎችን እንድንጨምር እግዚአብሔር እንደሚፈቅድልን ተስፋ እናደርጋለን።

***
አቡነ ሼኖዳ ሳልሳዊ

አከፋፋይ፦0933996449
#Facebook_telegram_tiktok
https://t.me/Goodnessprevails_ETH
https://www.facebook.com/Goodnessprevails.ETH
https://vm.tiktok.com/ZMLv338SY/