Get Mystery Box with random crypto!

በጉጂ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ575ሺ በላይ ዜጎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል 6ሺ በላይ የሚሆኑ | GONCHA PLUS 🌍

በጉጂ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ575ሺ በላይ ዜጎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል

6ሺ በላይ የሚሆኑ ህጻናት የከፋ ችግር ላይ ናቸው

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በአጠቃላይ 18 ወረዳች የሚገኙ ሲሆን በ9 ወረዳዎች ከ575 ሺ 675 በላይ ዜጎች ለረሀብ ተጋልተጠዋል ሲሉ የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮሀንስ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከ77ሺ በላይ ህጻናት ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6ሺ 400 ህጻናት ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። በመሆኑም በአፋጣኝ የተመጣጠነ ምግብ እና ህክምና ካላገኙ ከዚህ የከፋ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ኃላፊው ለጣቢያችን ተናግረዋል።


በወረዳዎቹ 819ሺ 192 በላይ እንስሳቶች ግጦሽ እና ውሃ ባለማግኘታቸው ለድርቅ አደጋ እንደታገለጡ እና በየእለቱ ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ተገልጿል።

በመሆኑም በተከሰተው ድርቅ የምግብ፣ የመድሀኒት ፥ የውሃ እና የግጦሽ ችግር በሰፊው እየተስተዋለ በመሆኑ መንግስታዊ ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአፋጣን ድጋፍ ካላደረጉ የሰዎች ህይወት አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ   አቶ ዮሀንስ ወርቁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡


በዞን ባሳለፍነው 2014 ዓመት በተከሰተዉ ረሃብ እና ድርቅ የተነሳ ከ700 ሺ በላይ የሚሆኑ እንስሳት ለሞት መዳረጋቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡